2 ጢሞቴዎስ 1:5 ግብዝነት የሌለበት እምነትህን አስታውሳለሁ፤ ይህ እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ እንዲሁም በእናትህ በኤውንቄ ዘንድ ነበረ፤ አሁን ደግሞ በአንተ እንዳለ ተረድቻለሁ።
1 ጴጥሮስ 5:5 ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
መዝሙር 34:11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
ምሳሌ 3:11-12 ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በዘለፋውም አትመረር፤ አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወድደውን ይገሥጻልና።
ዘፀአት 20:6 ለሚወድዱኝና ትእዛዞቼን ለሚጠብቁ ግን እስከ ሺሕ ትውልድ ፍቅርን የማሳይ ነኝ።
መዝሙር 144:12 ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣ የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።
ምሳሌ 19:14 ቤትና ሀብት ከወላጆች ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።
ምሳሌ 15:1 የለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራል።
ኤፌሶን 5:21 ለክርስቶስ ካላችሁ አክብሮታዊ ፍርሀት የተነሣ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ተገዙ።
1 ዮሐንስ 4:16 ስለዚህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ በፍቅሩም እናምናለን። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል።
1 ቆሮንቶስ 13:1 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።
ምሳሌ 31:25-26 ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤ መጪውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች። በጥበብ ትናገራለች፤ በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።
ምሳሌ 10:12 ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።
ዘፍጥረት 45:15 የቀሩትንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከርሱ ጋራ መጨዋወት ጀመሩ።
ዕብራውያን 12:14 ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም።
ሮሜ 15:7 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሆን ዘንድ ክርስቶስ እንደ ተቀበላችሁ፣ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።
ዮሐንስ 13:34 “አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
መዝሙር 127:4-5 በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣ በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው። ብፁዕ ነው፤ ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ ሰው፤ ከጠላቶቻቸው ጋራ በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።
ምሳሌ 20:7 ጻድቅ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት ይመራል፤ ከርሱም በኋላ የሚከተሉት ልጆቹ ብፁዓን ናቸው።
ኢሳይያስ 54:13 ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል።
ኤፌሶን 6:1 ልጆች ሆይ፤ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና።
ማቴዎስ 7:12 ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና።
ምሳሌ 27:17 ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።
ኤፌሶን 4:15 ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።
2 ቆሮንቶስ 5:17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል።
ሮሜ 12:12 በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።
1 ጴጥሮስ 3:9 ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።
ገላትያ 6:9 በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።
ኢሳይያስ 49:15 “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!
ገላትያ 5:13 ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል።
መዝሙር 145:4 ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ ብርቱ ሥራህን ያውጃል።
መዝሙር 128:1 ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ በመንገዱም የሚሄዱ፤
ምሳሌ 12:25 ሥጉ ልብ ሰውን በሐዘን ይወጥራል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሠኘዋል።
ምሳሌ 16:24 ደስ የሚያሰኝ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለዐጥንትም ፈውስ ነው።
1 ቆሮንቶስ 13:8 ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።
ምሳሌ 18:24 ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።
ምሳሌ 31:30 ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት።
ሮሜ 8:15 እንደ ገና የፍርሀት ባሪያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ ሳይሆን፣ “አባ፣ አባት” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋልና፤
1 ዮሐንስ 4:21 እርሱም “እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ወንድሙን መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥቶናል።
ሮሜ 15:2 እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን ለማነጽ፣ እርሱንም ለመጥቀም ደስ የሚያሠኘውን ነገር ማድረግ ይገባናል።
1 ቆሮንቶስ 13:4-7 ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም። ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።
1 ጢሞቴዎስ 5:8 አንድ ሰው ዘመዶቹን፣ በተለይም የቅርብ ቤተ ሰቡን የማይረዳ ከሆነ ሃይማኖቱን የካደ፣ ከማያምንም ሰው ይልቅ የባሰ ክፉ ነው።
ምሳሌ 15:17 ፍቅር ባለበት ጐመን መብላት፣ ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል።
መዝሙር 133:1 ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!
ምሳሌ 11:29 ቤተ ሰቡን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ ቂልም ሰው የጠቢብ ባሪያ ይሆናል።
ኤፌሶን 4:2 ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ።
ዘዳግም 6:6-7 ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።
ምሳሌ 31:28 ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤ ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤
ማቴዎስ 19:6 ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”
ሮሜ 13:10 ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው።
ኤፌሶን 5:33 ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባሏን ታክብር።
ሮሜ 12:10 እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።
1 ጴጥሮስ 4:8 ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
ኤፌሶን 5:25 ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ራሱንም ስለ እርሷ አሳልፎ እንደ ሰጠ፣ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤
ኤፌሶን 6:4 አባቶች ሆይ፤ እናንተም ልጆቻችሁን አታስቈጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና ተግሣጽ አሳድጓቸው።
ምሳሌ 22:6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤ በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
ቈላስይስ 3:13 እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።
ምሳሌ 17:17 ወዳጅ ምን ጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።
1 ዮሐንስ 4:7 ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል።
መዝሙር 127:3 እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
ቈላስይስ 3:20 ልጆች ሆይ፤ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።
ዘፍጥረት 2:24 ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
1 ተሰሎንቄ 3:12 እኛ ለእናንተ ፍቅር እንዳለን ሁሉ እርስ በርስ ያላችሁን ፍቅርና ለሌሎችም ያላችሁን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ፤ ያትረፍርፍላችሁም።
1 ቆሮንቶስ 11:3 ነገር ግን ይህን እንድታውቁ እወድዳለሁ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ ነው፤ የሴትም ራስ ወንድ ነው፤ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር ነው።
1 ዮሐንስ 4:12 እግዚአብሔርን ያየ ከቶ ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ ግን እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።
ሮሜ 8:39 ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
ሉቃስ 6:31 ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።
1 ቆሮንቶስ 13:13 እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።
ምሳሌ 12:4 መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።
ዘፍጥረት 33:4 ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ ዐቀፈው፤ በዐንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ።
ማቴዎስ 22:39 ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤
መዝሙር 128:3 ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው።
ሮሜ 12:15 ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ።
ዘዳግም 4:9 ዐይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱ፣ ደግሞም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ብቻ ተጠንቀቁ፣ ነቅታችሁም ራሳችሁን ጠብቁ። እነዚህን ለልጆቻችሁና ከእነርሱ በኋላ ለሚወለዱት ልጆቻቸው አስተምሯቸው።
ማቴዎስ 15:4 እግዚአብሔር፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል’ ብሎ ሲያዝዝ፣
ገላትያ 6:2 አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።
1 ዮሐንስ 3:18 ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።
ምሳሌ 23:24 የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ ጠቢብ ልጅ ያለውም በርሱ ሐሤት ያደርጋል።
ዘፀአት 20:12 አባትህንና እናትህን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም።
ኤፌሶን 5:28 ባሎችም እንደዚሁ ሚስቶቻቸውን እንደ ገዛ ሥጋቸው መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድድ ራሱን ይወድዳል።
ምሳሌ 31:10 ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቍ እጅግ ትበልጣለች።
1 ጴጥሮስ 3:7 ባሎች ሆይ፤ እናንተም ደግሞ ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ በኑሯችሁ ሁሉ ለሚስቶቻችሁ ዐስቡላቸው፤ ደካሞች ስለ ሆኑና የሕይወትንም በረከት ዐብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።
መዝሙር 103:17 የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤
ምሳሌ 14:26 እግዚአብሔርን የሚፈራ ጽኑ ዐምባ አለው፤ ልጆቹም መጠጊያ ይኖራቸዋል።
ኤፌሶን 4:32 እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።
ቈላስይስ 3:14 በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት።
ቈላስይስ 3:12 እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