ትዳር ሕይወት ውስጥ ካሉት ትልልቅ ጉዞዎች አንዱ ነው። ይህንን ጉዞ በደስታና በፍቅር ለመጓዝ እግዚአብሔር ማዕከል መሆን አለበት። እንደ ባለትዳር ንፅህናችንን፣ ሥነ ምግባራችንንና አስተሳሰባችንን በጥበብ እንጠብቅ። በንጽህና፣ በጥበብና በቅንነት እናስብ፣ እንነጋገር፣ እንኑር።
ኤፌሶን 5:22 ላይ እንደተፃፈው ለባሎቻችን አክብሮት ማሳየት ይገባናል። የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር ማዋል በጣም አስፈላጊ ነው። እውነተኛ የሕይወት አጋር ለመሆን፣ የክርስቶስን ባሕርይ ለማንፀባረቅና ትዳራችንን በእርሱ ላይ ለመገንባት የእግዚአብሔርን እርዳታ እንሻ።
በዚህ መልኩ ፈተናዎችን ማሸነፍ፣ ባሎቻችንንም እግዚአብሔርንም ደስ ማሰኘት እንችላለን። ለቤተሰባችንም የበረከት በሮች ይከፈታሉ።
ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ፣ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።
ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ፣ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው አኗኗር ተማርከው ይመለሳሉ፤ ስለዚህ፣ “ሕይወትን የሚወድድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል። ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም፤ ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።” መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባችሁ ብፁዓን ናችሁ፤ “ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።” ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ አክፋፍተው የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ። የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤ እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኀጢአት ሞቷልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤ በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው። ይህም የሚሆነው ንጹሕና ፍጹም አክብሮት የተሞላውን ኑሯችሁን ሲመለከቱ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቍ እጅግ ትበልጣለች። ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም። በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም። የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወድዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች። እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች። ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤ በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች። ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው። ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤ በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም። በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤ በጣቶቿም ዘንጉን ታሾራለች። “ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤ የስእለቴ ልጅ ሆይ፤ ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣ እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች። በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና። ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች። ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው። የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች። ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤ መጪውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች። በጥበብ ትናገራለች፤ በአንደበቷም ቀና ምክር አለ። የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤ የስንፍና እንጀራ አትበላም። ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤ ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤ አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።” ጕልበትህን በሴት አትጨርስ፤ ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል። ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት። የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።
ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ፣ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና። እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ፣ ሚስቶችም ለባሎቻቸው በማንኛውም ነገር እንደዚሁ መገዛት ይገባቸዋል።
አንዲት ያገባች ሴት ከባሏ ጋራ በሕግ የታሰረች የምትሆነው እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ነው፤ ባሏ ቢሞት ግን ከጋብቻ ሕግ ነጻ ትሆናለች። ላደርገው የማልፈልገውን ነገር የማደርገው ከሆነ፣ ያን የማደርገው እኔ ራሴ ሳልሆን፣ የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኀጢአት ነው። ስለዚህ ይህ ሕግ እየሠራ እንደ ሆነ ተረድቻለሁ፤ ይኸውም በጎ ነገር ለመሥራት ስፈልግ፣ ክፋት ከእኔ ጋራ አለ። በውስጤ በእግዚአብሔር ሕግ ሐሤት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን በብልቶቼ ውስጥ ለሚሠራው የኀጢአት ሕግ እኔን እስረኛ በማድረግ፣ ከአእምሮዬ ሕግ ጋራ የሚዋጋ ሌላ ሕግ በብልቶቼ ውስጥ ሲሠራ አያለሁ። እኔ ምን ዐይነት ጐስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ሊያድነኝ ይችላል? በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን! እንግዲያስ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ ባሪያ ስሆን፣ በኀጢአተኛ ተፈጥሮዬ ግን ለኀጢአት ሕግ ባሪያ ነኝ። ነገር ግን ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ሰው ብታገባ አመንዝራ ትባላለች፤ ባሏ ቢሞት ግን ሌላ ሰው ብታገባም እንኳ፣ ከዚያ ሕግ ነጻ ትሆናለች፤ አመንዝራ አትባልም።
እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? በሥጋም በመንፈስም የርሱ ናቸው። ለምን አንድ አደረጋቸው? ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለውን ዘር ይፈልግ ስለ ነበር ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁም ጋራ ያላችሁን ታማኝነት አታጓድሉ።
አዳምም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።” ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
ሴቶች በጉባኤ ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤ ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።
አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ከርሱ ጋራ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን፣ የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት። ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ባሏ እንጂ። እንዲሁም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሚስቱ እንጂ። እንደ እኔ ከሆነ ግን ሳታገባ እንዲሁ ብትኖር ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለች፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመስለኛል።
እንዲህ ከሆኑ፣ ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ማስተማር ይችላሉ፤ የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።
ባል ለሚስቱ የሚገባትን ሁሉ ያድርግላት፤ ሚስትም ለባሏ እንዲሁ። የሚያለቅሱ እንደማያለቅሱ፣ ደስተኞች ደስ እንደማይላቸው ይሁኑ፤ ዕቃ የሚገዙም የገዙት ነገር የእነርሱ እንዳልሆነ ይቍጠሩ፤ በዚህ ዓለም ነገር የሚጠቀሙም እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ፤ የዚህ ዓለም መልክ ዐላፊ ነውና። እኔስ ያለ ጭንቀት እንድትኖሩ እወድዳለሁ። ያላገባ ሰው ጌታን ደስ ለማሠኘት ስለ ጌታ ነገር ያስባል፤ ያገባ ሰው ግን ሚስቱን ደስ ለማሠኘት የዚህን ዓለም ነገር ያስባል፤ በዚህም ልቡ ተከፍሏል። ያላገባች ሴት ወይም ድንግል ስለ ጌታ ነገር ታስባለች፤ ዐላማዋም በሥጋና በመንፈስ ለጌታ መቀደስ ነው። ያገባች ሴት ግን ባሏን ደስ ለማሠኘት የዚህን ዓለም ነገር ታስባለች። ይህንም የምለው ለእናንተ የሚበጃችሁን ነገር በማሰብ እንጂ ላስጨንቃችሁ አይደለም፤ ዐላማዬም ልባችሁ ሳይከፈል በጌታ ጸንታችሁ በአግባብ እንድትኖሩ ነው። አንድ ሰው ያጫትን ድንግል በአግባቡ ካልያዘ፣ እርሷም በዕድሜ እየገፋች ከሄደች፣ ሊያገባት ካሰበ የወደደውን ያድርግ፤ ኀጢአት የለበትምና ይጋቡ። ነገር ግን በዚህ ጕዳይ ልቡን አረጋግቶ፣ ሳይናወጥ፣ ራሱንም በመግዛት ድንግሊቱን ላለማግባት የወሰነ ሰው መልካም አድርጓል። ስለዚህ ድንግሊቱን ያገባ መልካም አደረገ፤ ያላገባም የተሻለ አደረገ። አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ከርሱ ጋራ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን፣ የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት። ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ባሏ እንጂ። እንዲሁም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሚስቱ እንጂ። እንደ እኔ ከሆነ ግን ሳታገባ እንዲሁ ብትኖር ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለች፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመስለኛል። በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና ዐብራችሁ ሁኑ።
ስለዚህ ባል የሞተባቸው ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ፣ ልጆች እንዲወልዱ፣ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ጠላትም የሚነቅፍባቸውን ነገር እንዳያገኝ እመክራለሁ።
ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤ ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምን ጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤
እንዲሁም አሮጊቶች በአኗኗራቸው የተከበሩ እንዲሆኑ፣ በጎ የሆነውን የሚያስተምሩ እንጂ የሰው ስም የሚያጠፉ ወይም በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ አስተምራቸው።