ዘዳግም 20:4ድልን ያቀዳጃችሁ ዘንድ ስለ እናንተ ጠላቶቻችሁን ሊወጋ ዐብሯችሁ የሚወጣው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።”
መዝሙር 118:6እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
መዝሙር 91:5-6የሌሊትን አስደንጋጭነት፣ በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣ በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።
ዕብራውያን 13:6ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።
መዝሙር 125:2ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት፣ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።
ሮሜ 8:28እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።
መዝሙር 3:3እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ።
መዝሙር 57:1ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረኝ፤ ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና፤ በክንፎችህ ሥር እጠለላለሁ።
ዘዳግም 33:27ዘላለማዊ አምላክ መኖሪያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤ ‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
ኢሳይያስ 12:2እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።”
መዝሙር 9:9እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።
ኢሳይያስ 26:3በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
መዝሙር 46:10“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
መዝሙር 4:8በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።
2 ሳሙኤል 22:31“የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።
ኢሳይያስ 41:13እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።
መዝሙር 140:4እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፤ እግሮቼንም ለመጥለፍ ከሚያደቡ ዐመፀኞች ሰውረኝ።
ዮሐንስ 14:27ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።
ምሳሌ 3:25-26ድንገተኛን መከራ፣ በክፉዎች ላይ የሚደርሰውንም ጥፋት አትፍራ፤እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፤ እግርህንም በወጥመድ ከመያዝ ይጠብቃል።
መዝሙር 91:4በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።
መዝሙር 34:7እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ ያድናቸዋልም።
ኢሳይያስ 54:17በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
ምሳሌ 18:10የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።
መዝሙር 91:11በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይሰናከል፤
መዝሙር 46:1አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው።
ዘዳግም 31:6ብርቱና ደፋር ሁኑ፤ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡላቸው። አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሄዳልና፤ አይተውህም፤ አይጥልህምም።”
መዝሙር 23:4በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።
ኢሳይያስ 41:10እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
መዝሙር 91:1-2በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይሰናከል፤በእጆቻቸው ያነሡህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል።በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።“ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ።ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።
2 ጢሞቴዎስ 4:18ጌታ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ወደ ሰማያዊው መንግሥቱም በሰላም ያደርሰኛል፤ ለርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
ኢያሱ 1:9በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”
መዝሙር 121:7-8እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ነፍስህንም ይንከባከባታል።እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።
1 ጴጥሮስ 5:7እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በርሱ ላይ ጣሉት።
መዝሙር 32:7አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ በድል ዝማሬም ትከብበኛለህ። ሴላ
ሮሜ 8:31ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?
ዘፀአት 14:14እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ያለባችሁ መታገሥ ብቻ ነው።”
ናሆም 1:7እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በጭንቅ ጊዜም መሸሸጊያ ነው። ለሚታመኑበት ይጠነቀቅላቸዋል፤
መዝሙር 121:5እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።
መዝሙር 27:1እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ?
ኢሳይያስ 43:2በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
መዝሙር 112:7ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
ኢሳይያስ 45:2‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችን እደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።
መዝሙር 46:7የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ
ኤርምያስ 1:8እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር።
ዘዳግም 31:8እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋራ ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አይተውህምም፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቍረጥ።”
1 ሳሙኤል 2:9እርሱ የታማኝ አገልጋዮቹን እግር ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ። “ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤
ምሳሌ 12:21ጻድቃን ጕዳት አያገኛቸውም፤ ክፉዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው።
መዝሙር 138:7በመከራ መካከል ብሄድም፣ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ።
ኢሳይያስ 49:25እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “ከተዋጊዎች ላይ ምርኮኞች በርግጥ ይወሰዳሉ፤ ከጨካኞችም ላይ ምርኮ ይበዘበዛል፤ ከአንቺ ጋራ የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፤ ልጆችሽንም እታደጋለሁ።
ኢሳይያስ 57:15ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።
መዝሙር 125:1በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
ማቴዎስ 10:28ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ።
2 ቆሮንቶስ 1:10እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በርሱ ላይ ጥለናል።
ዘፀአት 33:14እግዚአብሔር “ሀልዎቴ ከአንተ ጋራ ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” ብሎ መለሰ።
መዝሙር 27:3ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤ ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ።
ዘካርያስ 2:5እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፣ ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’
ሮሜ 16:20የሰላም አምላክ፣ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።
ኢሳይያስ 43:5ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
2 ሳሙኤል 22:3አምላኬ፣ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፤ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ ከዐመፀኛ ሰዎችም ታድነኛለህ።
ዮሐንስ 10:28እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም።
መዝሙር 46:5እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤ አምላክ በማለዳ ይረዳታል።
መዝሙር 5:12እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤ በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።
ኢሳይያስ 30:15የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤ እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም፤
መዝሙር 145:18-19እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።
ምሳሌ 10:29የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣ ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው።
ኢሳይያስ 46:4እስከ ሽምግልናችሁ፣ እስከ ሽበትም፣ የምሸከማችሁ እኔ ነኝ፤ እኔው ነኝ። ሠርቻችኋለሁ፤ እሸከማችኋለሁ፤ እደግፋችኋለሁ፤ አድናችኋለሁ።
ኤርምያስ 29:11ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጣችሁ፣ የሰላም ሐሳብ እንጂ ለክፉ አይደለም።
መዝሙር 121:1-2ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
ዮሐንስ 16:33“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
ኢሳይያስ 50:10ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።
መዝሙር 56:3-4ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
ምሳሌ 29:25ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።
ኢሳይያስ 33:2እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረን፤ አንተን ተስፋ አድርገናል። በየማለዳው ብርታት፣ በጭንቅ ጊዜም ድነት ሁነን።
መዝሙር 37:39የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው።
2 ቆሮንቶስ 4:8-9ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም።
መዝሙር 34:4እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።
መዝሙር 55:22የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤ እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም።
ሮሜ 8:37ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
መዝሙር 20:7እነዚህ በሠረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤ እኛ ግን ትምክሕታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።
መዝሙር 91:15ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
ኢሳይያስ 60:1“ብርሃንሽ መጥቷልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል።
1 ቆሮንቶስ 10:13በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።
መዝሙር 41:2እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤ በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ ለጠላቶቹም ምኞት አሳልፎ አይሰጠውም።
መዝሙር 18:2እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።
2 ዜና መዋዕል 20:17ይህን ጦርነት የምትዋጉት እናንተ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁንም ማዳን እዩ። አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገውኑ ውጡና ግጠሟቸው፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋራ ይሆናል።’ ”
መዝሙር 37:23-24የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤ በመንገዱ ደስ ይለዋል።ቢሰናከልም አይወድቅም፣ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።
ኢሳይያስ 59:19በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤ በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣ እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና።
መዝሙር 27:5በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤ በተቀደሰ ድንኳኑም ውስጥ ይሸሽገኛል፤ በዐለቱ ላይ ከፍ ያደርገኛል።
ዘፀአት 15:2“እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
መዝሙር 91:7በአጠገብህ ሺሕ፣ በቀኝህም ዐሥር ሺሕ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።