Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


107 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ አጸያፊ ድርጊቶች

107 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ አጸያፊ ድርጊቶች

ልቤ ሆይ፣ እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር አስብ። በብሉይ ኪዳን ጣዖትን ማምለክ፣ በሐሰት አማልክት ማመን፣ አስማት መሥራት እንደ ርኩሰት ተቆጥሮ ሕዝቡ እንዲርቅ እግዚአብሔር ደጋግሞ አስጠንቅቋል። እነዚህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ፈቃድና ዕቅድ ውጪ ናቸው። ለምሳሌ ዘዳግም 18፡9-12 ላይ የተለያዩ የአስማትና የጥንቆላ ዓይነቶች በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ርኩሰት እንደሚቆጠሩ ተጽፏል።

በአዲስ ኪዳን ደግሞ ኢየሱስ ስለ ንጽሕናና ቅድስና አስፈላጊነት አስተምሮናል። አንዳንድ ድርጊቶች በእርሱ ዘንድ እንደ ርኩሰት እንደሚቆጠሩ ገልጿል። ማቴዎስ 15፡18-20 ላይ ኢየሱስ ከሰው አፍ የሚወጣው ከልብ ስለሚመነጭ ሰውን እንደሚያረክሰው ተናግሯል። ውሸት፣ ስድብ፣ ክፉ ምግባር ሁሉ ከልብ የሚመነጩ በመሆናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩሰት ናቸው።

እግዚአብሔር በቅድስናና በታዛዥነት እንድንኖር ይፈልጋል። እርሱ የሚጠላውን ነገር ሁሉ እንድንርቅ ይሻል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም በማጥናት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተረድተን እርሱ የሚጠላውን ነገር እንርቃለን። እግዚአብሔር ይርዳን።


ምሳሌ 6:16-19

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦ ትዕቢተኛ ዐይን፣ ሐሰተኛ ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆች፣ ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣ በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 23:18

ለዝሙት ዐዳሪ ሴት ወይም ለወንደቃ የተከፈለውን ዋጋ ለማንኛውም ስእለት አድርገህ ለመስጠት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታምጣ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 16:15

እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በሰዎች ፊት ራሳችሁን የምታጸድቁ ናችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰዎች ዘንድ የከበረ፣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሰ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:1

እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 18:22

“ ‘ከሴት ጋራ እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋራ አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 18:12

እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነውና። ከእነዚህ አስጸያፊ ልምዶች የተነሣም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 20:13

“ ‘አንድ ወንድ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ እንደሚፈጽም ሁሉ ከወንድ ጋራ ቢፈጽም፣ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋልና ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 7:25-26

የአማልክታቸውን ምስሎች በእሳት አቃጥል፤ በላያቸው የሚገኘውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ ለራስህ አታድርግ፤ አለዚያ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆነ ያሰናክልሃል። አስጸያፊ ነገርን ወደ ቤትህ ወይም ወደ ራስህ አታምጣ፤ አለዚያ አንተም እንደ እርሱ ለጥፋት ትዳረጋለህ፤ ፈጽመህ ጥላው፤ ተጸየፈውም፤ ለጥፋት የተለየ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዳንኤል 11:31

“የጦር ሰራዊቱም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 21:27

በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፣ ርኩሰትን የሚያደርግና ውሸትን የሚናገር ሁሉ አይገባባትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 17:1

እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 18:10-12

በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ ወይም መተተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ጠንቋይ ወይም በድግምት የሚጠነቍል፣ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ። እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነውና። ከእነዚህ አስጸያፊ ልምዶች የተነሣም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዳንኤል 12:11

“የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ጥፋትን የሚያመጣው የጥፋት ርኩሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:13-14

ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፣ ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም። የወር መባቻችሁንና በዓላታችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፤ መታገሥም አልቻልሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 22:5

ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ እንዲህ የሚያደርገውን ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ይጸየፈዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 21:8

ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:22

እግዚአብሔር ሐሰተኛ ከንፈርን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ደስ ይለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:26

እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 7:5

እንግዲህ በእነርሱ ላይ የምታደርጉት ይህ ነው፤ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የአሼራ ምስል ዐምዶቻቸውን ቍረጡ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 25:16

