Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


ንዑስ ምድብ

አስማትና የመናፍስት ሽንገላየአፍሪካ መንፈሳዊ እምነትኮከብ ቆጠራ እና ትንቢትከተከለከሉ ድርጊቶች መራቀቅእግዚአብሔር ጣዖታትን አለመቀበሉየእግዚአብሔር ኃያልነት እና የጥንቆላ ተሰራሪነትየአስማትና የድግምት አደጋዎችየመናፍስትና የጠንቋዮች ውሸትየመናፍስት ጥሪጣዖታትንና መሠዊያዎችን ማጥፋትሐሰተኛ ነቢያትና የማታለል ሽንገላቸውክፉ መንፈስን መቋቋምጥቁር አስማትን መቃወምከጣዖት መራቅ የሚያስገኘው ጥቅምየአስማትና የጥንቆላ ከንቱነትበእግዚአብሔር መታመን፥ በጣዖት አይደለምክፉ ድርጊቶችን መከልከልየሟጠኞችና የኮከብ ቆጠራ ሽንገላየጣዖት ፍርድየእግዚአብሔር ቃል እና አስማትየተሳሳቱ እምነቶች እና አጉል ልማዶችለጣዖታት መስዋዕትነትአጉል እምነቶችየሐሰት አማልክትንና ምስሎቻቸውን አለመቀበልጥንቆላ ድርጊቶችከመንፈሳዊ እስራት መውጣትየመናፍስት ሸፍጥሐሰተኛ አማልክትን ማጋለጥየአባት አምልኮ ውሸትነትክፉ መናፍስትን ለመከላከል የሚያገለግሉ ክታቦች አስማታዊ ኃይል የላቸውምክፉ መንፈስ አምልኮን ማቆምሟርት ተረትና ክህደትየሳንቴሪያ ልማዶች

89 የእግዚአብሔር ፍርድ በእነዚያ ላይ፡ ስለ ባዕድ አምልኮ

89 የእግዚአብሔር ፍርድ በእነዚያ ላይ፡ ስለ ባዕድ አምልኮ
ኢሳይያስ 65:3

በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣ በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 47:11

ጥፋት ይመጣብሻል፤ ነገር ግን በአስማትሽ እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ወጆ ከፍለሽ ለማስወገድ የማትችዪው፣ ጕዳት ይወድቅብሻል፤ ያላሰብሽው አደጋ፣ ድንገት ይደርስብሻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:1

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ቤት የት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 3:5

“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 26:30

የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 4:24

አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት፣ ቀናተኛም አምላክ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 31:1

ከዚያም ሙሴ ወጥቶ እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል ሁሉ ተናገረ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 51:17-18

“እያንዳንዳቸው ጅሎችና ዕውቀት የለሽ ናቸው፤ የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም። እነርሱ ከንቱ የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፣ ፍርድ ሲመጣባቸው ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:26

“ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ። “ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 13:1-3

ነቢይ ወይም ሕልም ዐላሚ ከመካከልህ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፣ የባርነት ምድር ከሆነው ከግብጽ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ፈልጓልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም ማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አያደርግም። አምላክህ እግዚአብሔር እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፣ ምናምንቴ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፣ “ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ” በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፣ ጕዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፣ በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማዪቱን ከነሕዝቧና ከነቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስሳት። በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። እግዚአብሔር ከብርቱ ቍጣው ይመለስ ዘንድ ዕርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥርህን ያበዛዋል፤ ይህም የሚሆነው ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞቹን ሁሉ በመጠበቅና መልካም የሆነውን በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በማድረግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስለ ታዘዝህለት ነው። የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፣ “አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው” ቢልህ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁ ነውና፣ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም ዐላሚውን አትስማ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 45:16

የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሁሉ ያፍራሉ፤ ይቀልላሉ፤ በአንድነት ይዋረዳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ናሆም 3:4

ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣ አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤ ይህች የጠንቋዮች እመቤት በዝሙቷ አሕዛብን፣ በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 15:23

ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 115:4-7

የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ ያበጃቸው፣ ብርና ወርቅ ናቸው። አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣ ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው፤ አያሸትቱም፤ እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤ እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤ በጕሮሯቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 7:25

የአማልክታቸውን ምስሎች በእሳት አቃጥል፤ በላያቸው የሚገኘውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ ለራስህ አታድርግ፤ አለዚያ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆነ ያሰናክልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 16:20

ሰዎች ለራሳቸው አማልክትን ያበጃሉን? ያደርጉ ይሆናል፤ እንዲህ ዐይነቶቹ ግን አማልክት አይደሉም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 17:17

እንዲሁም ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። ጥንቈላና መተት አደረጉ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ፤ ለቍጣም አነሣሡት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 23:24

ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሶፎንያስ 1:4

“እጄን በይሁዳ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤ የበኣልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 14:14

እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 21:21

የባቢሎን ንጉሥ በጥንቈላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ ጐዳናዎች መጋጠሚያ ላይ ይቆማል፤ ቀስቶቹን በመወዝወዝ ዕጣ ይጥላል፤ አማልክቱን ያማክራል፤ ጕበትንም ይመረምራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 47:12-13

“በይ እንግዲህ፣ ከልጅነትሽ ጀምሮ የደከምሽባቸውን፣ አስማቶችሽን፣ ብዙ መተቶችን ቀጥዪባቸው፤ ምናልባት ይሳካልሽ፣ ምናልባትም ጠላቶችሽን ታሸብሪባቸው ይሆናል። የተቀበልሽው ምክር ሁሉ ድካም ብቻ ሆኖ አስቀርቶሻል! እነዚያ ከወር እስከ ወር ከዋክብትን አንጋጦ በማየት የሚተነብዩ፣ ኮከብ ቈጣሪዎች እስኪ ይምጡ፤ ከሚደርስብሽም ነገር እስኪ ያድኑሽ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 4:19

ወደ ሰማይ ቀና ብለህ ፀሓይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን፣ የሰማይ ሰራዊትንም ሁሉ በምትመለከትበት ጊዜ፣ ወደ እነርሱ እንዳትሳብና እንዳትሰግድላቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ድርሻ አድርጎ የሰጣቸውንም ነገሮች እንዳታመልክ ተጠንቀቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 18:23

የመብራት ብርሃን፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽም ሕዝቦች ሁሉ ስተዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 20:27

“ ‘ከመካከላችሁ ሙታን ጠሪ ወይም መናፍስት ጠሪ የሆነ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ይገደል፤ በድንጋይም ይወገሩ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 5:12

ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አታሟርቱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዜና መዋዕል 10:13

ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:18

“መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 20:6

“ ‘ወደ ሙታን ጠሪዎችና ጠንቋዮች ዘወር በማለት፣ በሚከተላቸውና ከእነርሱም ጋራ በሚያመነዝር ሰው ላይ ጠላት እሆንበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 21:6

የገዛ ወንድ ልጁን በእሳት ሠዋ፤ አስማት፣ መተትና ጥንቈላ አደረገ፤ ሙታን ጠሪዎችንና መናፍስት ሳቢዎችን ጠየቀ። ለቍጣ ያነሣሣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 12:29-31

የምትወርሯቸውንና የምታስለቅቋቸውን አሕዛብ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ ያስወግዳቸዋል፤ ባስወጣችኋቸውና በምድራቸው በተቀመጣችሁ ጊዜ ግን፣ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የአሼራ ምስል ዐምዶቻቸውን በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን ጣዖቶች ቈራርጣችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከእነዚያ ስፍራዎች ላይ አጥፉ። ከፊትህ ከጠፉ በኋላ፣ “እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ” ብለህ በመጠየቅ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። አምላክህን እግዚአብሔርን በእነርሱ መንገድ ፈጽሞ አታምልክ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን ሲያመልኩ እግዚአብሔር የሚጸየፈውን ሁሉንም ዐይነት ነገር ያደርጋሉና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እንኳ ለአማልክታቸው መሥዋዕት አድርገው ያቃጥላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 20:3

“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 18:10-12

በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ ወይም መተተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ጠንቋይ ወይም በድግምት የሚጠነቍል፣ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ። እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነውና። ከእነዚህ አስጸያፊ ልምዶች የተነሣም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 8:19-20

ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ? እኔም፣ ካህኑን ኦርያንንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ታማኝ ምስክሮቼ እንዲሆኑ እጠራቸዋለሁ።” ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 44:25

የሐሰተኞችን ነቢያት ምልክቶች አከሽፋለሁ፤ ሟርተኞችን አነሆልላለሁ፤ የጥበበኞችን ጥበብ እገለባብጣለሁ፤ ዕውቀታቸውንም ከንቱ አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 27:9

ስለዚህ፣ የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም የሚሏችሁን ነቢያታችሁን፣ ሟርተኞቻችሁን፣ ሕልመኞቻችሁን፤ መናፍስት ጠሪዎቻችሁንና መተተኞቻቸሁን አትስሙ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 19:19

ሲጠነቍሉ ከነበሩትም መካከል ብዙዎች መጽሐፋቸውን ሰብስበው በማምጣት በሕዝብ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲሰላ ዐምሳ ሺሕ ብር ያህል ሆኖ ተገኘ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 13:10

“አንተ የጽድቅ ሁሉ ጠላት፣ ተንኰልንና ክፋትን ሁሉ የተሞላህ የዲያብሎስ ልጅ፣ የጌታን ቀና መንገድ ከማጣመም አታርፍምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 22:15

ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወድዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 21:8

ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 96:5

የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:28

ራሳቸውን ከበኣል ፌጎር ጋራ አቈራኙ፤ ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 10:2

ተራፊም አሳሳች ነገር ይናገራል፤ ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ፤ የውሸት ሕልም ይናገራሉ፤ ከንቱ መጽናናት ይሰጣሉ፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ተቅበዘበዙ፤ እረኛ በማጣትም ተጨነቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 13:18-20

እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሕዝብን ነፍስ ለማጥመድ፣ ለአስማታቸው ለእጃቸው አንጓ ሁሉ አሸንክታብ ለሚያሰፉና፣ የተለያየ መጠን ያለውን የራስ መሸፈኛ ለሚያበጁ ሴቶች ወዮላቸው! በውኑ የሕዝቤን ነፍስ እያጠመዳችሁ የራሳችሁን ነፍስ ታድናላችሁን? ዕፍኝ ለማይሞላ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ስትሉ ሐሰትን የሚያደምጥ ሕዝቤን እየዋሻችሁ መሞት የማይገባውን በመግደል፣ መኖር የማይገባውንም በማትረፍ በሕዝቤ መካከል አርክሳችሁኛል። “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት በሚናገሩት በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ ከገዛ ራሳቸው ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ የሕዝብን ነፍስ እንደ ወፍ በምታጠምዱበት አሸንክታብ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ከክንዳችሁ ላይ እቀዳድደዋለሁ፤ እንደ ወፍ የምታጠምዱትንም ሕዝብ ነጻ አወጣዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 47:12-14

“በይ እንግዲህ፣ ከልጅነትሽ ጀምሮ የደከምሽባቸውን፣ አስማቶችሽን፣ ብዙ መተቶችን ቀጥዪባቸው፤ ምናልባት ይሳካልሽ፣ ምናልባትም ጠላቶችሽን ታሸብሪባቸው ይሆናል። የተቀበልሽው ምክር ሁሉ ድካም ብቻ ሆኖ አስቀርቶሻል! እነዚያ ከወር እስከ ወር ከዋክብትን አንጋጦ በማየት የሚተነብዩ፣ ኮከብ ቈጣሪዎች እስኪ ይምጡ፤ ከሚደርስብሽም ነገር እስኪ ያድኑሽ። እነሆ፣ እነርሱ ገለባ ናቸው፤ እሳት ይበላቸዋል፤ ከነበልባሉ ወላፈን የተነሣ፣ ራሳቸውን ማዳን አይችሉም። ሰው የሚሞቀው ፍም አይኖርም፤ ተቀምጠው የሚሞቁትም እሳት የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:13

“ያልኋችሁን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ተጠንቀቁ፤ የሌሎችን አማልክት ስም አትጥሩ፤ ከአፋችሁም አይስሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 32:35

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ ይሠዉ ዘንድ በሄኖም ሸለቆ ለበኣል መስገጃ ኰረብቶችን ሠሩ፤ ነገር ግን ይሁዳን ኀጢአት ለማሠራት እንደዚህ ያለውን አስጸያፊ ተግባር እንዲፈጽሙ እኔ አላዘዝሁም፤ ከቶም አላሰብሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 44:9

ጣዖት የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች፣ የሚሠሩባቸውም ነገሮች ዋጋ ቢስ ናቸው፤ የሚናገሩላቸው ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም ያፍራሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 14:6

“ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ንስሓ ግቡ ከጣዖቶቻችሁ ተመለሱ፤ ጸያፍ ተግባራችሁንም ሁሉ ተዉ!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 97:7

ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ፣ በጣዖታትም የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ፤ እናንተ አማልክት ሁሉ፤ ለርሱ ስገዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 47:9

እነዚህ ሁለት ነገሮች፣ መበለትነትና የወላድ መካንነት፣ አንድ ቀን ድንገት ይመጡብሻል፤ የቱን ያህል አስማት፣ የቱንም ያህል መተት ቢኖርሽ፣ በሙሉ ኀይላቸው ይመጡብሻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 19:3-4

እንዲህም በል፤ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሰሚው ሁሉ ጆሮ የሚዘገንን ክፉ ነገር እነሆ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ፤ እኔን ትተውኝ፣ ይህን ስፍራ የባዕድ አማልክት ቦታ አድርገውታልና። እነርሱም ሆኑ አባቶቻቸው፣ የይሁዳ ነገሥታትም ለማያውቋቸው አማልክት ሠውተዋል፤ ይህንም ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 44:3

ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:29

“ደስ በተሰኛችሁባቸው የአድባር ዛፎች ታፍራላችሁ፤ በመረጣችኋቸውም የአትክልት ቦታዎች ትዋረዳላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 13:23

ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ አታዩም፣ ሟርትም አታሟርቱም፤ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።” ’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 23:30

ይህን አምጥተውብሻል፤ ከአሕዛብ ጋራ በማመንዘር በጣዖቶቻቸው ረክሰሻልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:3

እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲህ ይላታል፤ ዘርሽና ትውልድሽ ከከነዓን ምድር ነው፤ አባትሽ አሞራዊ፣ እናትሽም ኬጢያዊት ነበሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 17:5

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰው የሚታመን፣ በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:28-32

ከዚህም በላይ በሐሳባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ አይጠቅምም በማለታቸው፣ መደረግ የማይገባውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው። በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣ ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ሆነ፣ ስም አጥፊዎች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞችና ትምክሕተኞች ናቸው፤ ክፋትን የሚሠሩበትን መንገድ ያውጠነጥናሉ፤ ለወላጆቻቸው አይታዘዙም። የማያስተውሉ፣ ውል የሚያፈርሱ፣ ርኅራኄ የሌላቸውና ጨካኞች ናቸው። ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል የሚለውን ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 34:15

“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 4:6

ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል። ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 23:13

እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ከርኩሰት ኰረብታ በስተ ደቡብ የነበሩትን የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን የርኩሰት አምላክ ለአስታሮት፣ ለሞዓብ ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለካሞሽ፣ ለአሞን ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለሚልኮም ያሠራቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያዎች ንጉሡ አረከሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 13:18-23

እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሕዝብን ነፍስ ለማጥመድ፣ ለአስማታቸው ለእጃቸው አንጓ ሁሉ አሸንክታብ ለሚያሰፉና፣ የተለያየ መጠን ያለውን የራስ መሸፈኛ ለሚያበጁ ሴቶች ወዮላቸው! በውኑ የሕዝቤን ነፍስ እያጠመዳችሁ የራሳችሁን ነፍስ ታድናላችሁን? ዕፍኝ ለማይሞላ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ስትሉ ሐሰትን የሚያደምጥ ሕዝቤን እየዋሻችሁ መሞት የማይገባውን በመግደል፣ መኖር የማይገባውንም በማትረፍ በሕዝቤ መካከል አርክሳችሁኛል። “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት በሚናገሩት በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ ከገዛ ራሳቸው ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ የሕዝብን ነፍስ እንደ ወፍ በምታጠምዱበት አሸንክታብ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ከክንዳችሁ ላይ እቀዳድደዋለሁ፤ እንደ ወፍ የምታጠምዱትንም ሕዝብ ነጻ አወጣዋለሁ። መሸፈኛችሁን ቀድጄ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ በቍጥጥራችሁ ሥር አይሆኑም፤ በዚያ ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። እኔ ያላሳዘንሁትን ጻድቅ በውሸት ስላሳዘናችሁ፣ ኀጢአተኛም ከክፉ መንገዱ ተመልሶ ሕይወቱን እንዳያድን በኀጢአቱ ስላበረታታችሁት፣ ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ አታዩም፣ ሟርትም አታሟርቱም፤ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።” ’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:1

እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! ለመሆኑ ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በፊት ለፊታችሁ በግልጽ ተሥሎ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 101:3

በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:104

ከመመሪያህ ማስተዋልን አገኘሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:8

በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ወግና በዚህ ዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 6:14-17

ከማያምኑ ሰዎች ጋራ አግባብ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋራ ምን ግንኙነት አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋራ ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋራ ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋራ ምን ኅብረት አለው? የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖታት ጋራ ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ “ከእነርሱ ጋራ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” “ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤ ተለዩም፤ ይላል ጌታ። ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:8

ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፣ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:15

“በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:30

“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:7

እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:30

“ከእኔ ጋራ ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋራ የማይሰበስብ ይበትናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:2

መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:21

የጌታን ጽዋና፣ የአጋንንትን ጽዋ በአንድ ላይ መጠጣት አትችሉም፤ ከጌታ ማእድና ከአጋንንት ማእድ ተካፋይ መሆን አትችሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:15

አላዋቂው ሰው ሁሉን ያምናል፤ አስተዋይ ግን ርምጃውን ያስተውላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:128

መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:5-6

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:17

በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:7

እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ ያድናቸዋልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:30

“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:23

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 97:10

እግዚአብሔርን የምትወድዱ ክፋትን ጥሉ፤ እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:20

ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:14-15

ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:18

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት እንደማያደርግ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚጠብቀው፣ ክፉውም እንደማይነካው እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ንዑስ ምድብ

አስማትና የመናፍስት ሽንገላየአፍሪካ መንፈሳዊ እምነትኮከብ ቆጠራ እና ትንቢትከተከለከሉ ድርጊቶች መራቀቅእግዚአብሔር ጣዖታትን አለመቀበሉየእግዚአብሔር ኃያልነት እና የጥንቆላ ተሰራሪነትየአስማትና የድግምት አደጋዎችየመናፍስትና የጠንቋዮች ውሸትየመናፍስት ጥሪጣዖታትንና መሠዊያዎችን ማጥፋትሐሰተኛ ነቢያትና የማታለል ሽንገላቸውክፉ መንፈስን መቋቋምጥቁር አስማትን መቃወምከጣዖት መራቅ የሚያስገኘው ጥቅምየአስማትና የጥንቆላ ከንቱነትበእግዚአብሔር መታመን፥ በጣዖት አይደለምክፉ ድርጊቶችን መከልከልየሟጠኞችና የኮከብ ቆጠራ ሽንገላየጣዖት ፍርድየእግዚአብሔር ቃል እና አስማትየተሳሳቱ እምነቶች እና አጉል ልማዶችለጣዖታት መስዋዕትነትአጉል እምነቶችየሐሰት አማልክትንና ምስሎቻቸውን አለመቀበልጥንቆላ ድርጊቶችከመንፈሳዊ እስራት መውጣትየመናፍስት ሸፍጥሐሰተኛ አማልክትን ማጋለጥየአባት አምልኮ ውሸትነትክፉ መናፍስትን ለመከላከል የሚያገለግሉ ክታቦች አስማታዊ ኃይል የላቸውምክፉ መንፈስ አምልኮን ማቆምሟርት ተረትና ክህደትየሳንቴሪያ ልማዶች
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች