ነህምያ 8:10ነህምያም፣ “ሂዱ፤ ጥሩ ምግብ በመብላት፣ ጣፋጩን በመጠጣት ደስ ይበላችሁ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ካላችሁ ላይ ከፍላችሁ ላኩላቸው። ይህች ቀን ለጌታችን የተቀደሰች ናት፤ የእግዚአብሔር ደስታ ብርታታችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።
መዝሙር 16:11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።
ሮሜ 15:13በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው።
መዝሙር 5:11አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው።
መዝሙር 28:7እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።
ዮሐንስ 15:11ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ።
ገላትያ 5:22የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣
ኢሳይያስ 61:10በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
መዝሙር 118:24እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ በርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።
1 ተሰሎንቄ 5:16-18ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ሳታቋርጡ ጸልዩ፤በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።
1 ጴጥሮስ 1:8-9እርሱንም ሳታዩት ትወድዱታላችሁ፤ አሁን ባታዩትም በርሱ ታምናላችሁ፤ መግለጽ በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ብሏችኋል፤የእምነታችሁን ፍጻሜ፣ እርሱም የነፍሳችሁን ድነት እየተቀበላችሁ ነውና።
መዝሙር 126:2-3በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።
መዝሙር 4:7ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣ አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል።
ዕንባቆም 3:17-18ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በድነቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
ፊልጵስዩስ 3:1ከዚህ በተረፈ ወንድሞቼ ሆይ፤ በጌታ ደስ ይበላችሁ! ያንኑ ደግሜ ብጽፍላችሁ፣ እኔ አይሰለቸኝም፤ ለእናንተም ይጠቅማችኋል።
ኢሳይያስ 12:2-3እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።”ከድነቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
መዝሙር 97:11-12ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።
መዝሙር 32:11ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ።
ምሳሌ 10:28የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤ የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።
መዝሙር 100:1-2ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤ በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።
ሮሜ 14:17የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም፣ በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ሐሤት ነው እንጂ፣ የመብልና የመጠጥ ጕዳይ አይደለም፤
መዝሙር 30:5ቍጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል።
ኢሳይያስ 55:12በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኰረብቶች፣ በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤ የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ ያጨበጭባሉ።
መዝሙር 68:3ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት ሐሤት ያድርጉ፤ ደስታንና ፍሥሓን የተሞሉ ይሁኑ።
መዝሙር 144:15ብፁዕ ነው፤ ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ፤ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ።
ኤርምያስ 15:16ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።
መዝሙር 9:2በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።
መዝሙር 92:4እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።
መዝሙር 35:9ነፍሴም በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤ በማዳኑም ሐሤት ታደርጋለች።
ሮሜ 5:3-4በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን።ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤
ዮሐንስ 16:22ለእናንተም እንደዚሁ አሁን የሐዘን ጊዜ ነው፤ ሆኖም እንደ ገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።
መዝሙር 45:7ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።
መዝሙር 43:4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤ ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ።
ዘካርያስ 10:7ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል። ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።
መዝሙር 13:5እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
መዝሙር 97:1እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ።
መዝሙር 21:6ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍሥሓም ደስ አሠኘኸው፤
ኢሳይያስ 9:3ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
ፊልጵስዩስ 2:2በአንድ ሐሳብ፣ በአንድ ፍቅር፣ በአንድ መንፈስና በአንድ ዐላማ በመሆን ደስታዬን ፍጹም አድርጉልኝ።
መዝሙር 89:15-16ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣ በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ፤ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤ በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤
ኢሳይያስ 25:9በዚያ ቀን እንዲህ ይባላል፤ “እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤ በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”
መዝሙር 47:1ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
ዮሐንስ 17:13“አሁን ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ ነገር ግን ደስታዬ በእነርሱ ዘንድ የተሟላ እንዲሆን፣ አሁን በዓለም እያለሁ ይህን እናገራለሁ።
መዝሙር 40:16አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስ ይበላቸው፤ ዘወትር የአንተን ማዳን የሚወድዱ፣ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
ሮሜ 12:12በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።
ሶፎንያስ 3:17እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤ እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤ በዝማሬም በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል።”
ሉቃስ 10:20ይሁን እንጂ መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
መዝሙር 126:5-6በእንባ የሚዘሩ፣ በእልልታ ያጭዳሉ።ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዷቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ።
1 ጴጥሮስ 4:13ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ደስ ይበላችሁ።
መዝሙር 16:9ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
ማቴዎስ 5:12በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳድደዋቸዋልና።
2 ቆሮንቶስ 7:4በእናንተ ላይ ያለኝ እምነት ትልቅ ነው፤ በእናንተም ላይ ያለኝ ትምክሕት ትልቅ ነው፤ እንዲሁም እጅግ ተጽናንቻለሁ፤ በመከራችንም ሁሉ ደስታዬ ወሰን የለውም።
መዝሙር 149:2እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።
ሉቃስ 15:7እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።
ኢሳይያስ 51:11እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
ሐዋርያት ሥራ 2:46በየዕለቱ በቤተ መቅደስ በአንድነት እየተገናኙ፣ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በቀና ልብ ይመገቡ ነበር፤
መዝሙር 71:23ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።
ኢሳይያስ 41:16ታበጥራቸዋለህ፤ ነፋስ ጠርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእስራኤል ቅዱስ ሞገስ ታገኛለህ።
ፊልጵስዩስ 1:25ይህን በማስተዋል፣ በእምነት እንድታድጉና ደስ እንዲላችሁ፣ በሁላችሁ ዘንድ እንደምቈይና እንደምኖር ተረድቻለሁ።
መዝሙር 63:7አንተ ረዳቴ ነህና፣ በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።
መዝሙር 30:11ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ፤ ማቄን አውልቀህ ፍሥሓን አለበስኸኝ፤
ኤርምያስ 31:13ኰረዶች ይዘፍናሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤ ጐረምሶችና ሽማግሌዎችም ይፈነጥዛሉ፤ ልቅሷቸውን ወደ ደስታ እለውጣለሁ፤ ከሐዘናቸውም አጽናናቸዋለሁ፤ ደስታንም እሰጣቸዋለሁ።
ኢሳይያስ 35:10እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
ምሳሌ 12:20ክፋትን በሚያውጠነጥኑ ሰዎች ልብ አታላይነት አለ፤ ሰላምን የሚያራምዱ ግን ደስታ አላቸው።
ኢሳይያስ 65:18-19ነገር ግን በምፈጥረው፣ ደስ ይበላችሁ፤ ለዘላለም ሐሤት አድርጉ። ኢየሩሳሌምን ለደስታ፣ ሕዝቧን ለሐሤት እፈጥራለሁና።በኢየሩሳሌም እደሰታለሁ፤ በሕዝቤ ሐሤት አደርጋለሁ፤ የልቅሶና የጩኸት ድምፅ፣ ከእንግዲህ በዚያ አይሰማም።
ሮሜ 15:32ይኸውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተም ጋራ እንድታደስ ነው።
ምሳሌ 17:22ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል።
መዝሙር 98:4ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
ኢሳይያስ 44:23ሰማያት ሆይ፤ እግዚአብሔር ይህን አድርጓልና ዘምሩ፤ የምድር ጥልቆች ሆይ፤ በደስታ ጩኹ። እናንተ ተራሮች፣ እናንተ ደኖችና ዛፎቻችሁ ሁሉ እልል በሉ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቷል፣ በእስራኤልም ክብሩን ገልጧልና።
1 ተሰሎንቄ 1:6እናንተ እኛንና ጌታን መስላችኋል፤ ምንም እንኳ ብርቱ መከራ ቢደርስባችሁም፣ ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብላችኋል።
ዮሐንስ 14:27ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።
ሮሜ 5:11ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን።
ኢሳይያስ 49:13ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ! እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ ለተቸገሩትም ይራራልና።
መዝሙር 66:1-2ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል ይበል!አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤ እንደ ብርም አነጠርኸን።ወደ ወጥመድ አገባኸን፤ በጀርባችንም ሸክም ጫንህብን።ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤ በእሳትና በውሃ መካከል ዐለፍን፤ የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤በመከራ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣ በከንፈሬም የተናገርሁት ስእለት ነው።ፍሪዳዎችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣ አውራ በጎችንም የሚጤስ ቍርባን አድርጌ አቀርብልሃለሁ፤ ኰርማዎችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ። ሴላእግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤ በአንደበቴም አመሰገንሁት።ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ ጌታ ባልሰማኝ ነበር።አሁን ግን እግዚአብሔር በርግጥ ሰምቶኛል፤ ጸሎቴንም አድምጧል።ለስሙ ክብር ዘምሩ፤ ውዳሴውንም አድምቁ።
መዝሙር 89:12ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።
መዝሙር 95:1-2ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤ በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤ እኔም፣ “በልቡ የሳተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።ስለዚህ እንዲህ ብዬ በቍጣዬ ማልሁ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።”ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው።
1 ሳሙኤል 2:1ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ይለኛልና።
መዝሙር 64:10ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይበለው፤ እርሱንም መጠጊያ ያድርገው፤ ልበ ቅኖችም ሁሉ ደስ ይበላቸው።
መዝሙር 67:4ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ
ሐዋርያት ሥራ 16:34የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ወደ ቤቱ ወስዶ ማእድ አቀረበላቸው፤ ከቤተ ሰቡም ሁሉ ጋራ በእግዚአብሔር በማመኑ በደስታ ተሞላ።
ኢሳይያስ 52:9እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና።
መዝሙር 97:12እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።
ኢሳይያስ 12:6የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”
መዝሙር 126:1-2እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
ምሳሌ 23:24የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ ጠቢብ ልጅ ያለውም በርሱ ሐሤት ያደርጋል።
ኢሳይያስ 61:3በጽዮን ያዘኑትን እንዳረጋጋ፣ በዐመድ ፈንታ፣ የውበት አክሊል እንድደፋላቸው፣ በልቅሶ ፈንታ፣ የደስታ ዘይት በራሳቸው ላይ እንዳፈስስላቸው፣ በትካዜ መንፈስ ፈንታ፣ የምስጋና መጐናጸፊያ እንድደርብላቸው ልኮኛል፤ እነርሱም የክብሩ መግለጫ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር የተከላቸው፣ የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።
ፊልጵስዩስ 4:1ስለዚህ የምወድዳችሁና የምናፍቃችሁ፣ ወንድሞቼ ደስታዬና አክሊሌ የሆናችሁ፣ እንዲሁም ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ሁኔታ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ!
ዕብራውያን 12:2የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።
ኢሳይያስ 62:5ጕልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ ልጆችሽ እንዲሁ ያገቡሻል፤ ሙሽራ በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፣ አምላክሽም በአንቺ ደስ ይለዋል።
ሮሜ 8:28እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።
መዝሙር 63:5ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።
ምሳሌ 15:23ሰው ተገቢ መልስ በመስጠት ደስታን ያገኛል፤ በወቅቱም የተሰጠ ቃል ምንኛ መልካም ነው!
መዝሙር 16:8-9እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
መዝሙር 70:4አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስም ይበላቸው፤ ማዳንህን የሚወድዱ ሁሉ ሁልጊዜ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
ዘካርያስ 8:19የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”
ሐዋርያት ሥራ 11:23እርሱም እዚያ ደርሶ እግዚአብሔር በጸጋው የሠራውን ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በፍጹም ልብ በጌታ በመታመን እንዲጸኑ መከራቸው።
መዝሙር 51:8ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፤ ያደቀቅሃቸው ዐጥንቶቼም ደስ ይበላቸው።
መዝሙር 85:6ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣ መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?
ኢዩኤል 2:23የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቷችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል።
ዮሐንስ 20:20ይህንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርትም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው።
ምሳሌ 15:13ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይሰብራል።
መዝሙር 21:1እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥ በኀይልህ ደስ ይለዋል፤ በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል።
መዝሙር 90:14በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።
መዝሙር 32:7አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ በድል ዝማሬም ትከብበኛለህ። ሴላ
1 ዮሐንስ 3:18ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።
መዝሙር 48:11ስለ ፍርድህ፣ የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤ የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።
ማቴዎስ 25:21“ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ ባሪያ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።
ሉቃስ 24:52እነርሱም ሰገዱለት፤ በታላቅ ደስታም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤
ዕብራውያን 10:34እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ።
ኢሳይያስ 35:2በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤ የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል። የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ያያሉ።
ሉቃስ 6:23“እነሆ፤ ወሮታችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፣ በዚያ ቀን ደስ ይበላችሁ፤ ፈንድቁም፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነበርና።
መዝሙር 65:13ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም።
ሮሜ 4:7-8“መተላለፋቸው ይቅር የተባለላቸው፣ ኀጢአታቸው የተሰረየላቸው፣ ብፁዓን ናቸው።ኀጢአቱን፣ ጌታ ከቶ የማይቈጥርበት ሰው ምስጉን ነው።”
መዝሙር 43:5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤ አዳኜና አምላኬን፣ ገና አመሰግነዋለሁና።
ኤርምያስ 32:41ለእነርሱ መልካም በማድረግ ደስ ይለኛል፤ በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በእውነት በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።’
ነህምያ 12:43እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለ ሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።
ሉቃስ 15:23-24የሠባውንም ፍሪዳ አምጡና ዕረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት፤ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።
መዝሙር 138:5የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና፣ ስለ እግዚአብሔር መንገድ ይዘምሩ።
2 ቆሮንቶስ 8:2የደረሰባቸው መከራ ጽኑ ቢሆንም ደስታቸው ግን የላቀ ነበር፤ ድኽነታቸው ብርቱ ቢሆንም ልግስናቸው ግን የበዛ ነበር።
ይሁዳ 1:24-25እንዳትወድቁ ሊጠብቃችሁና ያለ ነቀፋና በደስታ በክብሩ ፊት ሊያቀርባችሁ ለሚችለው፣እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከዘመናት ሁሉ በፊት፣ አሁንና እስከ ዘላለምም ድረስ ክብር፣ ግርማ፣ ኀይልና ሥልጣን ይሁን! አሜን።
ዮሐንስ 3:29ሙሽራዪቱ የሙሽራው ናት፤ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን፣ የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል።
ዘዳግም 12:7በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትበላላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን በባረከበት፣ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተ ሰዎችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።
ኢሳይያስ 65:14ባሮቼ፣ ከልብ በመነጨ ደስታ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን፣ ልባችሁ በማዘኑ ትጮኻላችሁ፤ መንፈሳችሁ በመሰበሩም ወዮ ትላላችሁ።
መዝሙር 45:15በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤ ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ።
ሮሜ 5:2በርሱም በኩል አሁን ወደ ቆምንበት ጸጋ በእምነት መግባት ችለናል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ተስፋ በማድረግ ሐሤት እናደርጋለን።
መዝሙር 30:12እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።
ያዕቆብ 1:2ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤
1 ጴጥሮስ 1:6አሁን በብዙ ዐይነት ፈተና ውስጥ ሆናችሁ ለጥቂት ጊዜ መከራን ብትቀበሉም እንኳ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል።