ቀና ብለው በጫጫታ መካከል ብዙ ሰዎች ሲመጡ አዩ፤ ሙሽራው፤ ሚዜዎቹና ወንድሞቹ ብዙ ጓዝ ይዘው ከአጀቡ ፊት ፊት እየሄዱ፥ ከበሮ እየመቱ፥ እየዘፈኑ በጦርነት ጊዜ እንደሚሆነው የደመቀ ትርኢት እያሳዩ ሲመጡ ተመለለከቱ።