La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 25:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍልስጥኤማውያን በቀልን አድርገዋልና፥ በዘወትርም ጠላትነት ያጠፉ ዘንድ በነፍሳቸው ንቀት ተበቅለዋልና

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ፍልስጥኤማውያን በቂም ተነሣሥተው በክፉ ልብ ተበቅለዋልና፣ ይሁዳንም በቈየ ጠላትነት ለማጥፋት ፈልገዋልና፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ፍልስጥኤማውያን በማያቋርጥ ጠላትነት በቀልን ተበቅለዋል፤ ይህም የጥፋት በቀል ተንኰልን በተመላ ልብ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ በቀ​ላ​ቸ​ው​ንም አጽ​ን​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠፉ ዘንድ ነፍ​ሳ​ቸው ደስ ይላ​ታ​ልና፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍልስጥኤማውያን በቀልን አድርገዋልና፥ በዘወትርም ጠላትነት ያጠፉ ዘንድ በነፍሳቸው ንቀት ተበቅለዋልና

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 25:15
22 Referencias Cruzadas  

ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ የአገሩም ተወላጆች የጌት ሰዎች ከብቶቻቸውን ሊወስዱ ወርደው ነበርና የገደሉአቸው ልጆቹ ኤድርና ኤልዓድ ነበሩ።


ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።


ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።


የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥


ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዘመን ይህ ሸክም ሆነ።


ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።


የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዑፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዛጦንንም ትሩፍ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኤዶም በይሁዳ ቤት ላይ በቀል ተበቅሎአልና፥ በዚህም በደለኛ ሆኗል፥ በእነሱም ላይ ተበቅሎአልና፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥


የዘለዓለም ጥል ስላለህ በመጨረሻው የፍርዳቸው ጊዜ፥ በመከራቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፥