ዮናታንና ሕዝቡ እነዚህን ቃሎች በሰሙ ጊዜ አናምንም ቃሎቹንም አንቀበልም አሉ፤ ምክንያቱም ዲሜጥሮስ በእስራኤል ላይ ያደረገው ክፉ ነገር ሁሉና በነእርሱ ላይ የፈጸመው ከባድ ጭቆና ገና ከአሳባቸው አልጠፋም ነበር።