ልቤ ሆይ፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ፣ ልመናችንን ወደርሱ ማሳረፍ፣ በፊቱ መዋረድና መስገድ እንዴት ያለ ታላቅ ፀጋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ብዙ ምሳሌዎችን ይነግረናል። አንዱ እኔን የሚያስደንቀኝ የያቤጽ ጸሎት ነው፤ በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 4:9-10 ላይ የሚገኘው።
ያቤጽ "እባክህ ባርከኝ፤ ግዛቴንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ ክፉም እንዳያገኘኝ ከክፉ ጠብቀኝ" ብሎ ለመነ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
በጸሎት መጽናት እጅግ አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሕይወትን የመለወጥ፣ የመቀየር ኃይል አለው። በእኛ ላይ የተነገረውን የክፉ ቃል እንኳን በኢየሱስ ስም ሊሽረው ይችላል።
ብዙዎች ውድቀታችን ቢመኙም፣ ኢየሱስን ከክፉ እንዲጠብቀንና በሁሉም ሁኔታዎች ድል እንዲሰጠን ብንለምን፣ በእርሱ ብናምን፣ በጸሎት ብንጸና፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሕይወታችን ለማየት በየቀኑ ብንጥርና ተስፋ ባንቆርጥ እርሱ ያደርግልናል።
ለእግዚአብሔር የማይቻል ነገር የለም። ሁሉን ቻይ ነው፤ እኛ የማንችለውን እርሱ ማድረግ ይችላል። የጻድቅ ጸሎት ብርቱ ኃይል አለው፤ ለሚያምንም ሁሉ ይቻላል።
አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።
“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወድዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።
በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።
ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።
በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ቀርባችሁ ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁም ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤
በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውንም ነገር እንደ ፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል። የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ የለመንነውንም ነገር እንደ ተቀበልን እናውቃለን።
“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል። ልባችንንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስን ሐሳብ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና።
የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት። “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣ እምነቴን ጠብቄአለሁ። ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ። ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው? የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ። በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ። የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤ እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤ ከእስራቴም ፈታኸኝ። ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ። በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ። ሃሌ ሉያ። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”
በጸሎቴ እያስታወስኋችሁ ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረብን አላቋረጥሁም። የክብር አባት የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ይበልጥ እንድታውቁት፣ የጥበብና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ ያለ ማቋረጥ እለምናለሁ።
ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ ያህል ርቆ ተንበርክኮ ጸለየ፤ እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፤ ፈቃድህ ከሆነ፣ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም።”
እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ። ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር። ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤ ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች። ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት። ይሁን እንጂ ሴት በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም ራሷን እየገዛች ብትጸና ልጅ በመውለድ ትድናለች። ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይኸውም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው።
ከዚህ የተነሣ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም፤