የይሁዳ አገርና ሦስቱን አገርና በኢየሩሳሌም መሥዋዕት ለሚያቀርቡ ሰዎች ጥቅም እንዲውሉ እነዚህ አውራጃዎች በአካባቢያቸው ከሚገኙ አገሮች ሁሉ ጋር ከሰማርያ ተነጥለዋል፤ ቀድሞ ንጉሥ በየዓመቱ ይቀበላቸው የነበሩት የመሬታቸውና የዛፎቻቸው ፍሬዎች ግብሮች ለእነርሱ ይሆናሉ፤