La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 23:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የድንጋጤና የጥፋት ጽዋ በሆነው በእኅትሽ በሰማሪያ ጽዋ፥ በስካርና በኀዘን ትሞዪአለሽ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፣ በመፍረስና በጥፋት ጽዋ፣ በስካርና በሐዘን ትሞዪአለሽ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንቺ በስካርና በሐዘን የተሞላሽ ትሆኚአለሽ፤ የእኅትሽ የሰማርያንም የጥፋትና የውድመት ጽዋ ትጠጪአለሽ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ኅ​ትሽ በሰ​ማ​ርያ ጽዋ፥ በድ​ን​ጋ​ጤና በጥ​ፋት ጽዋ፥ በስ​ካ​ርና በው​ር​ደት ትሞ​ሊ​ያ​ለሽ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእኅትሽ በሰማሪያ ጽዋ፥ በድንጋጤና በጥፋት ጽዋ፥ በስካርና በውርደት ትሞልያለሽ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 23:33
6 Referencias Cruzadas  

ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል።


ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።


አንተም፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምልከው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም፥ ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው።


በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል፤ ስለዚህ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ እሰጥሻለሁ።


በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።