አምላክህ እግዚአብሔር እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 20:4-5

በላይ በሰማይ ወይም በታች በምድር ካለው ወይም ከምድር በታች ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ ነገሮች በማናቸውም ዐይነት ምስል ለራስህ ጣዖትን አታብጅ። አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 32:35

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ ይሠዉ ዘንድ በሄኖም ሸለቆ ለበኣል መስገጃ ኰረብቶችን ሠሩ፤ ነገር ግን ይሁዳን ኀጢአት ለማሠራት እንደዚህ ያለውን አስጸያፊ ተግባር እንዲፈጽሙ እኔ አላዘዝሁም፤ ከቶም አላሰብሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 14:24

ከዚያም ይልቅ፣ የቤተ ጣዖት ወንደቃዎች በምድሪቱ ላይ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት አሳድዶ ያስወጣቸው አሕዛብ የፈጸሙትን አስጸያፊ ድርጊት ሁሉ እነዚህም ፈጸሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:15

“እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተነገረው፣ ‘የጥፋት ርኩሰት’ በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፣ አንባቢው ያስተውል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 11:10-13

ነገር ግን በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ሁሉ፣ ከሚንፏቀቁት ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ሌሎች ፍጥረታት መካከል ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ፤ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆኑ ሥጋቸውን አትብሉ፤ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ፤ ክንፍና ቅርፊት የሌለው ማንኛውም በውሃ ውስጥ የሚኖር ፍጡር በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ይሁን። “ ‘ከአዕዋፍ ወገን እነዚህን ትጸየፋላችሁ፤ ጸያፍ ስለ ሆኑም አትብሏቸው፦ ንስር፣ የጥንብ አሞራ፣ ግልገል አንሣ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:3

ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 27:15

“የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራውን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ፣ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:8

እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:5

እግዚአብሔር በልብ የሚታበዩትን ሁሉ ይጸየፋል፤ እነርሱም ከቅጣት እንደማያመልጡ በርግጥ ዕወቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:32

እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 12:31

አምላክህን እግዚአብሔርን በእነርሱ መንገድ ፈጽሞ አታምልክ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን ሲያመልኩ እግዚአብሔር የሚጸየፈውን ሁሉንም ዐይነት ነገር ያደርጋሉና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እንኳ ለአማልክታቸው መሥዋዕት አድርገው ያቃጥላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:15

በደለኛውን ማጽደቅ ሆነ፣ ጻድቁን በደለኛ ማድረግ፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:20

እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 2:11

ይሁዳ አልታመነም፤ በእስራኤልና በኢየሩሳሌምም አስጸያፊ ነገር ተፈጽሟል፤ ይሁዳ የባዕድ አምላክ ሴት ልጅ በማግባት እግዚአብሔር የሚወድደውን መቅደስ አርክሷል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:10

ሁለት ዐይነት ሚዛን፣ ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:50

ኵራተኞች ነበሩ፤ በፊቴ አስጸያፊ ተግባር መፈጸማቸውን ባየሁ ጊዜም አስወገድኋቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:13

እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፤ እኔም ትዕቢትንና እብሪትን፣ ክፉ ጠባይንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 8:6

ደግሞም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ከመቅደሴ ያርቀኝ ዘንድ በዚህ የሚያደርገውን እጅግ አስጸያፊ ነገር ታያለህን? ከዚህም የባሰ አስጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 7:10

ስሜ ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ ትቆሙና “ደኅና ነን” እያላችሁ እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ታደርጋላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:12-15

ምናምንቴና ጨካኝ ሰው፣ ነውረኛ አንደበቱን ይዞ የሚዞር፣ በዐይኑ የሚጠቅስ፣ በእግሩ ምልክት የሚሰጥ፣ በጣቶቹ የሚጠቍም፣ በልቡ ተንኰል ክፋትን የሚያውጠነጥን፣ ምን ጊዜም ጠብ ይጭራል። ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 17:4-5

ሴቲቱም ሐምራዊና ቀይ ልብስ ተጐናጽፋ ነበር፤ ደግሞም በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቈችም አጊጣ ነበር፤ በእጇም የሚያስጸይፍ ነገርና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበትን የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር። በግንባሯም ላይ እንዲህ የሚል የምስጢር ስም ተጽፎ ነበር፤ ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ርኩሰቶች እናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:29

“ ‘ምድሪቱ ወደ ግልሙትና አዘንብላ በርኩሰት እንዳትሞላ፣ ሴት ልጅህ ጋለሞታ ትሆን ዘንድ አታዋርዳት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:24

እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:9

እግዚአብሔር የክፉዎችን መንገድ ይጸየፋል፤ ጽድቅን የሚከታተሉትን ግን ይወድዳቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 18:26-30

እናንተ ግን ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እናንተ የአገር ተወላጆችና በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም አትፈጽሙ። ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች። እናንተም ምድሪቱን ብታረክሷት፣ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም ትተፋችኋለች። “ ‘ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ሰው ሁሉ ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ። በኖራችሁበት በግብጽ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ። ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 5:11

ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ መቅደሴን በረከሱ ምስሎችሽና በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ስላጐደፍሽ፣ ፊቴን ከአንቺ እመልሳለሁ፤ በርኅራኄ አልመለከትሽም፤ አልምርሽም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:9

ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 44:4

እኔም፣ ‘ይህን የምጠላውን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ’ በማለት አገልጋዮቼን ነቢያትን ደጋግሜ ላክሁባቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 23:13

እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ከርኩሰት ኰረብታ በስተ ደቡብ የነበሩትን የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን የርኩሰት አምላክ ለአስታሮት፣ ለሞዓብ ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለካሞሽ፣ ለአሞን ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለሚልኮም ያሠራቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያዎች ንጉሡ አረከሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 28:3

እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ያስወገዳቸውን የአሕዛብን ርኩሰት ተከትሎ፣ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ዐጠነ፤ ወንዶች ልጆቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 18:23

“ ‘ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ በመፈጸም ራስህን አታርክስ። ሴትም ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ራሷን አታቅርብ፤ ይህ አስጸያፊ ምግባር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 44:19

ማንም ቆም ብሎ አላሰበም፤ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ስለሌለው እንዲህ ማለት አልቻለም፤ “ግማሹን በእሳት አቃጥዬዋለሁ፤ በፍሙ እንጀራ ጋግሬበታለሁ፤ ሥጋ ጠብሼበት በልቻለሁ፤ ታዲያ፣ በቀረው እንዴት ጸያፍ ነገር እሠራለሁ? ለግንድስ መስገድ ይገባኛልን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:27

የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 7:20

በውብ ዕንቋቸው ታብየዋል፤ ይህንም አስጸያፊ የጣዖት ምስሎቻቸውንና ርኩስ ቅርጻ ቅርጾችን ለመሥራት ተጠቅመውበታል። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ወደ ርኩሰት እለውጥባቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 3:2

መልካሙን ጠላችሁ፤ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ቈዳ ገፈፋችሁ፤ ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 6:15

ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም፤ ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 8:12

ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በሚቀጡ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:20

ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 9:10

“እስራኤልን ማግኘቴ፣ የወይንን ፍሬ በምድረ በዳ የማግኘት ያህል ነበር፤ አባቶቻችሁንም ማየቴ፣ የመጀመሪያውን የበለስ ፍሬ የማየት ያህል ነበር፤ ወደ በኣል ፌጎር በመጡ ጊዜ ግን፣ ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ራሳቸውን ለዩ፤ እንደ ወደዱትም ጣዖት የረከሱ ሆኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 22:15

ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወድዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 57:3-4

“እናንተ የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣ እናንተ የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤ እናንተ፣ ወዲህ ኑ! የምትሣለቁት በማን ላይ ነው? የምታሽሟጥጡት ማንን ነው? ምላሳችሁንስ አውጥታችሁ የምታሾፉት በማን ላይ ነው? እናንተ የዐመፀኞች ልጆች፣ የሐሰተኞች ዘር አይደላችሁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 8:13

ደግሞም፣ “ከእነዚህ የባሰ አስጸያፊ ነገር ሲሠሩ ታያለህ” አለኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 2:7

እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣ ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዳንኤል 9:27

አለቃው ከብዙዎች ጋራ ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕትና ቍርባን ማቅረብን ያስቀራል። የታወጀው ፍርድ በርሱ ላይ እስኪፈስስ ድረስ፣ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያቆማል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 13:27

በኰረብቶችና በሜዳዎች ላይ፣ አስጸያፊ ተግባርሽን፣ ምንዝርናሽንና ማሽካካትሽን፣ ኀፍረተ ቢስ ግልሙትናሽን አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ወዮልሽ! ከርኩሰትሽ የማትጸጂው እስከ መቼ ነው?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:2

“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለኢየሩሳሌም አስጸያፊ ተግባሯን ፊት ለፊት ንገራት፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሶፎንያስ 1:17

“እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣ በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና። ደማቸው እንደ ትቢያ፣ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይጣላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 6:10

በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤ እስራኤልም ረከሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 22:11

በውስጥሽ አንዱ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ ሌላውም የልጁን ሚስት ያስነውራል፤ ሌላው ደግሞ የገዛ እኅቱ የሆነችውን የአባቱን ልጅ ይደፍራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 14:1

ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገሮችን ይሠራሉ። በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 5:30-31

“የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኗል፤ ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 33:29

ካደረጓቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሣ፤ ምድሪቱን ጠፍና ባድማ በማደርግበት ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 16:18

ምድሬን በድን በሆኑ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ፣ ርስቴንም በአሳፋሪ ነገሮች ስለ ሞሉ፣ ላደረጉት በደልና ኀጢአት ዕጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:9

የተላላ ዕቅድ ኀጢአት ነው፤ ሰዎችም ቂልነትን ይጸየፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 18:21

“ ‘ከልጆችህ ማንኛውንም ለሞሎክ እንዲሠዋ አሳልፈህ አትስጥ፤ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 32:16

በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስጸያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቈጡት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 44:22

እግዚአብሔር ክፉ አድራጎታችሁንና አስጸያፊ ተግባራችሁን ሊታገሥ ባለመቻሉ፣ ዛሬ እንደ ሆነው ምድራችሁ የርግማን ምልክትና ሰው የማይኖርበት ባዶ ምድረ በዳ ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 20:1-5

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ ‘አንድ ሰው ከባልንጀራው ሚስት ጋራ ቢያመነዝር፣ አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ይገደሉ። “ ‘አንድ ሰው ከአባቱ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም አባቱን አዋርዷል፤ ሰውየውና ሴትዮዋ ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። “ ‘አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ሁለቱም ይገደሉ፤ ነውር አድርገዋልና ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። “ ‘አንድ ወንድ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ እንደሚፈጽም ሁሉ ከወንድ ጋራ ቢፈጽም፣ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋልና ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። “ ‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ አድራጎቱ ጸያፍ ነው፤ በመካከላችሁ እንዲህ ዐይነት ርኩሰት እንዳይገኝ ሰውየውና ሴቶቹ በእሳት ይቃጠሉ። “ ‘ማንኛውም ሰው ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ይገደል፤ እንስሳዪቱንም ግደሏት። “ ‘አንዲት ሴት ወደ እንስሳ ቀርባ ግብረ ሥጋ ብትፈጽም፣ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። “ ‘አንድ ሰው የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ የሆነችውን እኅቱን አግብቶ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አድራጎቱ አሳፋሪ ነው፤ በሕዝባቸው ፊት ከሕዝባቸው ተለይተው ይጥፉ። ሰውየው እኅቱን አዋርዷልና ይጠየቅበታል። “ ‘ማንኛውም ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ የፈሳሿን ምንጭ ገልጧልና፣ እርሷም የፈሳሿን ምንጭ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ። “ ‘ከእናትህም ሆነ ከአባትህ እኅት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ የሥጋ ዝምድናን ማቃለል ስለ ሆነ ሁለታችሁም ትጠየቁበታላችሁ። “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ይገደል፤ እርሱንም የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው። “ ‘ማንኛውም ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አጎቱን አዋርዷልና ሁለቱም ይጠየቁበታል፤ ያለ ልጅም ይሞታሉ። “ ‘ማንኛውም ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ አድራጎቱ ርኩሰት ነው፤ ወንድሙን አዋርዷልና፣ ያለ ልጅም ይቀራሉ። “ ‘እንድትኖሩባት እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ አድርጉም። ከፊታችሁ የማሳድዳቸውን አሕዛብ ልማድ አትከተሉ፤ እነዚህን ሁሉ በማድረጋቸው ተጸየፍኋቸው። እናንተ ግን፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ማርና ወተት የምታፈስሰውን አገር ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ” አልኋችሁ፤ ከአሕዛብ የለየኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። “ ‘ንጹሕ በሆኑትና ንጹሕ ባልሆኑት እንስሳት እንዲሁም ንጹሕ በሆኑትና ንጹሕ ባልሆኑት ወፎች መካከል ልዩነት አድርጉ። ርኩስ ነው ብዬ በለየሁት በማንኛውም እንስሳ ወይም ወፍ ወይም በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም ነገር ራሳችሁን አታርክሱ። እናንተ ለእኔ ቅዱሳን ትሆኑልኛላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና፤ የእኔ ትሆኑ ዘንድ ከአሕዛብ መካከል ለይቻችኋለሁ። “ ‘ከመካከላችሁ ሙታን ጠሪ ወይም መናፍስት ጠሪ የሆነ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ይገደል፤ በድንጋይም ይወገሩ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’ ” ልጁን ለሞሎክ በመስጠት መቅደሴን አርክሷልና፣ ቅዱሱን ስሜንም አቃልሏልና፣ በዚያ ሰው ላይ ጠላት እሆንበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ። የአገሩ ሕዝብ፣ ሰውየው ልጁን ለሞሎክ ሲሰጥ አይተው ቸል ቢሉ፣ ባይገድሉትም፣ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ጠላት እሆናለሁ፤ እርሱንና ከሞሎክ ጋራ በማመንዘር እርሱን የተከተሉትን ሁሉ ከሕዝባቸው መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 19:4-5

እኔን ትተውኝ፣ ይህን ስፍራ የባዕድ አማልክት ቦታ አድርገውታልና። እነርሱም ሆኑ አባቶቻቸው፣ የይሁዳ ነገሥታትም ለማያውቋቸው አማልክት ሠውተዋል፤ ይህንም ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታል፤ እኔም ያላዘዝኋቸውን፣ ያልተናገርኋቸውን፣ ፈጽሞም ያላሰብሁትን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን በእሳት ሊሠዉለት ለበኣል መስገጃ ኰረብቶች ሠርተዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 8:17

እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን አይተሃልን? የይሁዳ ቤት በዚህ ቦታ የሚፈጽሙት ጸያፍ ተግባር ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱንስ በዐመፅ በመሙላት ዘወትር ያስቈጡኝ ዘንድ ይገባልን? እነሆ፤ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 5:5

እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
አሞጽ 5:21-24

“ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ጠልቼውማለሁ፤ ጉባኤዎቻችሁ ደስ አያሰኙኝም። የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልቀበለውም፤ ከሠቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልመለከተውም። የዝማሬህን ጩኸት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ዜማ አልሰማም። ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:24-27

ስለዚህም እግዚአብሔር በኀጢአት በተሞላው የልባቸው ምኞት እርስ በርሳቸው የገዛ አካላቸውን እንዲያስነውሩ ቅድስና ለሌለው ሩካቤ ሥጋ አሳልፎ ሰጣቸው። የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው። አሜን። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር አሳፋሪ ለሆነ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም እንኳ ለባሕርያቸው የሚገባውን ግንኙነት ባሕርያቸው ላልሆነው ግንኙነት ለወጡ። እንደዚሁም ወንዶች ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወት ተቃጠሉ፤ ወንዶች ከወንዶች ጋራ ነውር ፈጸሙ፤ በዚህም ጥፋታቸው በገዛ ራሳቸው የሚገባቸውን ቅጣት ተቀበሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:27

ጻድቃን አታላዮችን ይጸየፋሉ፤ ክፉዎችም ቅኖችን ይጠላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:24

ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም አታምልካቸው፤ ወይም ልምዳቸውን አትከተል፤ እነርሱን ማፈራረስ አለብህ፤ የአምልኮ ድንጋዮቻቸውንም ሰባብር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 21:26

እግዚአብሔር ከእስራኤል ፊት ያሳደዳቸው አሞራውያን እንዳደረጉት ሁሉ፣ እርሱም ጣዖታትን በማምለክ እጅግ የሚያስጸይፍ ርኩሰት ፈጸመ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 19:13

በጣራዎቻቸው ላይ ለሰማይ ሰራዊት ዕጣን የታጠነባቸውና ለባዕዳን አማልክት የመጠጥ ቍርባን የቀረበባቸው፣ የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:20-21

አይደለም፤ አሕዛብ የሚሠዉት ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአጋንንት ነው፤ ከአጋንንት ጋራ እንድትተባበሩም አልሻም። የጌታን ጽዋና፣ የአጋንንትን ጽዋ በአንድ ላይ መጠጣት አትችሉም፤ ከጌታ ማእድና ከአጋንንት ማእድ ተካፋይ መሆን አትችሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 12:30

ከፊትህ ከጠፉ በኋላ፣ “እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ” ብለህ በመጠየቅ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 15:23

ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 18:9

አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፣ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 7:30

“ ‘የይሁዳ ሕዝብ በፊቴ ክፉ ነገር አድርጓል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ አስጸያፊ ነገራቸውን ስሜ በተጠራበት ቤት በማስቀመጥ አርክሰውታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:58

ለብልግናሽና ለአስጸያፊ ተግባርሽ የሚገባውን ቅጣት ትሸከሚያለሽ፤ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 15:8

አሳ ይህን ቃልና የነቢዩን የዖዴድን ልጅ የዓዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ በረታ። ከመላው ይሁዳና ከብንያም ምድር፣ በኤፍሬምም ኰረብቶች ላይ ከያዛቸው ከተሞች አስጸያፊዎቹን ጣዖታት አስወገደ። ከእግዚአብሔር መቅደስ ሰበሰብ ፊት ለፊት የነበረውንም የእግዚአብሔር መሠዊያ ዐደሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 16:22

አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:43

“ ‘በእነዚህ ነገሮች አስቈጣሽኝ እንጂ የልጅነትሽን ወራት አላሰብሽም፤ ስለዚህ የሥራሽን እከፍልሻለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በሌላው አስጸያፊ ተግባርሽ ሁሉ ላይ ዘማዊነትን አልጨመርሽምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:33

በምድርህ ላይ እንዲኖሩ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ እኔን እንድትበድል ያደርጉሃል፤ አማልክታቸውን ማምለክ በርግጥ ወጥመድ ይሆንብሃልና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:10

ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣ በቈፈረው ጕድጓድ ይገባል፤ ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 18:24

“ ‘ከእነዚህ በአንዱ እንኳ ራሳችሁን አታርክሱ፤ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ በእነዚህ ሁሉ ረክሰዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 6:30

እግዚአብሔር ንቋቸዋልና፣ የተናቀ ብር ተብለው ይጠራሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 3:8-9

ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና። የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ፣ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 22:2

“የሰው ልጅ ሆይ፤ አትፈርድባትምን? ደም በምታፈስሰው በዚህች ከተማ ላይ አትፈርድባትምን? ጸያፍ ተግባሯን ፊት ለፊት ንገራት፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 73:27

እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ የሚያመነዝሩትን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 5:23

ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልኸኛ ልብ አለው፤ መንገድ ለቅቆ ሄዷል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ የልዑል ስም ባለቤት፣ ለዘላለም የተመሰገንክ እና የተከበርክ፣ ከፍ ከፍ ያልክ እና የሚያስፈራ ቅዱስ ነህ። ዛሬ በሙሉ ልቤ እሰግድልሃለሁ። ማንነትህን አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ወሰን የለሽ ፍቅርህና ምህረትህ፣ ስላደረግክልኝ ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ጌታ ሆይ፣ ብዙ የምለውጣቸው ነገሮች እንዳሉብኝ አውቃለሁ። በራሴ ኃይል ግን አልችልም። እንደ ፈቃድህ ለመኖር፣ የሥጋ ምኞቴንም ላለማስደሰት የአንተን እርዳታ እሻለሁ። ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፣ ቅን መንፈስንም አድስልኝ። ከቅድስናህ ስጠኝ፤ ሕይወቴ በሙሉ በእውነተኝነት የተሞላ ይሁን፣ በፊትህም የሚያስጸይፍ ነገር እንዳላደርግ። በአንተ ፊት መፍራትን በልቤ አኑር፣ በአኗኗሬም በአስተሳሰቤም አክብርህ። አዲስ ሰው አድርገኝ፣ ለአንተ ብቻ የሚኖር፣ ስምህንም የሚያስከብር። በኢየሱስ ስም፣ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች