Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


105 ጥቅሶች፡ የክርስቶስ አምላክነት

105 ጥቅሶች፡ የክርስቶስ አምላክነት

ብዙ ጊዜ፣ ኢየሱስ እግዚአብሔር ብቻ የማድረግና የመናገር መብት ያለውን ነገር አድርጎና ተናግሯል። እንዲሁም፣ አምላክነቱን የሚያሳይ በሆነ መንገድ ስለራሱ ተናግሯል።

ለእርሱም ግዛት፣ ክብርና መንግሥት ተሰጠው፤ ሕዝቦች፣ አሕዛብና ቋንቋዎች ሁሉ እንዲያመልኩት፤ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ሲሆን አያልፍም፤ መንግሥቱም ፈጽሞ አይጠፋም።

በዳንኤል መጽሐፍ ላይ «በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ በሰማይ ደመናት የሰው ልጅ የሚመስል መጣ፤ ወደ አረጋዊው ቀረበ፤ ወደ እርሱም አቀረቡት። ግዛትም፣ ክብርም፣ መንግሥትም ተሰጠው፤ ሕዝቦች፣ አሕዛብና ቋንቋዎች ሁሉ እንዲያመልኩት፤ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ሲሆን አያልፍም፤ መንግሥቱም ፈጽሞ አይጠፋም» (ዳንኤል 7:13-14) ተብሎ ተጽፏል።

በዚህ የዳንኤል ራእይ ውስጥ፣ ኢየሱስ ራሱን የሰው ልጅ እንደሆነ ገልጿል፤ የማያልቅ የዘላለም ግዛት የተሰጠው እርሱ ነው። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነና ለዘላለም እንደሚነግሥ ነው። ይህንን በማሰብ ተባርከህ።


ቈላስይስ 2:9

የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በርሱ ይኖራልና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 8:58

ኢየሱስም፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 20:28

ቶማስም፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 1:1

በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋራ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 14:33

ከዚያም በጀልባው ውስጥ የነበሩት፣ “በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:6

ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:30

እኔና አብ አንድ ነን።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 2:2

“የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” ሲሉ ጠየቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:38

የማደርገው ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ እኔም በአብ እንዳለሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ታምራቱን እመኑ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 1:14

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:9

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋራ ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ፣ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:9

ወዲያው ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:8

ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤ “አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 5:18

እንግዲህ አይሁድ፣ ኢየሱስ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቱ በማድረግ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር እኩል በማድረጉ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉት ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 1:23

“እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ” ማለት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:18

ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት ቀርቦ እንዲህም አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 1:35

መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፤ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ የሚወለደው ቅዱሱ ሕፃን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 2:11

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:3-4

ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ሆነ፣ ስም አጥፊዎች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞችና ትምክሕተኞች ናቸው፤ ክፋትን የሚሠሩበትን መንገድ ያውጠነጥናሉ፤ ለወላጆቻቸው አይታዘዙም። የማያስተውሉ፣ ውል የሚያፈርሱ፣ ርኅራኄ የሌላቸውና ጨካኞች ናቸው። ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል የሚለውን ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ። በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በኀይል ስለ ተገለጠው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 9:5

አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው! አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:4

የእግዚአብሔር አምሳል የሆነውን የክርስቶስ፣ የክብሩን ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን ሰዎች ልቡና አሳውሯል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 4:4

ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:20-21

ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየው ነው። የተቀመጠውም ከግዛትና ከሥልጣን፣ ከኀይልና ከጌትነት እንዲሁም በአሁኑ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚቻለው ስም ሁሉ በላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:5-7

በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋራ መተካከልን ሊለቅቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:15

እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:19

እግዚአብሔርም ሙላቱ ሁሉ በርሱ ይሆን ዘንድ ወድዷልና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 3:16

የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱ በሥጋ ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:1-3

እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ፣ ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤ እንደ ልብስም ይለወጣሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።” እግዚአብሔር፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው? መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን? በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን። እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:14

እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:20

የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣ፣ እውነተኛ የሆነውን እርሱን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነተኛ በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አለን። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 1:8

“ያለውና የነበረው፣ የሚመጣውም፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 22:13

አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 16:16

ስምዖን ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት መለሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 6:51

ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 11:25

ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:6

ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ከቤተ መቅደስ የሚበልጥ በዚህ አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 14:61-62

ኢየሱስ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም። ሊቀ ካህናቱም እንደ ገና፣ “የቡሩኩ ልጅ፣ ክርስቶስ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አዎን ነኝ፤ የሰው ልጅ በኀያሉ ቀኝ ሲቀመጥ፣ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 9:35

ከደመናውም ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 10:22

“ሁሉም ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ደግሞም ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፤ አብ ማን እንደ ሆነም ከወልድ በቀር፣ ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅደው በቀር የሚያውቅ የለም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 3:16

በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 5:22

አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:6

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:9

“ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 8:6

ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከርሱ የሆነ፣ እኛም ለርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ደግሞም ሁሉም ነገር በርሱ አማካይነት የሆነ፣ እኛም በርሱ አማካይነት የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 12:3

ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ የሚናገር፣ “ኢየሱስ የተረገመ ነው” የሚል የለም፤ እንደዚሁም በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር፣ ማንም “ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚል እንደሌለ እነግራችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:19

እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋራ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 2:20

ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 3:20-21

እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው እንደ ኀይሉ መጠን፣ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፣ በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በዘመናት ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለርሱ ክብር ይሁን! አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:1

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋራ ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን ፈልጉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:4

በሰው ዘንድ ወደ ተናቀው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደዚህ ሕያው ድንጋይ እየቀረባችሁ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 1:2

ይህም ሕይወት ተገለጠ፤ እኛም አይተናል፤ እንመሰክራለንም። ከአብ ዘንድ የነበረውን፣ ለእኛም የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት እንነግራችኋለን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:2

የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 4:12

ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 16:31

እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:16

በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 7:3

አባትና እናት ወይም የትውልድ ሐረግ የለውም፤ ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:12

ይህኛው ካህን ግን ስለ ኀጢአት አንዱን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 2:5

አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ መካከለኛ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:13

ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 5:12

በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ዘመሩ፤ “የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፣ ጥበብና ብርታት፣ ክብርና ሞገስ፣ ምስጋናም፣ ሊቀበል ይገባዋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 19:16

በልብሱና በጭኑ ላይ እንዲህ የሚል ስም ተጽፏል፤ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶችም ጌታ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 2:11

ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 17:5

እርሱ እየተናገረ ሳለ፣ ብሩህ ደመና ሸፈናቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ ተሰማ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:19

ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 1:1

የእግዚአብሔር ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 9:7

ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “ይህ የምወድደው ልጄ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 4:41

አጋንንትም ደግሞ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” እያሉና እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እርሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም ያውቁ ስለ ነበር፣ አንዳች እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 12:41

ኢሳይያስ ይህን ያለው የኢየሱስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እርሱም ተናገረ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 17:5

እንግዲህ አባት ሆይ፤ ዓለም ሳይፈጠር ከአንተ ጋራ በነበረኝ ክብር በአንተ ዘንድ አክብረኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 17:24

“አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ፣ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:31-32

ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል? ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከርሱ ጋራ እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 13:14

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 1:3

ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:18

ሁላችንም በርሱ አማካይነት በአንዱ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:19

አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:27

ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደ ሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:3

የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የሚገኘው በርሱ ዘንድ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 1:10

ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 1:1

በአዳኛችን በእግዚአብሔር፣ ተስፋችንም በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 1:4

በምንጋራው እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ፣ ከአዳኛችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 3:1

እንግዲህ የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፤ የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 11:6

ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሠኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:3

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:23

ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድን የሚያምን ሁሉ አብም አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:11-12

ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 1:8

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:36

“እንግዲህ፣ እግዚአብሔር ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን፣ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ ይረዳ!”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 10:42

ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታንም ላይ እንዲፈርድ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን እንድንመሰክር እርሱ ራሱ አዘዘን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:10

የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከርሱ ጋራ ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:23

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 2:9

ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:57

ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:26

ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:7

በርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአት ይቅርታ አገኘን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:3-4

ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋራ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰውሯልና፤ ሕይወታችሁ የሆነው ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም በዚያ ጊዜ ከርሱ ጋራ በክብር ትገለጣላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:14-15

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ይህን ትእዛዝ ያለ ዕድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ እንድትጠብቅ ነው፤ ያም መገለጥ፣ የተባረከውና ብቻውን ገዥ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ የሚያሳየው ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:8

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:10

በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላላወቀው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:15

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምኖ በሚመሰክር ሁሉ፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 7:10

በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ጮኹ፤ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው፣ የአምላካችንና የበጉ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 11:15

ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 22:20

እነዚህን ነገሮች የሚመሰክረው፣ “አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:36

ታዲያ፣ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ለራሱ ለይቶ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን፣ ‘ተሳድበሃል’ ብላችሁ ለምን ትወነጅሉኛላችሁ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታላቅና ድንቅ ነህ፤ በግርማና በሥልጣን ዙፋን ላይ የተቀመጥክ አንተ ልዑል ነህ፤ በሁሉም ሥራህ ፍጹም ነህ። የተወደድክ ኢየሱስ ሆይ፥ ወደ አንተ እቀርባለሁ፤ ክብር፥ ኃይልና ግዛት የአንተ ብቻ ነውና። በመገኘትህ ሙላኝ፤ መንፈስ ቅዱስህም በሕይወቴ ይገለጥ። በሄድኩበት ሁሉ እምነትህንና ታዛዥነትህን እንድመስል እርዳኝ። የመንፈስ ቅዱስህ ኃይልና መገኘት ቃልህን ከአፌ በሚሰሙት ሕይወት ውስጥ በግልጽ ይታይ። ቃልህ «በታንኳይቱ የነበሩትም ሰገዱለትና። በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ አሉት» ይላል። ኢየሱስ ሆይ፥ አንተ እንደ ተጓዝክ፥ በሽተኞችን እየፈወስክ፥ እስረኞችን እያስፈታህ፥ የተጨቆኑትንም ሁሉ እየረዳህ እንድጓዝ አስተምረኝ። ከጨለማ ሥልጣን አውጥተኸኛል። ኢየሱስ ሆይ፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል መካከለኛ ነህ። ስለ ፍቅርህ ስለ እኛ ሲል ራስህን ሰጥተህ ስለ ኃጢአታችን ታላቅ ዋጋ ስለ ከፈልክልን አመሰግንሃለሁ። ፈጽሞ ስላልተውከኝና ሁልጊዜ ስለምትፈልገኝ አመሰግንሃለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች