መዝሙር 5:3 እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ።
መዝሙር 119:147 ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድድ ተነሥቼ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ።
መዝሙር 63:1 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች።
መዝሙር 88:13 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።
መዝሙር 130:6 ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።
ኢሳይያስ 26:9 ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።
መዝሙር 143:6 እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። ሴላ
መዝሙር 55:17 በማታ፣ በጧትና በቀትር፣ እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤ እርሱም ድምፄን ይሰማል።
መዝሙር 4:1 የጽድቄ አምላክ ሆይ፤ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።
መዝሙር 90:14 በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።
ማቴዎስ 6:6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።
መዝሙር 42:1-2 ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች። ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣ በነገር ጠዘጠዙኝ፣ ዐጥንቴም ደቀቀ። ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና። ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤ መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?
ሰቈቃወ 3:22-23 ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው።
ዕብራውያን 4:16 እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
መዝሙር 25:5 አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣ በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
ምሳሌ 8:17 የሚወድዱኝን እወድዳቸዋለሁ፤ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።
መዝሙር 119:145-146 እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ እጮኻለሁና መልስልኝ፤ ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ። ወደ አንተ እጣራለሁና አድነኝ፤ ምስክርነትህንም እጠብቃለሁ።
መዝሙር 119:119 የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
ፊልጵስዩስ 4:6-7 በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
መዝሙር 91:15 ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
መዝሙር 37:7 በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።
መዝሙር 63:5-6 ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል። በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።
ኢሳይያስ 50:4 ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።
መዝሙር 4:8 በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።
ገላትያ 6:9 በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።
መዝሙር 112:1 ሃሌ ሉያ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ፤
መዝሙር 56:9 ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።
መዝሙር 119:9 ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።
መዝሙር 94:19 የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
መዝሙር 36:5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል።
መዝሙር 86:5 ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።
መዝሙር 31:14-15 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፤ “አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁም። ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው፤ ከጠላቶቼ እጅ ታደገኝ፤ ከሚያሳድዱኝም አድነኝ።
ኢሳይያስ 58:9 የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም፣ ‘አለሁልህ’ ይልሃል። “የጭቈና ቀንበር፣ የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ፣
ማቴዎስ 7:7 “ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል።
መዝሙር 38:15 እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ።
ምሳሌ 15:8 እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሠኘዋል።
ሮሜ 12:12 በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።
መዝሙር 118:24 እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ በርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።
መዝሙር 73:28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ።
ኢሳይያስ 41:10 እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
መዝሙር 27:8 “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ ልቤ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።
መዝሙር 34:1 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።
1 ጴጥሮስ 5:7 እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በርሱ ላይ ጣሉት።
መዝሙር 9:10 ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
መዝሙር 139:1-2 እግዚአብሔር ሆይ፤ መረመርኸኝ፤ ደግሞም ዐወቅኸኝ። በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች፤ ቀኝ እጅህም አጥብቃ ትይዘኛለች። እኔም፣ “ጨለማው በርግጥ ይሰውረኛል፤ በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል” ብል፣ ጨለማ የአንተን ዐይን አይዝም፤ ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል፤ ጨለማም ብርሃንም ለአንተ አንድ ናቸውና። አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤ በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች። እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፤ በምድር ጥልቀት ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ፣ ዐይኖችህ ገና ያልተበጀውን አካሌን አዩ፤ ለእኔ የተወሰኑልኝም ዘመናት፣ ገና አንዳቸው ወደ መኖር ሳይመጡ፣ በመጽሐፍ ተመዘገቡ። አምላክ ሆይ፤ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ክቡር ነው! ቍጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው! ልቍጠራቸው ብል፣ ከአሸዋ ይልቅ ይበዙ ነበር። ተኛሁም ነቃሁም፣ ገና ከአንተው ጋራ ነኝ። አምላክ ሆይ፤ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት! ደም የተጠማችሁ ሰዎች ሆይ፤ ከእኔ ራቁ! አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።
ፊልጵስዩስ 4:8 በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።
መዝሙር 139:5 አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ፤ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
መዝሙር 130:5-6 እግዚአብሔርን ደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤ በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ። ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።
መዝሙር 56:3-4 ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ። ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
መዝሙር 119:169 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴ ከፊትህ ይድረስ፤ እንደ ቃልህም ማስተዋልን ስጠኝ።
መዝሙር 111:10 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።
ኢሳይያስ 26:3-4 በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና።
መዝሙር 63:6-7 በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ። አንተ ረዳቴ ነህና፣ በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።
መዝሙር 5:12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤ በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።
መዝሙር 54:2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ።
መዝሙር 86:7 አንተ ስለምትመልስልኝ፣ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።
መዝሙር 42:8 እግዚአብሔር ምሕረቱን በቀን ያዝዛል፤ ዝማሬውም በሌሊት በእኔ ዘንድ አለ፤ ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው።
መዝሙር 84:2 ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ።
መዝሙር 37:5 መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤
ማቴዎስ 5:6 ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና።
መዝሙር 5:2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ ድረስልኝ ብዬ ስጮኽ ስማኝ።
ኢሳይያስ 40:31 እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
መዝሙር 145:8 እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ፣ ለቍጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው።
መዝሙር 130:5 እግዚአብሔርን ደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤ በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ።
መዝሙር 139:23-24 እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤ በዘላለምም መንገድ ምራኝ።
መዝሙር 40:1 እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።
ሮሜ 8:26 እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል።
መዝሙር 5:1-2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ቸል አትበል። አምላክ ሆይ፤ የእጃቸውን ስጣቸው! ተንኰላቸው መውደቂያቸው ይሁን፤ ከኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፣ በአንተ ላይ ዐምፀዋልና። አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤ በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ። ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ ድረስልኝ ብዬ ስጮኽ ስማኝ።
መዝሙር 119:2 ብፁዓን ናቸው እግዚአብሔር ሕግ፤ ምስክርነቱን የሚጠብቁ፣ በፍጹምም ልብ የሚሹት፤
ምሳሌ 15:29 እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።
መዝሙር 143:8 በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
መዝሙር 4:4 ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤ በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ
መዝሙር 119:145 እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ እጮኻለሁና መልስልኝ፤ ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ።
ኢሳይያስ 54:10 ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።
መዝሙር 118:5 በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።
ማቴዎስ 11:28-30 “እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ “ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀ። ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።”
መዝሙር 36:7-9 አምላክ ሆይ፤ ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰዎች ልጆች ሁሉ፣ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ። ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፣ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
መዝሙር 91:1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።
መዝሙር 30:5 ቍጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል።
ኢሳይያስ 12:2 እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።”
ምሳሌ 3:6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።
መዝሙር 66:20 ጸሎቴን ያልናቀ፣ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፣ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው።
ኢሳይያስ 30:18 እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት ብፁዓን ናቸው!
መዝሙር 27:14 እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ አይዞህ፣ በርታ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
መዝሙር 22:19 አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
መዝሙር 68:19 ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ
መዝሙር 146:5 ብፁዕ ነው፤ ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው፤
መዝሙር 113:7 ድኻውን ከዐፈር ያነሣል፤ ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
መዝሙር 119:43 ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።
ዕብራውያን 10:19-22 እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በኢየሱስ ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ድፍረት አግኝተናል፤ ፍጹም ሊያደርጋቸው ቢችል ኖሮ፣ መሥዋዕት ማቅረቡን ይተዉት አልነበረምን? ደግሞም ለአምልኮ የሚቀርቡት ሰዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለሚነጹ፣ በኅሊናቸው ኀጢአተኝነት ባልተሰማቸውም ነበር። ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው። በእግዚአብሔር ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን፣ ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።
መዝሙር 136:1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
መዝሙር 121:1-2 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል? ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
ኢሳይያስ 26:8 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣ አንተን ተስፋ አድርገናል፤ ስምህና ዝናህ፣ የልባችን ምኞት ነው።
መዝሙር 34:10 አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
ማቴዎስ 5:14 “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤
ሮሜ 8:31 ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?
መዝሙር 42:2 ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤ መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?
መዝሙር 19:14 ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።
መዝሙር 69:13 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት፣ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አምላክ ሆይ፤ በታላቅ ምሕረትህ፣ በማዳንህም ርግጠኛነት መልስልኝ።
መዝሙር 77:1-2 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ። እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ ይህ ድካሜ ነው” አልሁ። የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤ የጥንት ታምራትህን በርግጥ አስታውሳለሁ፤ ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ። አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? ታምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ በሕዝቦችም መካከል ኀይልህን ትገልጣለህ። የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፣ ሕዝብህን በክንድህ ተቤዠሃቸው። ሴላ አምላክ ሆይ፤ ውሆች አዩህ፤ ውሆች አንተን አይተው ተሸማቀቁ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ። ደመናት ውሃን አንጠባጠቡ፤ ሰማያት አንጐደጐዱ፤ ፍላጾችህም ዙሪያውን አብለጨለጩ። የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ተሰማ፤ መብረቅህ ዓለምን አበራው፤ ምድርም ራደች፤ ተንቀጠቀጠች። መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤ መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም። በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴም አልጽናና አለች።
መዝሙር 36:5-6 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል። ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ።
ፊልጵስዩስ 4:19 አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል።
ምሳሌ 16:3 የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል።
ሮሜ 10:12 በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤
ምሳሌ 12:25 ሥጉ ልብ ሰውን በሐዘን ይወጥራል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሠኘዋል።
መዝሙር 5:11 አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው።