Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


108 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ስለ ዝሙት

108 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ስለ ዝሙት

በሮሜ ሰዎች 13:13-14 ላይ እንደተጻፈው፣ ጨለማን የሚመስሉ ሥራዎችን እንደ ዘፈን፣ ስካር፣ ዝሙት፣ ፍትወት፣ ክርክርና ቅናት ራቅ ብለን በአግባቡ እንድንኖር ተመክረናል። በምትኩስ ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንለብስና ከሥጋዊ ምኞት እንድንርቅ ይነግረናል።

ወሲብ በእግዚአብሔር የተፈጠረው በጋብቻ ውስጥ ለመደሰት ነው። የእግዚአብሔርን የመጀመሪያ ፍጹምነት የሚያንጸባርቅ ሲሆን ባለባቶች በአንድነታቸው ፍቅርን ሙሉ በሙሉ እንዲለማመዱ ያስችላቸዋል። ነገር ግን በዚህ በተዛባና በበሰበሰ ዓለም ውስጥ ብዙዎች ከትክክለኛው መንገድ ወጥተው ለሥጋዊ ምኞታቸው ተሸንፈው ኃጢአትን እየሠሩ ነው።

በተለይ ፍትወት ብዙ ቤተሰቦችን እያፈረሰ ነው። በዚህ ኃጢአት የተጠመዱ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና ሕግጋት በመተላለፍ የሚያደርጉት ድርጊት ምን ያህል ከባድ መዘዝ እንዳለው አያስተውሉም።

ስለዚህ ስለ ድርጊታችን ማሰብ፣ ንስሐ መግባትና ወደ ትክክለኛው ጎዳና የሚመልሰንን የእግዚአብሔርን ምሕረት መፈለግ በጣም አስፈላጊ ነው። ልባችን በነጻነት ለመኖር መፈለግ አለበት። ይህን ስናደርግ፣ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ ይሠራል፣ ድክመታችንን ለመቋቋም ብርታት ይሰጠናል፣ እና ሁልጊዜም ይደግፈናል።


ያዕቆብ 1:13-15

ማንም ሲፈተን፣ “እግዚአብሔር ፈተነኝ” አይበል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንም፤ እርሱም ማንንም አይፈትንም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:28

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ሴትን በምኞት ዐይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከርሷ ጋራ አመንዝሯል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 6:18-19

ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል። ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 6:18-20

ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል። ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ እንግዲያው፣ በትንሹ ነገር ላይ ለመፍረድ አትበቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:16

ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:16-17

እንግዲህ በመንፈስ ኑሩ እላለሁ፤ የሥጋንም ምኞት አትፈጽሙም። ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን፣ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን ይመኛልና፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚጋጩ፣ የምትፈልጉትን አታደርጉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 31:1

“ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ ከዐይኔ ጋራ ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 7:5

ኀጢአተኛ በሆነ ተፈጥሮ ቍጥጥር ሥር ሳለን፣ ለሞት ፍሬ እንድናፈራ በሕግ የተቀሰቀሰው የኀጢአት መሻት በሥጋችን ላይ ይሠራ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:14-15

ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:3

አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:5

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞትና አምልኮተ ጣዖት የሆነው መጐምጀት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:22

ቀድሞ ስለ ነበራችሁበት ሕይወትም፣ በሚያታልል ምኞቱ የጐደፈውን አሮጌ ሰውነታችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:24

የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋራ ሰቅለውታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:3

ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሣ፤ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 4:4-5

ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤ ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:22

ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋራም ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከታተል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:12

ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:13

በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:11

ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:23-25

እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን፣ የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤ እርሷም ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ ልዝብ አንደበት ካላት ባዕድ ሴት ትጠብቅሃለች። ውበቷን በልብህ አትመኝ፤ በዐይኗም አትጠመድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:25-26

ውበቷን በልብህ አትመኝ፤ በዐይኗም አትጠመድ። ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:5-6

እንደ ሥጋ የሚኖሩ ሐሳባቸውን በሥጋ ፍላጎት ላይ ያሳርፋሉ፤ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን ሐሳባቸውን በመንፈስ ፍላጎት ላይ ያደርጋሉ። የሥጋን ነገር ማሰብ ሞት ነው፤ የመንፈስን ነገር ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 4:3-5

የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤ ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤ ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:18-19

ከንቱ ቃል እየደረደሩ በስሕተት ከሚኖሩት መካከል አምልጠው የመጡትን ሰዎች በሴሰኛ ሥጋዊ ምኞት በማባበል ያታልላሉና። እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሮች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ነገር ባሪያ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 7:2

ነገር ግን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:12-13

ስለዚህ ክፉ መሻቱን ትፈጽሙ ዘንድ በሟች ሥጋችሁ ላይ ኀጢአት እንዲነግሥበት አታድርጉ። ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 15:19

ክፉ ሐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ማመንዘር፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ በሐሰት መመስከርና ስም ማጕደፍ ከልብ ይመነጫሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:22

ከማንኛውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:12

ምክንያቱም አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው ይወለዳሉ፤ ሌሎች በሰው እጅ ተሰልበው ጃንደረባ ይሆናሉ፤ ደግሞም ለመንግሥተ ሰማይ ሲሉ ራሳቸውን ጃንደረባ የሚያደርጉ አሉ። ይህን መቀበል የሚችል ይቀበል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 7:25-27

ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ፤ ወደ ስሕተት ጐዳናዋም አትግቡ። አዋርዳ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤ የገደለቻቸውም ስፍር ቍጥር የላቸውም። ቤቷ ወደ ሲኦል የሚወስድ፣ ወደ ሞት ማደሪያም የሚያወርድ ጐዳና ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:1

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:13

እንደ ሥጋ ብትኖሩ ትሞታላችሁና፤ ክፉ የሆነውን የሥጋ ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ ግን፣ በሕይወት ትኖራላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:22-24

ቀድሞ ስለ ነበራችሁበት ሕይወትም፣ በሚያታልል ምኞቱ የጐደፈውን አሮጌ ሰውነታችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ ደግሞም በአእምሯችሁ መንፈስ እንድትታደሱ፣ እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:13-14

በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን። ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:37

ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤ በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:23

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:1-2

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ። ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ። በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ። ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ። የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ። እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ በመስማማት ኑሩ። ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋራ ዐብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ። ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ። ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 101:3

በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 6:11-12

የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ። ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋራ ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋራ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:20-23

ለዚህ ዓለም መርሕ ከክርስቶስ ጋራ ከሞታችሁ፣ ታዲያ በዚህ ዓለም እንደሚኖር ለምን ትገዙላቸዋላችሁ? “አትያዝ! አትቅመስ! አትንካ!” እንደሚሉት ዐይነት፣ እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ ጠፊ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:4

ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ይከበር፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአመንዝሮችና በሴሰኞች ሁሉ ላይ ይፈርዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:13

ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉው አድነን እንጂ፤ መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም ለዘላለሙ ያንተ ነውና፤ አሜን። ’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:8

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:7-8

እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል። ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:31-32

መልኩ ቀይ ሆኖ፣ በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ ሰተት ብሎ በሚወርድበትም ጊዜ፣ ወደ ወይን ጠጅ ትክ ብለህ አትመልከት። በመጨረሻው እንደ እባብ ይነድፋል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:3

በርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 10:5

በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:41

ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:27

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር፣ ሰውነቴን እየጐሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 7:18

በእኔ፣ ማለትም ኀጢአተኛ በሆነው ተፈጥሮዬ ውስጥ ምንም በጎ ነገር እንደማይኖር ዐውቃለሁ፤ በጎ የሆነውን የማድረግ ምኞት አለኝ፤ ነገር ግን ልፈጽመው አልችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:10

አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:33-34

አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኛነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።” ወደ ሰከነ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 5:3-5

የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ያንጠባጥባልና፤ አንደበቷም ከቅቤ ይለሰልሳል፤ በመጨረሻ ግን እንደ እሬት ትመርራለች፤ ሁለት አፍ እንዳለውም ስል ሰይፍ ትሆናለች። እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፤ ርምጃዎቿም በቀጥታ ወደ ሲኦል ያመራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:14

ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:12

በፈተና የሚጸና ሰው ብፁዕ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወድዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:1-2

እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንሁ እኔ፣ ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ወደ ታች የወረደውም፣ መላውን ፍጥረተ ዓለም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው እርሱ ራሱ ነው። አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይኸውም የክርስቶስ አካል ይገነባ ዘንድ፣ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት ሲሆን፣ ይህም የሚሆነው፣ ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኘው አንድነት በመምጣትና ሙሉ ሰው በመሆን፣ በክርስቶስ ወዳለው ፍጹምነት ደረጃ እስከምንደርስ ነው። ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም። ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው። ከርሱም የተነሣ፣ አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፣ እያንዳንዱ ክፍል የራሱን ሥራ እያከናወነ በፍቅር ያድጋል፤ ራሱንም ያንጻል። ስለዚህ ይህን እነግራችኋለሁ፤ በጌታም ዐደራ እላለሁ፤ በአስተሳሰባቸው ከንቱነት እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ልትመላለሱ አይገባም። እነርሱ ከልባቸው መደንደን የተነሣ ስለማያስተውሉ ልቡናቸው ጨልሟል፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ተለይተዋል። ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ በማይረካ ምኞት፣ በርኩሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመኖር ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል። ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:4

ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ፣ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:20

ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:6-7

ከእንግዲህ የኀጢአት ባሮች እንዳንሆን፣ የኀጢአት ሰውነት እንዲሻር አሮጌው ሰዋችን ከርሱ ጋራ እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ ምክንያቱም የሞተ ከኀጢአት ነጻ ወጥቷል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:13

እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:4

ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሸንፈውም እምነታችን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 23:3

ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:12

የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 16:24-25

ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነገር ግን ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ያድናታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:32

የሚያመነዝር ሰው ግን ልበ ቢስ ነው፤ እንዲህ የሚያደርግ ሁሉ ራሱን ያጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ ይህን ዕወቅ። አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዐላማዬን፣ እምነቴን፣ ትዕግሥቴን፣ ፍቅሬንና ጽናቴን ሁሉ ታውቃለህ፤ ስደቴንና መከራዬን፣ በአንጾኪያና በኢቆንዮን፣ በልስጥራንም የደረሰብኝን ሁሉ፣ የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከእነዚህ ሁሉ አዳነኝ። በርግጥም በክርስቶስ ኢየሱስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መኖር የሚወድዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። ክፉዎችና አታላዮች ግን እየሳቱና እያሳቱ፣ በክፋትም ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ። አንተ ግን በተማርኸውና በተረዳኸው ጽና፤ ይህን ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። ሰዎች ራሳቸውን የሚወድዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወድዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኵሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድዱ ይሆናሉና። ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:14

ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤ ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 7:1

እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፤ ይህ የተስፋ ቃል ስላለን፣ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:15-16

ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤ ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፏል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:6

ቅኖችን ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፤ ወስላቶች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:12

ሌሊቱ ሊያልፍ፣ ቀኑም ሊጀምር ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን፣ የብርሃንን ጦር ዕቃ እንልበስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 4:4

ኢየሱስም፣ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:26

እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 4:7

እግዚአብሔር በቅድስና እንድንመላለስ እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 1:9

ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 33:15-16

በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣ ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 13:4-5

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 11:34-36

የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ናት፤ ዐይንህ ጤናማ ስትሆን መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል፤ ዐይንህ ታማሚ ከሆነች ግን መላ ሰውነትህ የጨለመ ይሆናል። ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። እንግዲህ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነና የጨለመ የሰውነት ክፍል ከሌለበት፣ የሰውነትህ ሁለንተና መብራት በወገግታው ያበራልህ ያህል ይደምቃል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:26-27

የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 3:18

ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ። ለርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን! አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 4:12

ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:29-30

ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል። “በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና። ቀኝ እጅህ ቢያሰናክልህ ቈርጠህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:17

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:13

ስለዚህ እርስ በርሳችን፣ አንዱ በሌላው ላይ ከመፍረድ እንቈጠብ፤ በዚህ ፈንታ ግን በወንድምህ መንገድ ላይ የማሰናከያ ድንጋይ ወይም ወጥመድ እንዳታስቀምጥ ቍርጥ ሐሳብ አድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 14:20

ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ፤ በአስተሳሰባችሁ ግን ጕልማሶች ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:12-14

እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤ እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ። በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:32

ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:9

እላችኋለሁ፤ ዝሙት ፈጽማ እስካልተገኘች ድረስ፣ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሴት የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል፤ እርሷንም አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 3:16-17

በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤ ይኸውም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲያድር ነው። ደግሞም ሥር ሰድዳችሁ፣ በፍቅር ታንጻችሁ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 141:4

ከዐመፀኞች ጋራ፣ በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣ ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤ ከድግሳቸውም አልቋደስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:16-17

ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤ መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 3:17

ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ ዕሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና ግብዝነት የሌለባት ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:4

ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:27

ወደ ቀኝ ወደ ግራ አትበል፤ እግርህን ከክፉ ጠብቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:13-14

“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 6:13

ደግሞም፣ “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 1:7

እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር፣ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሀት መንፈስ አልሰጠንምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:5

ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:1-2

እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፣ ማታለልን ሁሉ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ። ቀድሞ የርሱ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል። ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ። ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ። ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለሥልጣን ሁሉ ተገዙ፤ የበላይ ባለሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣትና በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤ ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እንደ እግዚአብሔር ባሮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት። ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ። እናንተ አገልጋዮች ሆይ፤ ለደጎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን፣ ለክፉዎችም በፍጹም አክብሮት ታዘዙ። ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል። በድነታችሁ እንድታድጉ፣ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:12-14

ይህን ሁሉ አግኝቻለሁ ወይም ፍጹም ሆኛለሁ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ እኔን የራሱ ያደረገበትን ያን፣ እኔም የራሴ ለማድረግ እጣጣራለሁ። ወንድሞች ሆይ፤ እኔ ገና እንደ ያዝሁት አድርጌ ራሴን አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ከኋላዬ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ላይ ስለ ጠራኝ፣ ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:18

ለእኛ ደግሞ ጸልዩልን። በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚናፍቅ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን ርግጠኞች ነን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህ ወሰን የለውም፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይገባል። በዚህች ቀን ቅድስናህን አመልካለሁ፤ ምሕረትህን በሕይወቴ ላይ ስታሳይ አመሰግንሃለሁ። ከእኔ ጋር ስለሆንክ፣ ደሜን ስለኔ ስለማፍሰስህ እና በውድቀቴና በድካሜ ሁሉ መልካም ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። አቤቱ፥ በየዕለቱ ብዙ ስህተቶችን ስለማደርግና ላንተ ታማኝ መሆን ስለምፈልግ ራሴን ላንተ አስገዛለሁ፤ አንተ ያስፈልገኛል። ቀጥ ያለና ደስ የሚያሰኝ ልብ እንዲኖረኝ እፈልጋለለሁ፤ ለዚህም ነው ወደ አንተ የምመጣው። ሕይወቴን እንድትለውጥልኝ ከልቤ እሻለሁ። ቤተሰቤን ማጣት አልፈልግም፤ የሥጋ ምኞቴ ሰውነቴን መግዛቱን እንዲያቆም እፈልጋለሁ። እባክህ እርዳኝ፤ ነፍሴን ከዝሙት አርቅልኝ። ዛሬ ስሜቴንና ስሜቴን ሁሉ በፊትህ አኖራለሁ። መንፈስ ቅዱስህ ይለውጠኝ፤ የክርስቶስ ደም ከክፋቴ ሁሉ ያጥረኝ። አቤቱ፥ ቀድሰኝ፤ ወደ ፊት ለመራመድ ብርታት ስጠኝ፤ በፈተና እንዳልወድቅ እርዳኝ። ለሁሉም ነገር አመሰግንሃለሁ፥ የተወደድከው አምላኬ። እኔ በእጅህ ነኝ። አንተ ጽኑ ዐለቴ፥ መጠጊያዬና ተስፋዬ እንደሆንክ አምናለሁ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም። በኢየሱስ ስም፥ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች