Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


111 ጥቅሶች፡ የመንግስተ ሰማያት ሀብት

111 ጥቅሶች፡ የመንግስተ ሰማያት ሀብት

ብዙ ጊዜ በዚህ ዓለም ላይ ያለው ሀብትና ንብረት እንድናካብት የሚገፋፋን ማህበረሰብ ውስጥ እንገኛለን። ግን እዚህ ምድር ላይ ባለን ነገር ከማተኮር ይልቅ በሰማይ ሀብት መፈለግ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስበህበታል?

በሰማይ ሀብት መፈለግ ማለት ለሌሎች የሚጠቅሙና ለጋራ ጥቅም የሚያበረክቱ ተግባራትን ማድረግ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረቱ እሴቶቻችንን ማጠናከር ማለት ነው። ጊዜያዊና የሚጠፉ የሆኑት ቁሳዊ ሀብቶች በተለየ መልኩ፣ በሰማይ የሚገኙ ሀብቶች ዘላለማዊ ናቸው፤ ከዚህኛው ህይወታችንም በላይ ይዘልቃሉ።

በአጭሩ፣ በሰማይ ሀብት መፈለግ እግዚአብሔር ለእኛ በወሰነው ፈቃድ መሰረት መኖር እና ዘላቂ የሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ ላላቸው ተግባራት ጊዜና ጉልበታችንን መስጠት ማለት ነው።

በዚህ ዓለም ብልጽግናንና ምቾትን ከመፈለግ ባሻገር፣ ለሌሎች ደግነትና ፍቅር የተሞላ ውርስ መገንባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ማስታወስ አለብን። እውነተኛ ሀብትንና የህይወት ትርጉምን የምናገኘው በዚህ መንገድ ነው።

ማቴዎስ 6:20 “ነገር ግን ለራሳችሁ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ በዚያ ሌባ አይቆፍርም፥ ብልም አያጠፋም።”


ማቴዎስ 6:19-21

“ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። “ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤ ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:20

ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:21

ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:21

ኢየሱስም፣ “ፍጹም ለመሆን ከፈለግህ፣ ሄደህ ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ይኖርሃል፤ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:45-46

“እንዲሁም መንግሥተ ሰማይ ውብ ዕንቍ የሚፈልግ ነጋዴ ትመስላለች፤ እጅግ ውድ የሆነ ዕንቍ ባገኘም ጊዜ፣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ገዛው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:33

ያላችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ፤ ሌባ በማይሰርቅበት፣ ብል በማይበላበት፣ በማያረጅ ከረጢት የማያልቅ ሀብት በሰማይ አከማቹ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:33-34

ያላችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ፤ ሌባ በማይሰርቅበት፣ ብል በማይበላበት፣ በማያረጅ ከረጢት የማያልቅ ሀብት በሰማይ አከማቹ፤ ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁ በዚያ ይሆናልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:22

ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ “እንግዲያውስ አንድ ነገር ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ይኖርሃል፤ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 2:5

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:16

እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:7-8

ነገር ግን ይጠቅመኝ የነበረውን ሁሉ አሁን ለክርስቶስ ስል እንደ ጕድለት ቈጥሬዋለሁ። ከዚህም በላይ ለርሱ ብዬ ሁሉን ነገር የተውሁለትን፣ ወደር የሌለውን ጌታዬን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ ታላቅነት ጋራ ሳነጻጽር፣ ሁሉንም ነገር እንደ ጕድለት እቈጥረዋለሁ፤ ለርሱ ስል ሁሉን ዐጥቻለሁ፤ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:2

ሐሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:7

ነገር ግን ይህ እጅግ ታላቅ ኀይል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አለመሆኑን ለማሳየት፣ ይህ የከበረ ነገር በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:21

“ስለዚህ ለራሱ ሀብት የሚያከማች፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:17-19

በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። መልካም እንዲሠሩ፣ ቸሮችና ለማካፈል ፈቃደኞች የሆኑ እንዲሆኑ እዘዛቸው። በዚህ ዐይነት እውነተኛ የሆነውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ፣ ለሚመጣው ዘመን ጽኑ መሠረት የሚሆን ሀብት ለራሳቸው ያከማቻሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:44

“መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፤ አንድ ሰው ባገኛት ጊዜ መልሶ ሸሸጋት፤ ከመደሰቱም የተነሣ፣ ሄዶ ያለውን ሁሉ በመሸጥ ያን የዕርሻ ቦታ ገዛ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:19

በዚህ ዐይነት እውነተኛ የሆነውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ፣ ለሚመጣው ዘመን ጽኑ መሠረት የሚሆን ሀብት ለራሳቸው ያከማቻሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:33

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:20

በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ ሞኝ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:3

“በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 48:7

በድርጊታችሁና በብልጽግናችሁ ስለምትታመኑ፣ እናንተም ትማረካላችሁ፤ ካሞሽም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋራ፣ በምርኮ ይወሰዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:17-18

ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ የክብሩ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ በርግጥ የመከራው ተካፋዮች ብንሆን፣ የእግዚአብሔር ወራሾች፣ ከክርስቶስ ጋራ ዐብረን ወራሾች ነን። የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው፣ ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋራ ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 50:25

እግዚአብሔር የመሣሪያ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤ የቍጣውን የጦር ዕቃ አውጥቷል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በባቢሎናውያን ምድር ሥራ አለውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:17-18

ምክንያቱም ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል። ስለዚህ ዐይናችን የሚያተኵረው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን በማይታየው ላይ ነው፤ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:35

መልካም ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር መልካም ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ካከማቸው ክፉ ነገር መጥፎ ነገርን ያወጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:52

እርሱም፣ “ስለዚህም የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ማንኛውም የኦሪት ሕግ መምህር፣ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለንብረት ይመስላል” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:4

እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ፣ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደ ገና ወለደን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 10:21

ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ “እንግዲያው አንድ ነገር ይጐድልሃል፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ይኖርሃል፤ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 11:26

ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ፤ ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 12:33

ይህን የተናገረው በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት ለማመልከት ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 10:39

ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፤ ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ግን ያገኛታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 16:26

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው በነፍሱ ምትክ ሊከፍለው የሚችለው ዋጋ ምንድን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:10-11

ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤ ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:12

በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳድደዋቸዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:34

እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:18

እንዲሁም በርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:2-3

ደግሞም ልባቸው እንዲጽናናና በፍቅር እንዲተሳሰሩ፣ ፍጹም የሆነውን የመረዳት ብልጽግና አግኝተው የእግዚአብሔር ምስጢር የሆነውን ክርስቶስን እንዲያውቁ እተጋለሁ፤ ለዚህ ዓለም መርሕ ከክርስቶስ ጋራ ከሞታችሁ፣ ታዲያ በዚህ ዓለም እንደሚኖር ለምን ትገዙላቸዋላችሁ? “አትያዝ! አትቅመስ! አትንካ!” እንደሚሉት ዐይነት፣ እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ ጠፊ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም። የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የሚገኘው በርሱ ዘንድ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 6:23

“እነሆ፤ ወሮታችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፣ በዚያ ቀን ደስ ይበላችሁ፤ ፈንድቁም፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነበርና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:72

ከአእላፋት ብርና ወርቅ ይልቅ፣ ከአፍህ የሚወጣው ሕግ ይሻለኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:21

“ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ ባሪያ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 22:12

“እነሆ፤ ቶሎ እመጣለሁ፤ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 73:25-26

በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምሻው የለኝም። ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣ የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 3:12-14

ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ወይም በብር፣ በከበረ ድንጋይ ወይም በዕንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ ሥራው እንዴት እንደ ሆነ ይታያል፤ ምክንያቱም ያ ቀን ወደ ብርሃን ያመጣዋል። በእሳት ስለሚገለጥ እሳቱ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ምንነት ይፈትናል። ማንም የገነባው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 4:8

ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በዚያ ቀን ለእኔ ይሰጠኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የርሱን መገለጥ ለናፈቁ ሁሉ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:31-32

ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ አንድ ሰው ወስዶ በዕርሻው ቦታ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች። የሰናፍጭ ዘር ከሌሎች ሁሉ ያነሰች ብትሆንም፣ ስታድግ ግን ከአትክልት ሁሉ በልጣ፣ የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቿ ላይ እስኪያርፉ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:21

“በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:5

ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 33:6

እርሱ ለዘመንህ የሚያስተማምን መሠረት፣ የድነት፣ የዕውቀትና የጥበብ መዝገብ ይሆናል፤ እግዚአብሔርንም መፍራት የዚህ ሀብት ቍልፍ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 3:8

ምንም እንኳ ከቅዱሳን ሁሉ ያነስሁ ብሆንም፣ የማይመረመረውን የክርስቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ ይህ ጸጋ ለእኔ ተሰጠኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:13-15

ብፁዕ ነው፤ ጥበብን የሚያገኛት፣ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው፤ እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና። ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 11:11

እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴት ከተወለዱት መካከል እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 10:20

ይሁን እንጂ መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:6-7

እግዚአብሔር “ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል”። በጎ የሆነውን ጸንቶ በማድረግ ክብርን፣ ሞገስንና ዘላለማዊነትን ለሚሹ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 3:16

በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:10

መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:34

“በዚያ ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 16:11

የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:24

“ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወድዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:15

ደግሞም፣ “የሰው ሕይወቱ በሀብቱ ብዛት የተመሠረተ ስላልሆነ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ራሳችሁንም ጠብቁ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:1

መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤ መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:23-24

ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለሀብታም ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት ከባድ ነው። ደግሜ እላችኋለሁ፤ ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 8:36-37

ሰው ዓለሙ ሁሉ የርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል? ለመሆኑ፣ ሰው ለነፍሱ ምን መተኪያ አለው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:33

የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም፤ ለመንገዱም ፈለግ የለውም!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:7

እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ፣ እውነተኛ መሆኑ እንዲረጋገጥና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:4

የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን አክሊል ትቀበላላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:1-2

“እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤ እናንተ ገንዘብ የሌላችሁ፣ ወደ ውሆች ኑ፤ ኑና ግዙ፤ ብሉም! ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣ የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣ ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል። በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኰረብቶች፣ በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤ የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ ያጨበጭባሉ። በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣ በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል። ይህም የእግዚአብሔር መታሰቢያ፣ ሊጠፋ የማይችል፣ የዘላለም ምልክት ይሆናል።” ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:4

በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:4

በቍጣ ቀን ሀብት ፋይዳ የለውም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ትታደጋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 2:12

ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ አበረታታናችሁ፤ አጽናናናችሁ፤ አጥብቀንም ለመንናችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:11

እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 3:18

ስለዚህ ሀብታም እንድትሆን፣ በእሳት የነጠረ ወርቅ እንድትገዛ፣ የዕራቍትነትህ ኀፍረት እንዳይታይ፣ ነጭ ልብስ እንድትለብስና ለማየት እንድትችል ዐይንህን በኵል እንድትኳል እመክርሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:33

አሁንም ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ በመደባለቅ የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 14:33

እንደዚሁም፣ ከእናንተ ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው፣ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:29

ስለ ስሜ ብሎ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን ወይም ዕርሻን የሚተው ሁሉ መቶ ዕጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 84:10

በሌላ ስፍራ ሺሕ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣ በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 22:14

“የተጠሩት ብዙዎች፣ የተመረጡት ግን ጥቂቶች ናቸውና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 2:9

ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:13-14

“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:19

አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 8:9

የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:12

በፈተና የሚጸና ሰው ብፁዕ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወድዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:23

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:8-9

በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:8

እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤ እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ብፁዕ ነው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:11

ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:17

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም፣ በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ሐሤት ነው እንጂ፣ የመብልና የመጠጥ ጕዳይ አይደለም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:3

በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:3-4

በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል። ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ፣ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:8

ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:5

የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 61:7

ሕዝቤ በኀፍረታቸው ፈንታ፣ ዕጥፍ ይቀበላሉ፤ በውርደታቸው ፈንታ፣ በርስታቸው ደስ ይላቸዋል፤ የምድራቸውንም ዕጥፍ ርስት ይወርሳሉ፤ ዘላለማዊ ደስታም የእነርሱ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:32

ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከርሱ ጋራ እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:23

“ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ ባሪያ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:18

ሀብትና ክብር፣ ዘላቂ ብልጽግናና ስኬት በእኔ ዘንድ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 1:21

ለእኔ፣ መኖር ክርስቶስ ነው፤ ሞትም ማትረፍ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 21:7

ድል የሚነሣ ይህን ሁሉ ይወርሳል፤ እኔም አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 16:11

እንግዲህ፣ በዚህ ዓለም ሀብት ካልታመናችሁ፣ እውነተኛውንማ ሀብት ማን ዐደራ ብሎ ይሰጣችኋል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:127

ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ ትእዛዞችህን ወደድሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:47-50

“ደግሞም መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር ተጥሎ የዓሣ ዐይነቶችን የያዘ መረብ ትመስላለች፤ ዓሣ አጥማጆቹ መረቡ ሲሞላላቸው ጐትተው ወደ ባሕሩ ዳር አወጡት፤ ከዚያም ተቀምጠው ጥሩ ጥሩውን እየለዩ በቅርጫት ውስጥ ጨመሩ፤ መጥፎ መጥፎውን ግን ጣሉት። በዓለም መጨረሻም ልክ እንደዚሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኀጢአተኞችን ከጻድቃን በመለየት፣ አንዳንዱም ዘር በቂ ዐፈር በሌለበት በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፤ ዐፈሩ ጥልቀት ስላልነበረው ፈጥኖ በቀለ፤ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:10

ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:22

የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤ መከራንም አያክልባትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:10

ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 9:8

ሁልጊዜ በሁሉ ነገር የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ እንድትተርፉ፣ እግዚአብሔር ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:2-3

በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። እኔ በአባቴ እንዳለሁ፣ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፣ እኔም ደግሞ በእናንተ እንዳለሁ በዚያ ቀን ትረዳላችሁ። የሚወድደኝ ትእዛዜን ተቀብሎ የሚጠብቅ ነው፤ የሚወድደኝንም አባቴ ይወድደዋል፤ እኔም እወድደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” ከዚያም የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳ፣ “ጌታ ሆይ፤ ታዲያ፣ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወድደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወድደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከርሱም ጋራ እንኖራለን። የማይወድደኝ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። “አሁን ከእናንተ ጋራ እያለሁ ይህን ሁሉ ነግሬአችኋለሁ፤ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል። ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም። “ ‘እሄዳለሁ፤ ተመልሼም ወደ እናንተ እመጣለሁ’ ማለቴን ሰምታችኋል፤ ብትወድዱኝስ አብ ከእኔ ስለሚበልጥ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ የተናገርሁት ሲፈጸም እንድታምኑ፣ ከመሆኑ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋራ እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:25

ለውድድር የሚዘጋጅ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል፤ እነርሱ ዐላፊ ጠፊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ይደክማሉ፤ እኛ ግን ለዘላለም የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት እንደክማለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:12

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:1

መኖሪያችን የሆነው ምድራዊ ድንኳን ቢፈርስም፣ በሰው እጅ ያልተሠራ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሆነ ዘላለማዊ ቤት በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:9

ስለዚህ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ገና ቀርቶለታል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:18-19

እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል። በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤ በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ታማኝ ነህ፣ መንገዶችህም ሁሉ ቅን ናቸው። ከውበትህ ጋር የሚተካከል ምንም የለም። ቅዱስና የተከበርክ ነህ። ስምህ የአምልኮና የክብር ሁሉ ይገባዋል። እግዚአብሔር ሆይ፣ የሕይወቴ ማዕከል እንድትሆን እፈልጋለሁ። የኖርኩባቸው ቀናት ሁሉ ፈቃድህን ለማድረግና በሕግጋትህና በሥርዓትህ ለመመላለስ እንዲሆኑልኝ እሻለሁ። ስለዚህ፣ ሙሉ በሙሉ በአንተ ላይ እንድያተኩር እርዳኝ። ምንም ነገር እንዳያዘናጋኝ። በምድር ላይ የሰጠኸኝን ጊዜ ዋጋ እንድሰጠው እፈልጋለሁ፣ በሰማይ የሚከማቹ ሀብቶችን እንዳከማች፣ ልክ እንደ ቃልህ፣ "ዝገትና ብል በማያጠፉበት፣ ሌቦችም በማይሰብሩበትና በማይሰርቁበት በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት ክምችቱ።" አንተ ግቤ፣ ዋንጫዬና ፍቅሬ ሁን። ዛሬ እንደገና ሕይወቴ የአንተ እንደሆነ ልነግርህ በእግርህ ሥር እሰግዳለሁ። በእጅህ የክብር ዕቃ እንድሆን እፈልጋለሁ። በአምሳልህ ቅረፀኝ። እርምጃዬን አቅና። ልቤን በመገኘትህ ሙላው። መንፈስህም ሁልጊዜ ይምራኝ። ቸርና ሩኅሩኅ ስለሆንክ አመሰግናለሁ። በኢየሱስ ስም አመልክሃለሁ እና አከብርሃለሁ። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች