Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


136 የፈጣሪ ቃላት፡ የዓለም አፈጣጠር

136 የፈጣሪ ቃላት፡ የዓለም አፈጣጠር
ዘፍጥረት 1:1

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:1

ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:28

አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው። አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 33:6-9

በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤ በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት። የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል። ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤ በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ። እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:16

ሁሉ ነገር በርሱ ተፈጥሯል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በርሱና ለርሱ ተፈጥሯል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:20

ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:26-27

እግዚአብሔር፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:24-25

እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች። ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸውም የሚርመሰመሱ ፍጥረታት በውስጧ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 38:4-6

“ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? በርግጥ የምታስተውል ከሆንህ ንገረኝ። እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ። ልጆቿ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣ ምግብ ዐጥተው ሲንከራተቱ፣ ለቍራ መብልን የሚሰጥ ማን ነው? ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ? በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ? የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 45:18

ሰማያትን የፈጠረ፣ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣ የመሠረታት፣ የሰው መኖሪያ እንጂ፣ ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:31

እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ። መሸ፤ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 8:3-4

የጣቶችህን ሥራ፣ ሰማያትህን ስመለከት፣ በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣ በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 139:13-14

አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤ በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 11:3

ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:5

ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤ ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 65:17

“እነሆ፤ እኔ፣ አዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:7

እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:1-2

ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ ክብርንና ግርማን ለብሰሃል። ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤ በተራሮችም መካከል ይፈስሳሉ፤ የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ። የሰማይ ወፎች ጐጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤ በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ። ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች። ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤ የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል። ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤ ወፎች ጐጇቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች። ረዣዥሙ ተራራ የዋሊያ መኖሪያ፣ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው። ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች። ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 3:11

ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ አምላክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 26:7

የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤ ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 95:4-5

የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የርሱ ናቸው። እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:3

እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:36

ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ ነውና፤ ለርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን! አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:17

እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በርሱ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 148:1-5

ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በላይ በአርያም አመስግኑት። የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣ በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበርሩ ወፎችም፣ የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣ ወጣት ወንዶችና ደናግል፣ አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት። ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ። እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ። መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት። ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት። እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:14-19

ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣ ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው። ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:5

ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 42:5

ሰማያትን የፈጠረ፣ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ያበጀ፣ ለሕዝቧ እስትንፋስን፣ ለሚኖሩባትም ሕይወትን የሚሰጥ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:20-22

እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 136:5-9

ሰማያትን በብልኀት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ምድርን በውሃ ላይ የዘረጋ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ፀሓይ በቀን እንዲሠለጥን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 33:4

የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ የሁሉን ቻዩ አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 48:13

ምድርን የመሠረተች የእኔው እጅ ናት፤ ሰማያትን የዘረጋችም ቀኝ እጄ ናት፤ በምጠራቸው ጊዜ፣ ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:25-26

ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸውም የሚርመሰመሱ ፍጥረታት በውስጧ አሉ። መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:19-20

እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራውን በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ይሠራ ከነበረው ሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። ስለዚህ አዳም ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 102:25

አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 24:1-2

ምድርና በርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤ ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው። ሴላ እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤ በውሆችም ላይ አጽንቷታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 147:4-5

የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል። ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 11:5

የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የአምላክን ሥራ ማስተዋል አትችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:12

ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ ማነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:24-25

እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:90

ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ሁሉ ይኖራል፤ ምድርን መሠረትሃት፤ እርሷም ጸንታ ትኖራለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:19-20

እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤ ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል። በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤ ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 111:2

የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 4:17

ይህም “የብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው፤ እርሱም ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥ፣ ያልነበረውንም እንደ ነበረ በሚያደርግ፣ ባመነበት አምላክ ፊት አባታችን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:29-30

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በምድር ላይ ያሉትን ዘር የሚሰጡ ተክሎችን ሁሉ፣ በፍሬአቸው ውስጥ ዘር ያለባቸውን ዛፎች ሁሉ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ ሰጥቻችኋለሁ። እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:69

መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 139:15

እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፤ በምድር ጥልቀት ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 26:4

በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:10

ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 8:1-2

እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሏል። ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ ምስጋናን አዘጋጀህ፤ ከጠላትህ የተነሣ፣ ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:5

እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን”፣ ጨለማውን “ሌሊት” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:27-29

ሰማያትን በዘረጋ ጊዜ፣ በውቅያኖስ ላይ የአድማስ ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፤ ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሠረተ ጊዜ፣ ለባሕር ድንበርን በከለለ ጊዜ፣ ውሆችም የርሱን ትእዛዝ እንዳያልፉ፣ የምድርንም መሠረቶች ወሰን ባበጀ ጊዜ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 93:1

እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:7

ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 12:12-13

ጥበብ ያለው በአረጋውያን ዘንድ አይደለምን? ማስተዋልስ ረዥም ዕድሜ ባላቸው ዘንድ አይገኝምን? “ጥበብና ኀይል የእግዚአብሔር ናቸው፤ ምክርና ማስተዋልም በርሱ ዘንድ ይገኛሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:3-4

ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም። ያም ሆኖ ድምፃቸው በምድር ሁሉ፣ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል። እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሏል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:7

በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣ ለክብሬ የፈጠርሁትን፣ ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:4

እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 66:4

ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤ በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ ለስምህም ይዘምራሉ።” ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 38:22-23

“ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃልን? የዐመዳዩንስ ማከማቻ አይተሃልን? ይኸውም ለመከራ ጊዜ፣ ለጦርነትና ለውጊያ ቀን ያስቀመጥሁት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:14

ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:22

እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 96:11-13

ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤ መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤ እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይፈርዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:8

እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:1-3

ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ። ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣ እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል። ደግሞም አገልጋይህ በርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤ እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው። ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል? ከተሰወረ በደል አንጻኝ። ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤ እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤ ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤ ከታላቅ በደልም እነጻለሁ። ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን። ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤ ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 51:6

ዐይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሡ፤ ወደ ታች ወደ ምድርም ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፤ ምድር እንደ ልብስ ታረጃለች፤ ነዋሪዎቿም እንደ ዐሸን ፈጥነው ይረግፋሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘላለም ይኖራል፤ ጽድቄም መጨረሻ የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 33:9

እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 139:16

ዐይኖችህ ገና ያልተበጀውን አካሌን አዩ፤ ለእኔ የተወሰኑልኝም ዘመናት፣ ገና አንዳቸው ወደ መኖር ሳይመጡ፣ በመጽሐፍ ተመዘገቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:26

እግዚአብሔር፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:16

ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 3:4

እያንዳንዱ ቤት የራሱ ሠሪ አለው፤ ነገር ግን ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:5-6

ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤ ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ። ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤ እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:22

እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:2

ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 37:14

“ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 148:6

ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤ የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 30:4

ወደ ሰማይ የወጣ፣ የወረደስ ማነው? ነፋስን በእጁ ሰብስቦ የያዘ ማነው? ውሆችንስ በመጐናጸፊያው የጠቀለለ ማነው? የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማነው? ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? የምታውቅ ከሆነ እስኪ ንገረኝ!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:12

ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 103:19

እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቷል፤ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 135:6

በሰማይና በምድር፣ በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሠኘውን ሁሉ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:25-26

ቅዱሱ፣ “ከማን ጋራ ታወዳድሩኛላችሁ? የሚስተካከለኝስ ማን አለ?” ይላል። ዐይናችሁን አንሡ፤ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤ እነዚህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? የከዋክብትን ሰራዊት አንድ በአንድ የሚያወጣቸው፣ በየስማቸው የሚጠራቸው እርሱ ነው። ከኀይሉ ታላቅነትና ከችሎታው ብርታት የተነሣ፣ አንዳቸውም አይጠፉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:8

እግዚአብሔር አምላክ በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:13

መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤ ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 37:6

በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:19

መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:1

በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:1

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ቤት የት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:21

በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:18

ረዣዥሙ ተራራ የዋሊያ መኖሪያ፣ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 39:1-4

“የበረሓ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋሊያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን? ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ? እህልህን እንዲሰበስብልህ፣ በዐውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ ታምነዋለህን? “ሰጎን ክንፎቿን በደስታ ታራግባለች፤ ነገር ግን እንደ ሽመላ ላባዎች ሊሆኑ አይችሉም። ዕንቍላሏን መሬት ላይ ትጥላለች፤ እንዲሞቅም በአሸዋ ውስጥ ትተወዋለች። እግር እንደሚሰብረው፤ የዱር አውሬም እንደሚረግጠው አታስብም። የእርሷ እንዳልሆኑ ሁሉ በልጆቿ ትጨክናለች፤ ድካሟም በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም፤ እግዚአብሔር ጥበብ ነሥቷታልና፤ ማስተዋልንም አልሰጣትም። ለመሸምጠጥም ክንፎቿን ስትዘረጋ፣ በፈረስና በጋላቢው ትሥቃለች። “ለፈረስ ጕልበትን ትሰጠዋለህን? ዐንገቱንስ ጋማ ታለብሰዋለህን? የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደ ሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? እንደ አንበጣ የምታስዘልለው አንተ ነህን? የማንኰራፋቱም ገናናነት አስፈሪ ነው። በጕልበቱ እየተመካ በብርቱ ይጐደፍራል፤ ጦርነት ሊገጥም ይወጣል። ያለ አንዳች ሥጋት፣ በፍርሀት ላይ ይሥቃል፤ ሰይፍ ቢመዘዝበትም ወደ ኋላ አይልም። ከሚብረቀረቀው ጦርና ዐንካሴ ጋራ፣ የፍላጻው ኰረጆ ጐኑ ላይ ይንኳኳል። በወኔ መሬቱን እየጐደፈረ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል። መለከቱ ሲያንባርቅ፣ ‘ዕሠይ’ ይላል፤ የአዛዦችን ጩኸትና የሰራዊቱን ውካታ፣ ጦርነትንም ከሩቅ ያሸትታል። “ጭልፊት የሚበርረው፣ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው፣ በአንተ ጥበብ ነውን? ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ ጐጆውንም በከፍታ ላይ የሚሠራው፣ በአንተ ትእዛዝ ነውን? በገደል ላይ ይኖራል፤ በዚያም ያድራል፤ ምሽጉም የቋጥኝ ጫፍ ነው። እዚያ ሆኖ የሚነጥቀውን ይቃኛል፤ ዐይኑም ከሩቅ አጥርቶ ያያል። ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ ከምጣቸውም ጣር ይገላገላሉ። ጫጩቶቹ ደም ይጠጣሉ፤ እርሱም በድን ካለበት አይታጣም።” ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:19-20

ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው ለእነርሱ ግልጽ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእነርሱ ግልጽ አድርጎታል። ስለዚህ ወንጌል በነቢያቱ በኩል በቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ተሰጠ። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:22

“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:23

ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤ እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:16

እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:89

እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃልህ በሰማይ፣ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 38:31-33

“ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጕም፣ ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን? ማዛሮት የተባለውን የከዋክብት ክምችት በወቅቱ ልታወጣ፣ ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ? የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ? ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 121:2

ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 45:12

ምድርን የሠራሁ እኔ ነኝ፤ ሰውንም በላይዋ ፈጥሬአለሁ፤ እጆቼ ሰማያትን ዘርግተዋል፤ የሰማይንም ሰራዊት አሰማርቻለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:15

እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:9

እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤ ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:19

እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:7

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤ አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:11

እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 111:5

ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:15

የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 33:5

እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍትሕን ይወድዳል፤ ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 24:1

ምድርና በርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:20-21

የምድረ በዳ አራዊት፣ ቀበሮና ጕጕት ያከብሩኛል፤ በምድረ በዳ ውሃ፣ በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና። ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤ ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብ ምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 86:9

ጌታ ሆይ፤ አንተ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ፣ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ፤ ለስምህም ክብር ይሰጣሉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:4

እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:17

እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:26

እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 135:5

እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፣ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:10

እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 67:6

ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር፣ አምላካችን ይባርከናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:13

መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:19

ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:21

ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:73

እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ ትእዛዞችህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:24

እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:28

እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 8:6

በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:8

ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:7-8

በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤ የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ። በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:17

ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:144

ምስክርነትህ ለዘላለም የጽድቅ ምስክርነት ነው፤ በሕይወት እኖር ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:78

እብሪተኞች ያለ ምክንያት በደል አድርሰውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእዛዞችህን አሰላስላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 1:20

እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:22-25

“እግዚአብሔር ከቀድሞ ሥራዎቹ በፊት፣ የተግባሮቹ መጀመሪያ አድርጎ አመጣኝ፤ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ፣ ከጥንት ከዘላለም ተሾምሁ። ከውቅያኖሶች በፊት፣ የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤ ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ ከኰረብቶችም በፊት ተወለድሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:20

ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣ በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:19

እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:16

አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች