ሕዝቅኤል 29:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመንግሥታት ሁሉ ይልቅ የተዋረደች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲያ በሕዝቦች ላይ ከፍ ከፍ አትልም፤ በሕዝቦችም መካከል እንዳይገዙ አሳንሳቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመንግሥታት ሁሉ አነስተኛ ትሆናለች፤ ከሌሎችም አሕዛብ በላይ ራሷን ከፍ ማድረግ አትችልም። እጅግ ደካማ አደርጋታለሁ፤ ስለዚህ ሌሎችን አሕዛብ እንደ ገና መግዛት አትችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም ከሁሉ የደከመ መንግሥት ስለሚሆን ዳግመኛ ሌሎች መንግሥታትን የመግዛት ዕድል አይኖረውም፤ ከሁሉ ያነሰ ስለማደርገው ሌላ መንግሥት ማስገበር አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ገና በአሕዛብ ላይ ከፍ ከፍ እንዳይሉ ትንሽ መንግሥት ይሆናሉ፤ በአሕዛብም ላይ እንዳይበዙ አሳንሳቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ ይልቅ የተዋረደች ትሆናለች፥ ከእንግዲህ ወዲያ በአሕዛብ ላይ ከፍ አትልም፥ በአሕዛብም ላይ እንዳይገዙ አሳንሳቸዋለሁ። |
በበቀለም ጊዜ ቁመቱ አጭር፥ ሐረጉ ወደ እርሱ የሚመለስ፥ ሥሮቹም በበታቹ የነበሩት ሰፊ ወይን ሆነ፥ ወይንም ሆነ፥ ቅርንጫፎችን አበቀለ፥ ቅጠልም አወጣ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶችን አስወግዳለሁ፥ ምስሎችንም ከኖፍ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከግብጽ ምድር ገዢ አይነሳም፥ በግብጽ ምድር ላይ ፍርሃትን አኖራለሁ።
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።
እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕር ሞገድም ጸጥ ያሰኛል፥ የዐባይም ወንዝ ከጥልቀት ይደርቃል። የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይጠፋል።