Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


119 የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሎት ለሌሎች

119 የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሎት ለሌሎች

በዙሪያህ ላሉት ሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት ማቅረብ ፍቅርን ለማሳየት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። ከራስህ ችሎታ በሚወጡ ሺህ ቃላት ይልቅ ልመናህ ዋጋ አለው።

ለሌሎች ስትጸልይ፣ እነሱ የሚያጋጥሟቸውን መከራዎች ታውቃለህ፣ ህመማቸውንና ሸክማቸውን ትጋራለህ፣ መንፈስህም ለእነሱ በእግዚአብሔር ፊት እስከማልቀስ ድረስ ይነካል። ከጸሎት በኋላ የሚሰማህ እርካታ እጅግ ውብ ነው።

ለሌሎች ስትጸልይ፣ ለራስህም ጭምር እየጸለይክ ነው፤ ይህም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ነገር ነው፤ ምክንያቱም ትኩረትህ በራስህ ላይ ሳይሆን በሌሎች ደህንነት ላይ ስለሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ በኤፌሶን 6:18 ላይ ሁልጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ እንድንጸልይ ያስተምረናል።

ጸሎትን ማዳበር ለሌሎች ደህንነት ዘወትር ለመለመን ቁልፍ ነው። ለሌሎች ካልተማለድክ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን መልካም ማድረግን ችላ እያልክ ነው። የምታስብለት ሰው ካለ፣ ህይወቱን በእግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ከሁሉ የተሻለው ነገር ነው።

ዛሬውኑ አማላጅ ለመሆን ወስን፣ ጩኸትህ ሰማይን ለአንተ ሊያንቀሳቅስ እንደሚችል እመን። ህይወትን ማዳን፣ ትዳርን መጠገን፣ በቤተሰቦች መካከል እርቅ ማምጣት፣ ይቅርታ ማግኘት እና የጠፉትን ማግኘት የምትችለው የኢየሱስን ምህረት በመለመን ብቻ ነው።

ስለዚህ፥ እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፥ ትፈወሱም ዘንድ እርስ በርሳችሁ ጸልዩ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ብርቱ እና ውጤታማ ናት (ያዕቆብ 5:16)።


መዝሙር 10:12

እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤ ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:7

ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:20

ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:6

አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:15

የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ የለመንነውንም ነገር እንደ ተቀበልን እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:6

ዳሩ ግን ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ ምክንያቱም የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚናወጥ የባሕር ማዕበል ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:13

አብ በወልድ እንዲከብር፣ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:14

እነዚህ ሁሉ ከሴቶቹና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ጋራ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋራ በአንድ ልብ ሆነው ያለ ማቋረጥ ተግተው ይጸልዩ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 1:19

በእኔ ላይ የደረሰው ነገር፣ በጸሎታችሁ አማካይነትና ከኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በተሰጠ ረድኤት ለመዳኔ እንደሚሆን ዐውቃለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕዝራ 8:23

ስለዚህ ጾምን፤ ወደ አምላካችንም ስለዚህ ነገር ልመና አቀረብን፤ እርሱም ጸሎታችንን ሰማ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:44

እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 11:25

እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። [

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 12:5

ጴጥሮስም በዚህ መሠረት እስር ቤት ተጣለ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ስለ እርሱ አጥብቃ ወደ እግዚአብሔር ትጸልይ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 33:3

‘ወደ እኔ ጩኽ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና የማይመረመር ነገር እገልጥልሃለሁ።’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:12

በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 29:12

እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ቀርባችሁ ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 13:34

“አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:16-18

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:6-7

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 4:2

ከማመስገን ጋራ ነቅታችሁ በትጋት ጸልዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 2:1-2

እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ። ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር። ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤ ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች። ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት። ይሁን እንጂ ሴት በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም ራሷን እየገዛች ብትጸና ልጅ በመውለድ ትድናለች። ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይኸውም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 15:30

ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የተጋድሎዬ አጋር እንድትሆኑ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:9

ከዚህ የተነሣ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:25

ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 1:3-5

እናንተን ባስታወስሁ ቍጥር አምላኬን አመሰግናለሁ። ቀድሞ እንዳያችሁትና አሁንም በእኔ እንዳለ በምትሰሙት በዚያው ዐይነት ተጋድሎ እናንተም እያለፋችሁ ነውና። ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁ ስጸልይ፣ በደስታ እጸልያለሁ፤ ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስካሁን ድረስ በወንጌል አገልግሎት ተካፋይ ሆናችኋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:2

አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 122:6

እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤ “የሚወድዱሽ ይለምልሙ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 55:17

በማታ፣ በጧትና በቀትር፣ እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤ እርሱም ድምፄን ይሰማል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:16

ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይጸልይ፤ እግዚአብሔርም ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ላደረጉት ሕይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃም ኀጢአት አለ፤ ስለዚህኛው ግን ይጸልይ አልልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:8

ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:17

ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:29

እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 102:17

እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:19-20

“ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፤ በምድር ላይ ሁለት ሆናችሁ ስለ ምንም ነገር በመስማማት ብትጠይቁ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላችኋል፤ ኢየሱስ አንድ ሕፃን ወደ ራሱ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመና እንዲህ አላቸው፤ ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 4:2-4

ከማመስገን ጋራ ነቅታችሁ በትጋት ጸልዩ። እኔ እስረኛ የሆንሁለትን የክርስቶስን ምስጢር ማወጅ እንድንችል፣ እግዚአብሔር የቃሉን በር እንዲከፍትልን ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ደግሞም መናገር እንደሚገባኝ ቃሉን በግልጽ እንድናገር ጸልዩልኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:3

በእስር ላይ ያሉትን ከእነርሱ ጋራ እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ አስቧቸው፤ እንዲሁም በሰው እጅ የሚንገላቱትን ራሳችሁ መከራ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ አስቧቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 126:5

በእንባ የሚዘሩ፣ በእልልታ ያጭዳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 1:11

እናንተም በጸሎታችሁ ደግፉን፤ በብዙዎች ጸሎት ስለ ተሰጠን ስጦታ ብዙ ሰዎች ስለ እኛ ምስጋና ያቀርባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 12:23

ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት እግዚአብሔርን መበደል ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 141:2

ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤ እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 22:32

እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 17:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ። ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤ በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ። አሳድደው ደረሱብኝ፤ ከበቡኝም፤ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ። እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ አንበሳ፣ በስውርም እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው። እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ። ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ። እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ስነቃም ክብርህን አይቼ እረካለሁ። ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 7:14

በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 9:38

ስለዚህ የመከሩ ጌታ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:20

አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት ማምለጥ የሚቻለውም በጌታ በእግዚአብሔር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:16-18

በጸሎቴ እያስታወስኋችሁ ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረብን አላቋረጥሁም። የክብር አባት የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ይበልጥ እንድታውቁት፣ የጥበብና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ ያለ ማቋረጥ እለምናለሁ። እንዲሁም በርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 86:6-7

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤ የልመናዬን ጩኸት ስማ። አንተ ስለምትመልስልኝ፣ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 1:3

ሳላቋርጥ ሌሊትና ቀን በጸሎቴ ስለ አንተ ሳስብ፣ ቀደምት አባቶች እንዳደረጉት በንጹሕ ኅሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:10-12

አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ። የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤ በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:9

ሁልጊዜ ምን ያህል እንደማስባችሁ፣ የልጁን ወንጌል በመስበክ በሙሉ ልቤ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:147-148

ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድድ ተነሥቼ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ። ቃልህን አሰላስል ዘንድ፣ ዐይኔ ሌሊቱን ሙሉ ሳይከደን ያድራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:5

ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጐድለው፣ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለርሱም ይሰጠዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:1

ደቀ መዛሙርቱ ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ እንደሚገባቸው ለማሳየት ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:10

በሙሉ ልቤ ፈለግሁህ፤ ከትእዛዞችህ ፈቀቅ እንዳልል አድርገኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 12:26

አንድ ብልት ቢሠቃይ፣ ብልቶች ሁሉ ዐብረው ይሠቃያሉ፤ አንድ ብልት ቢከብር፣ ሌሎቹም ብልቶች ዐብረው ደስ ይላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:12

እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 30:8

እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 53:12

ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋራ እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውን ከኀያላን ጋራ ይካፈላል፤ እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ ከክፉ አድራጊዎችም ጋራ በመቈጠሩ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:24-25

እርስ በርሳችንም ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ። አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:176

እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና፣ ባሪያህን ፈልገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 3:10

እንደ ገና ልናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለማሟላት ሌሊትና ቀን እጅግ ተግተን እንጸልያለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 143:1

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን አድምጥ፤ በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ ሰምተህ መልስልኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 4:19

የምወድዳችሁ ልጆቼ ሆይ፤ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ፣ ስለ እናንተ እንደ ገና ምጥ ይዞኛል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:17

ወዳጅ ምን ጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:22

ትእዛዞቹንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሠኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከርሱ እንቀበላለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 8:4-5

በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:41

ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:1

ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እስራኤላውያን የልቤ ምኞት፣ እግዚአብሔርንም የምለምነው እንዲድኑ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 16:25-26

እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 61:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ። ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:14

ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 103:1-2

ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ። እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት። ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣ መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ። አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል። እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ ትቢያ መሆናችንንም ያስባል። ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ ምልክቱም በቦታው አይገኝም። የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤ ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጕት ላይ ይሆናል። እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቷል፤ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:3

ስለ እናንተ በምንጸልይበት ጊዜ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:31-32

ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል? ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከርሱ ጋራ እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:15

ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:15

ለብዙ ሰዎች እየደረሰ ያለው ጸጋ፣ ለእግዚአብሔር ክብር በምስጋና ላይ ምስጋናን እንዲጨምር ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:1

የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሠኘው ይመራዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:7

የልጅነቴን ኀጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣ እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 1:2

በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 88:13

እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:7-8

“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:21

እርሱም “እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ወንድሙን መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥቶናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:38-39

ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣ ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:12

ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 130:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ። ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣ የሚያዳምጡ ይሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:43

ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 10:4-5

ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው። በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:26-27

ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ከክርስቶስ ጋራ አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:4

እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 18:6

በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም በፊቱ ከጆሮው ደረሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:16

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:15

ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 31:22

እኔ በደነገጥሁ ጊዜ፣ “ከዐይንህ ፊት ተወግጃለሁ” አልሁ፤ አንተ ግን ወደ አንተ ስጮኽ፣ የልመናዬን ቃል ሰማህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 116:1-2

የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት። “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣ እምነቴን ጠብቄአለሁ። ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ። ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው? የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ። በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ። የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤ እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤ ከእስራቴም ፈታኸኝ። ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ። በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ። ሃሌ ሉያ። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:28

ነፍሴ በሐዘን ተዝለፈለፈች፤ እንደ ቃልህ አበርታኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:9

ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 6:19-20

የወንጌልን ምስጢር ለመግለጥ አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ በድፍረት እንድናገር ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ጸልዩልኝ። “አባትህንና እናትህን አክብር” በሚለው ቀዳሚ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ፣ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና። ስለዚህ መናገር የሚገባኝን ያለ ፍርሀት እንድናገር ጸልዩልኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 66:20

ጸሎቴን ያልናቀ፣ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፣ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 4:12

ከእናንተ ወገን የሆነው የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተረጋግታችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋደለ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 139:23-24

እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤ በዘላለምም መንገድ ምራኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:10

እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 118:5

በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:14

በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውንም ነገር እንደ ፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:18

ለእኛ ደግሞ ጸልዩልን። በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚናፍቅ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን ርግጠኞች ነን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:10

በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 54:2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 8:3-4

የጣቶችህን ሥራ፣ ሰማያትህን ስመለከት፣ በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣ በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዜና መዋዕል 16:11

እግዚአብሔርንና ብርታቱን ፈልጉ፤ ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 42:10

ኢዮብ ለወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ፣ እግዚአብሔር እንደ ገና አበለጸገው፤ ቀድሞ በነበረው ፈንታ ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 6:18

በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩ፤ ይህንም በማሰብ ንቁ፤ ስለ ቅዱሳንም ሁሉ በትጋት ልመና አቅርቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 2:1

እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:26-27

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል። ልባችንንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስን ሐሳብ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:16

ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:7

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:6

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:1

የበዓለ ዐምሳ ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድነት፣ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፣ አምላኬ፣ መድኃኒቴ፣ ፈጣሪዬ፣ አንተ በሕይወቴ ውስጥ እጅግ የተከበርክ፣ ቅዱስ እና የምወደው ነህ። ብዙ ምሕረትህ ጠብቆኝ አበርትቶኛል። ጸጋህ ደግፎኛል ለሌሎችም ፍላጎት እንዳስብ አስችሎኛል። ዛሬ በወንድሜ/በእህቴ (...) ሕይወት ስል በጌታችን በኢየሱስ ስም እጸልያለሁ። በፈተናና በመከራ ውስጥ ብርታት ስጠው/ስጪው። አዕምሮ የማይገባው ሰላምህ ዓላማውን/ዓላማዋን እንዲፈጽም/እንድትፈጽም ይሸፍነው/ይሸፍናት። በቤተሰቡ ላይ ፈቃድህን አኑር። እግዚአብሔር ሆይ፣ አክብር። እምነቱ/እምነቷ እንዲጸና እና በሥራህ እንዳይታክት/እንዳትታክት በእርሱ/በእርሷ ላይ ድንቅ ሥራ አድርግ። በውስጡ/በውስጧ ቀና መንፈስ አድስ። በቅብዓት ሙላው/ሙላት። የእጆቹን/የእጆቿን ሥራ ባርክ። በሁሉም ነገር እንዲበለጽግ/እንድትበለጽግ የሰማያትን በር ክፈትለት/ክፈትላት። እግዚአብሔር ሆይ፣ በክፉ ቀን በማደሪያህ ጥላ ስር ደብቀው/ደብቂያት። በእርሱ/በእርሷ ላይ አካላዊና መንፈሳዊ ፈውስን እናውጃለሁ። በሕይወቱ/በሕይወቷ ውስጥ በእያንዳንዱ ዘርፍ ነፃነትን እናውጃለሁ። ጠላት ነፍሱን/ነፍሷን፣ ንብረቱን/ንብረቷን ወይም ልቡን/ልቧን እንደማይነካው እናውጃለሁ። አንተ እግዚአብሔር በዙሪያው/በዙሪያዋ ጋሻ ነህና። አንተ ክብሩ/ክብሯ እና ራሱን/ራሷን የሚያነሳ/የምታነሳ ነህ። የተወደድክ አባት ሆይ፣ ጎተራዎቹ/ጎተራዎቿ በብዛት እንደሚሞሉ እና የወይን መጭመቂያዎቹ/የወይን መጭመቂያዎቿ በወይን ጠጅ እንደሚሞሉ እናውጃለሁ። ቃልህ «በምንለምነው ሁሉ እንዲሰማን የምናውቅ ከሆነ፥ ከእርሱ የለመንነውን እንዳገኘን እናውቃለን» ስላለ፥ በኢየሱስ ስም እጸልያለሁ። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች