እንደ እግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር ፍጹም ፍትሃዊ እንደሆነ ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ፍትህ የእግዚአብሔር ባህሪ አንዱ መገለጫ ነው።
እግዚአብሔር በራሱ ፍጹም ፍትሃዊ ነው። ከቅድስናው ጋር የሚቃረንን ሁሉ ይቃወማል። ይህ ፍጹም ንጽሕናውን ያሳያል።
በሮሜ 2:6-10 ላይ "እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍላል። በመልካም ሥራ ጸንተው የሚኖሩ፣ ክብርንና ሞገስን፣ የማይጠፋንም ሕይወት የሚሹ፣ የዘላለም ሕይወትን ያገኛሉ። ለእነዚያ ግን ለእውነት በማይታዘዙ፣ በዓመፅም ጸንተው በሚኖሩ፣ ቁጣና መዓት ይጠብቃቸዋል። ክፉ የሚያደርግ ሰው ሁሉ መከራና ጭንቀት ያገኘዋል፤ አይሁዳዊ ሳይቀድም፣ ግሪካዊ ይከተላል። መልካም የሚያደርግ ሰው ግን ክብርንና ሞገስን፣ ሰላምንም ያገኛል፤ አይሁዳዊ ሳይቀድም፣ ግሪካዊ ይከተላል።" ተብሎ ተጽፏል።
እግዚአብሔር ፍትሃዊ ስለሆነ የእርሱ ፍትህ የባህሪው መገለጫ ነው። ይህንን ማስታወስ እና በዚህ እውነት መጽናናት እንችላለን።
“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
ማንኛውም ሰው በሥልጣን ላሉት ሹማምት መገዛት ይገባዋል፤ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።
እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት ብፁዓን ናቸው!
ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?
ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ። ወገን የሌለውንና ድኻውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።
ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤ እግዚአብሔር የዕውራንን ዐይን ያበራል፤ እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድኻ አደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትሕን ለንጉሥ፣ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጡለታል፤ የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣ እጅ መንሻ ያቀርባሉ። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል። ድኻው በጮኸ ጊዜ፣ ችግረኛውና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል። ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ድኾችንም ከሞት ያድናል። ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ ደማቸውም በርሱ ፊት ክቡር ነው። ዕድሜው ይርዘም! ወርቅም ከሳባ ይምጣለት፤ ዘወትር ይጸልዩለት፤ ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት። በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ። ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ። ሕዝቦች ሁሉ በርሱ ይባረኩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው። ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ። አሜን፤ አሜን። እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።
“በዳኝነት ጊዜ በድኻው ላይ ፍርድ አታጓድልበት። ከሐሰት ክስ ራቅ፤ በደል የሌለበትን ወይም ጻድቁን ሰው ለሞት አሳልፈህ አትስጥ፣ በደለኛውን ንጹሕ አላደርግምና።
ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው! የጣዖታትን መንግሥታት፣ ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ መንግሥታት የሚበልጡትን እጄ እንደ ያዘች ሁሉ፣ በሰማርያና በጣዖቶቿ ያደረግሁትን፣ በኢየሩሳሌምና በተቀረጹ ምስሎቿስ እንዲሁ አላደርግምን?” ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤ “ ‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤ ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና። የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤ ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤ ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ። ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ” መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው። ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል። የእስራኤል ብርሃን እሳት፣ ቅዱሱም ነበልባል ይሆናል፤ በአንድ ቀንም እሾኹንና ኵርንችቱን እሳት ይበላዋል፤ ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣ የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣ ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል። በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ ሕፃን ልጅ እንኳ ቈጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል። የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!
አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣ በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ። ምድርና ሕዝቦቿ ሁሉ በሚናወጡበት ጊዜ፣ ምሰሶዎቿን አጽንቼ የምይዝ እኔ ነኝ። ሴላ
“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
በአገር ውስጥ ድኻ ተጨቍኖ፣ ፍትሕ ተጓድሎ፣ መብትም ተረግጦ ብታይ፣ እንደነዚህ ባሉ ነገሮች አትደነቅ፤ ምክንያቱም አንዱን አለቃ የበላዩ ይመለከተዋል፤ በእነዚህ በሁለቱም ላይ ሌሎች ከፍ ያሉ አሉ። ከምድሩ የሚገኘው ትርፍ ለሁሉም ነው፤ ንጉሡም ራሱ የሚጠቀመው ከዕርሻ ነው።
ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም በሩቁ ቆሟል፤ እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሏል፤ ቅንነትም መግባት አልቻለም። እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ።
ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? ለምንስ ወንድምህን ትንቃለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቀርባለንና፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ ‘እኔ ሕያው ነኝና’ ይላል ጌታ፤ ‘ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይመሰክራል።’ ” ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል? አካሄዱ የቀና፣ ጽድቅን የሚያደርግ፤ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
በጽዮን ያዘኑትን እንዳረጋጋ፣ በዐመድ ፈንታ፣ የውበት አክሊል እንድደፋላቸው፣ በልቅሶ ፈንታ፣ የደስታ ዘይት በራሳቸው ላይ እንዳፈስስላቸው፣ በትካዜ መንፈስ ፈንታ፣ የምስጋና መጐናጸፊያ እንድደርብላቸው ልኮኛል፤ እነርሱም የክብሩ መግለጫ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር የተከላቸው፣ የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።
“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ ወዮላችሁ! ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት እየሰጣችሁ በሕጉ ውስጥ ዋነኛ የሆኑትን ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና ታማኝነትን ግን ንቃችኋልና፤ እነዚያን ሳትተዉ እነዚህን ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤
የእኛ ዐመፃ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አጕልቶ የሚያሳይ ከሆነ፣ ምን ማለት እንችላለን? እንደ ሰው ለመከራከር ያህል እግዚአብሔር በእኛ ላይ ቍጣውን በማምጣቱ ዐመፀኛ ነውን? እንደ ሰው ሲታሰብ ማለቴ ነው። ከቶ አይሆንም! እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዴት ሊፈርድ ይችላል?
ዐመፀኞችን በማየት አትሸበር፤ በክፉ አድራጊዎችም አትቅና፤ ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ ስፍራውንም ብታሥሥ አታገኘውም። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ። ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል። እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፣ ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና። ችግረኞችንና ድኾችን ለመጣል፣ አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣ ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ ቀስታቸውንም ገተሩ። ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል። የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል። የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፣ ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል። እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል። በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤ በራብ ዘመንም ይጠግባሉ። እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፤ እንደ ለምለም ቅጠልም ይጠወልጋሉ።
“ ‘ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ‘ክፉ አድራጊውን ሰው አትቃወሙት’፤ ነገር ግን ቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ አዙርለት።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
በደለኛውን፣ “አንተ ንጹሕ ነህ” የሚለውን፣ ሕዝቦች ይረግሙታል፤ መንግሥታትም ያወግዙታል። በደለኛውን፣ “አንተ ጥፋተኛ ነህ” የሚሉት ግን መልካም ነገር ይገጥማቸዋል፤ የተትረፈረፈ በረከትም ይወርድላቸዋል።
ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም፤ ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል፤ እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል።
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ። እግዚአብሔርን የምትወድዱ ክፋትን ጥሉ፤ እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል። ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ። እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ። ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤ መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።
ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል የሚለውን ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
“እንግዲህ እኔ የመረጥሁት ጾም፣ የጭቈናን ሰንሰለት እንድትበጥሱ፣ የቀንበርን ገመድ እንድትፈቱ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንድታወጡ፣ ቀንበርን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን? ምግብህን ለተራበ እንድታካፍለው፣ ተንከራታቹን ድኻ ወደ ቤትህ እንድታስገባው፣ የተራቈተውን ስታይ እንድታለብሰው፣ የሥጋ ዘመድህንም ፊት እንዳትነሣው አይደለምን?
ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው? ከክፉ አድራጊዎችስ ጋራ የሚሟገትልኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣ ነፍሴ ወደ ዝምታው ዓለም ፈጥና በወረደች ነበር።
አንተም፣ “ስለዚህ ነገር ምንም አላውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ሕይወትህን የሚጠብቃት እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን አይከፍለውምን?
መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።