Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


101 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ የኢየሱስ ዕርገት

101 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ የኢየሱስ ዕርገት

ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለአርባ ቀናት ለደቀ መዛሙርቱ ስለእግዚአብሔር መንግሥት አስተምሯቸዋል። በዕርገት ቀን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ በፍቅርና በርኅራኄ ተናገራቸው፣ ተልእኳቸውን አስታወሳቸው፣ የመንፈስ ቅዱስን መምጣትም ቃል ገባላቸው። ሐዋርያት ሥራ 2:33 “ስለዚህም በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎ፥ ከአባቱም የተሰጠውን የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ተቀብሎ ይህን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰ።”

ወደ ሰማይ የኢየሱስ ዕርገት በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው። ኢየሱስ በምድር ላይ ተልእኮውን ከጨረሰ በኋላ ወደ አባቱ ዘንድ የተመለሰበት ጊዜ ነው። ዕርገቱ የምድራዊ አገልግሎቱ መጨረሻና በስሙ ላመኑና ለሚያምኑ አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ምልክት ነው።

እግዚአብሔር እንሆኖ ኢየሱስ ሥለ እኛ መዳን ሲል ሰው ሆኖ በመካከላችን እንደኖረ፣ እንዳስተማረን፣ እንደፈወሰንና እንደዋጀን ሰምተናል ወይም አንብበናል። ዕርገቱ ይህ ዓለም የመጨረሻ ቤታችን እንዳልሆነ ያስታውሰናል። የመጨረሻ መድረሻችን በሰማይ ነው፣ በዚህ በአንድ ወቅት በሚጠፋ ምድር ላይ አይደለም።

ዕርገት ማለት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሄዷል ማለት ብቻ አይደለም። ስለራሳችን ጥሪና ተልእኮ እንድናስብ ያደርገናል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ መልእክቱን ለአሕዛብ ሁሉ የማድረስና የትንሣኤው ምስክር የመሆን ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል። እኛም የክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን በዚህ ምድር ላይ የምንፈጽመው ልዩና የተወሰነ ተልእኮ አለን። በጨለማ ውስጥ ብርሃን እንድንሆን፣ ጠፍቶ የነበረውን እንድናገኝ፣ የክርስቶስን ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ እንድንሰብክ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለዓለም እንድናሳይና ኅብረተሰባችንን ለመለወጥ እንድንሠራ ተጠርተናል።


ሐዋርያት ሥራ 1:9

ይህን ካለ በኋላ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረችው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 24:50-53

ከዚህ በኋላ እስከ ቢታንያ ይዟቸው ወጣ፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። እየባረካቸውም ሳለ፣ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ። እነርሱም ሰገዱለት፤ በታላቅ ደስታም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ዘወትር በቤተ መቅደስ ነበሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 24:51

እየባረካቸውም ሳለ፣ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:10-11

እርሱም በሚሄድበት ጊዜ ትኵር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ፣ እነሆ፤ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤ እንዲህም አሏቸው፤ “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 16:19

ጌታ ኢየሱስ ይህን ከተናገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:20-21

ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየው ነው። የተቀመጠውም ከግዛትና ከሥልጣን፣ ከኀይልና ከጌትነት እንዲሁም በአሁኑ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚቻለው ስም ሁሉ በላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 16:28

ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ አሁን ግን ዓለምን ትቼ ወደ አብ እሄዳለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:2

በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 20:17

ኢየሱስም፣ “ገና ወደ አብ ስላላረግሁ፣ አትንኪኝ፤ ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፣ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ’ ብሏል ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 7:33

ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ ጋራ የምቈየው ጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:1

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋራ ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን ፈልጉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:12

እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ ከእነዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:14

እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 3:16

የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱ በሥጋ ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:12

ይህኛው ካህን ግን ስለ ኀጢአት አንዱን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:33

ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ካለ በኋላ፣ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ከአብ ተቀብሎ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:18

ወደ ላይ ዐረግህ፤ ምርኮ አጋበስህ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ፣ ከዐመፀኞችም ሳይቀር፣ ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 110:1

እግዚአብሔር ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:1-3

ቴዎፍሎስ ሆይ፤ ኢየሱስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ ቀደም ባለው መጽሐፌ ጽፌልሃለሁ፤ እርሱም በሚሄድበት ጊዜ ትኵር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ፣ እነሆ፤ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤ እንዲህም አሏቸው፤ “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።” ከዚያም ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ይህም ተራራ ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል ይርቅ ነበር። ወደ ከተማዪቱም በገቡ ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፤ እነዚህም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናኢው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ከሴቶቹና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ጋራ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋራ በአንድ ልብ ሆነው ያለ ማቋረጥ ተግተው ይጸልዩ ነበር። በእነዚያም ቀናት፣ ጴጥሮስ መቶ ሃያ በሚሆኑ ወንድሞች መካከል ቆሞ፣ እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፣ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፉ ቃል መፈጸም ስላለበት፣ እርሱ ከእኛ እንደ አንዱ ተቈጥሮ በዚህ አገልግሎት የመሳተፍ ዕድል አግኝቶ ነበር።” ይህ ሰው ስለ ክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በዚያም በግንባሩ ተደፍቶ ሰውነቱ እመካከሉ ላይ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ። ይህም በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ መሬቱም በቋንቋቸው “አኬልዳማ” ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም “የደም መሬት” ማለት ነው። ይኸውም እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ለመረጣቸው ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሰጣቸው ትእዛዝ ነው። ጴጥሮስም በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “በመዝሙር መጽሐፍ፣ ‘መኖሪያው ባድማ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይገኝ’ ደግሞም፣ ‘ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏል። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በመካከላችን በገባበትና በወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ ከእኛ ጋራ ከነበሩት መካከል አንድ ሰው መምረጥ ያስፈልጋል፤ ይኸውም፣ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ ተለይቶ እስካረገበት ቀን ድረስ የነበረ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋራ የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።” ስለዚህ ኢዮስጦስ የሚሉትን፣ በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቀረቡ፤ እንዲህም ብለው ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ታውቃለህ፤ ከእነዚህ ከሁለቱ መካከል የመረጥኸውን ሰው አመልክተንና ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና በሐዋርያዊነት ቦታ ላይ ሹመው።” ከዚያም ዕጣ ጣሉላቸው፤ ዕጣውም ለማትያስ ወጣ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋራ ተቈጠረ። ከሕማማቱም በኋላ ራሱ ቀርቦ ሕያው መሆኑን፣ ለእነዚሁ በብዙ ማስረጃ እያረጋገጠላቸው አርባ ቀንም ዐልፎ ዐልፎ እየታያቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:34

ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ እኛ ይማልዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:18

ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት ቀርቦ እንዲህም አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:2-3

በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። እኔ በአባቴ እንዳለሁ፣ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፣ እኔም ደግሞ በእናንተ እንዳለሁ በዚያ ቀን ትረዳላችሁ። የሚወድደኝ ትእዛዜን ተቀብሎ የሚጠብቅ ነው፤ የሚወድደኝንም አባቴ ይወድደዋል፤ እኔም እወድደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” ከዚያም የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳ፣ “ጌታ ሆይ፤ ታዲያ፣ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወድደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወድደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከርሱም ጋራ እንኖራለን። የማይወድደኝ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። “አሁን ከእናንተ ጋራ እያለሁ ይህን ሁሉ ነግሬአችኋለሁ፤ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል። ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም። “ ‘እሄዳለሁ፤ ተመልሼም ወደ እናንተ እመጣለሁ’ ማለቴን ሰምታችኋል፤ ብትወድዱኝስ አብ ከእኔ ስለሚበልጥ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ የተናገርሁት ሲፈጸም እንድታምኑ፣ ከመሆኑ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋራ እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 9:51

ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ጊዜ በመቃረቡ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 3:21

እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፣ ሁሉን ነገር እስከሚያድስበት ዘመን ድረስ እርሱ በሰማይ ይቈይ ዘንድ ይገባል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:64

ኢየሱስም፣ “አንተው ራስህ ብለኸዋል፤ ነገር ግን ለሁላችሁም ልንገራችሁ፤ ወደ ፊት የሰው ልጅ በኀያሉ ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 6:62

ታዲያ፣ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 7:55-56

እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፣ “እነሆ፤ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:6-7

ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?’ አትበል”፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ “ወይም ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል”፤ ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:3

እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:8

ስለዚህም እንዲህ ይላል፤ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ፣ ምርኮን ማረከ፤ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 19:12

ስለዚህም እንዲህ አለ፤ “አንድ መስፍን የንጉሥነትን ማዕርግ ተቀብሎ ለመመለስ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 17:5

እንግዲህ አባት ሆይ፤ ዓለም ሳይፈጠር ከአንተ ጋራ በነበረኝ ክብር በአንተ ዘንድ አክብረኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 16:27

የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክት ጋራ ይመጣል፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 9:24

ክርስቶስ የእውነተኛዪቱ ድንኳን ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደ ተሠራችው መቅደስ አልገባም፤ ነገር ግን አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ እርሷ፣ ወደ ሰማይ ገባ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:34-36

ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፤ እርሱ ራሱ ግን እንዲህ ብሏል፤ “ ‘ጌታ ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።’ “እንግዲህ፣ እግዚአብሔር ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን፣ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ ይረዳ!”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 110:4

“እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት፤ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሏል፤ እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:6

እግዚአብሔርም ከክርስቶስ ጋራ አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከርሱ ጋራ አስቀመጠን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:15

የገዦችና የባለሥልጣናትንም ማዕርግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:20

እኛ ግን አገራችን በሰማይ ነው፤ ከዚያ የሚመጣውንም አዳኝ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በናፍቆት እንጠባበቃለን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:8

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 3:13

ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:20

ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 10:42

ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታንም ላይ እንዲፈርድ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን እንድንመሰክር እርሱ ራሱ አዘዘን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:16

እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 7:25

ስለዚህ ስለ እነርሱ እየማለደ ሁልጊዜ በሕይወት ስለሚኖር፣ በርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:30-31

ነቢይ በመሆኑም፣ እግዚአብሔር ከዘሮቹ አንዱን በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል የገባለት መሆኑን ዐወቀ። ይህን አስቀድሞ በማየቱ እርሱ በሲኦል እንዳልቀረና ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ተናገረ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 1:1

ከሰዎች ወይም በሰው ከተላከው ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:24

ከዚያም ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ መንግሥትን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ፣ ያን ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:1

እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 24:47

ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለሕዝቦች ሁሉ ንስሓና የኀጢአት ስርየት በስሙ ይሰበካል’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:4

በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በኀይል ስለ ተገለጠው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:57

ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:22

እግዚአብሔርም ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም በማንኛውም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾመው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 9:12

የገባውም የፍየልንና የጥጃዎችን ደም ይዞ አይደለም፤ ነገር ግን የዘላለም ቤዛነት ሊያስገኝ የራሱን ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:9

ወዲያው ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 110:5

ጌታ በቀኝህ ነው፤ በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 7:39

ይህን ያለው በርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ ነበር፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ አልተሰጠም ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:10

እርሱም በሚሄድበት ጊዜ ትኵር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ፣ እነሆ፤ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:22

እርሱም ወደ ሰማይ ወጥቶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት፣ ኀይላትም ተገዝተውለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 2:9

ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ጥቂት እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ፣ የሞትን መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 47:5

አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:30

“በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 5:31

እርሱም ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአትን ስርየት ይሰጥ ዘንድ፣ እግዚአብሔር የሁሉ ራስና አዳኝ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 12:32

እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:4

ሕይወታችሁ የሆነው ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም በዚያ ጊዜ ከርሱ ጋራ በክብር ትገለጣላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 23:43

ኢየሱስም፣ “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:19-20

ከዚህ የተነሣ እናንተ ከቅዱሳን ጋራ የአንድ አገር ዜጋ፣ የእግዚአብሔርም ቤተ ሰብ አባል ናችሁ እንጂ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም። በዚህም፣ የዓለምን ክፉ መንገድ ተከትላችሁ፣ በአየር ላይ ላሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ ለሆነውና አሁንም ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 13:33

ኢየሱስንም ከሙታን በማስነሣቱ ለእነርሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሟል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር እንዲህ ብሎ ተጽፏል፤ “ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 8:1

እንግዲህ የምንናገረው ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 2:20

ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:9

ለዚሁ፣ የሙታንና የሕያዋን ጌታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል፤ በሕይወትም ተነሥቷል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 2:6

ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣ በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:8-9

ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 17:24

“አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ፣ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:20

ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቷል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:18

በእነዚያ ቀናት በወንዶችና በሴቶች ባሮቼም ላይ፣ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:15

ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰው መተላለፍ ብዙዎቹ ከሞቱ፣ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው፣ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የመጣው ስጦታ ለብዙዎች እንዴት አብልጦ ይትረፈረፍ!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:13-14

እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወድደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤ በርሱም ቤዛነትን በደሙ አግኝተናል፤ ይህም የኀጢአት ይቅርታ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 9:26

እንዲህ ቢሆን ኖሮ፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ መከራን መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኀጢአትን ለማስወገድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገልጧል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:8

“እላችኋለሁ፤ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ፣ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:6

እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ፣ “ጌታ ሆይ፤ የእስራኤልን መንግሥት መልሰህ የምታቋቁምበት ጊዜው አሁን ነውን?” ብለው ጠየቁት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 110:2

እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤ “አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:21

በርሱም አማካይነት፣ ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ፤ ስለዚህ እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:9

“ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:5-7

መልአኩም ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ ዐውቃለሁና፤ እርሱ በዚህ የለም፤ እንደ ተናገረው ተነሥቷል፤ ኑና ተኝቶበት የነበረውን ቦታ እዩ። አሁንም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ፣ ‘ከሙታን ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ በዚያ ታዩታላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው። እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ!”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 6:20

ይህም ስፍራ ኢየሱስ ስለ እኛ ቀድሞ የገባበት ነው። እርሱም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:21-23

የተቀመጠውም ከግዛትና ከሥልጣን፣ ከኀይልና ከጌትነት እንዲሁም በአሁኑ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚቻለው ስም ሁሉ በላይ ነው። እግዚአብሔርም ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም በማንኛውም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾመው። እርሷም ሁሉን ነገር በሁሉም ረገድ የሚሞላው፣ የርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 93:1

እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 4:4-5

ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:4

ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:20

የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣ፣ እውነተኛ የሆነውን እርሱን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነተኛ በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አለን። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 47:7-8

እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት። እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሧል፤ እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:3

ከሕማማቱም በኋላ ራሱ ቀርቦ ሕያው መሆኑን፣ ለእነዚሁ በብዙ ማስረጃ እያረጋገጠላቸው አርባ ቀንም ዐልፎ ዐልፎ እየታያቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:19

ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:12-13

ይህኛው ካህን ግን ስለ ኀጢአት አንዱን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጠላቶቹ የእግሩ መረገጫ እስኪሆኑ ድረስ ይጠብቃል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:10

እናንተም የገዥነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሙሉ ሆናችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 15:12

ኢሳይያስም እንዲሁ፣ “በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣ የእሴይ ሥር ይመጣል፤ በርሱም ሕዝቦች ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 3:21

እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋራ በርሱ ዙፋን ላይ እንደ ተቀመጥሁ፣ ድል የሚነሣውንም ከእኔ ጋራ በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚኦ ኢየሱስ ሆይ በሕይወቴ ውስጥ እንዴት መልካም ነህ! ጠፍቼ ሳለሁ አንተ አገኘኸኝ፤ ስለዚህ አመሰግንሃለሁ። በእንጨት ላይ ስለፈሰሰው ደምህ ኃጢአቴ ይቅር ስለተባለ አመሰግንሃለሁ። ሀሳብህ መልካም እንደሆነና ለሰው ልጆች ያለህ ዕቅድ መልካም እንደሆነ አውቃለሁ፤ ስለዚህ አመሰግንሃለሁ። አንተን ማግኘቴ እንዴት ድንቅ ነው! በሕይወቴ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ብቻዬን ስላላስቀረኸኝ አመሰግንሃለሁ። ታጋሽ ነህ፤ ሁልጊዜም ፍቅርህን አሳይተኸኛል። በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጠህ ስለ እኔ ስለምትማልድ አመሰግንሃለሁ። የመንፈስ ቅዱስን ውብ ሕብረት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። እናንተን ባላገኝ ኖሮ ሕይወቴ ባዶ ትሆን ነበር። ላደረግኸው ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ወደፊትም ለምታደርግልኝ ነገር አመሰግንሃለሁ። አሁን ለጠራኸኝ ዓላማ እንድኖር እርዳኝ። ከቃልህ እንዳልርቅ ጠብቀኝ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በፊትህ እንድኖርና ፈቃድህን እንዳደርግ እርዳኝ። አንተን ለሚያስፈልገው ዓለም ምሳሌ እንድሆን እፈልጋለሁ። ለጠፉት የክርስቶስን ወንጌል እንድሰብክና እነርሱም እንዲድኑ እፈልጋለሁ። እግዚኦ ሆይ፥ ድፍረትህን ስጠኝ፤ አንተ ሁሉን እንደሰጠኸኝ ሁሉ እኔም ሁሉን እንድሰጥ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም፣ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች