Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


119 የእግዚአብሔርን አመፅ የሚያወግዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

119 የእግዚአብሔርን አመፅ የሚያወግዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

እግዚአብሔር ታላቅና የሚያስፈራ ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለእርሱ ይገባዋል። በእርሱ ፊት ተራሮች ይንቀጠቀጣሉ፤ ማንም አመፀኛ ከቅጣት አያመልጥም።

የዘላለም ስሙ ጽኑ ነው፤ የማይወዳደር ኃይል አለው። ስለዚህ በውስጥህ ያለውን ጠማማ ነገር አቅና። በልብህ ክፋት ካለ ከእግዚአብሔር ይቅርታን ፈልግ፤ እርሱ ጻድቅና መሐሪ ነውና።

ቃሉንና ፈቃዱን አትፈታተን፤ በተቃራኒው ብትሰራ በምድር ላይ አትለመልምም። ዛሬ ከእርሱ ጋር የምትታረቅበት፣ ልብህን የምትከፍትበትና በእርሱ ፊት የምትዋረድበት ቀን ነው፤ ትሑት ልብ በእርሱ ዘንድ አይጣልምና።

በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፤ በራስህ አስተሳሰብ አትታበይ፤ ይልቁንም በእግዚአብሔር ታመን፤ በምንም ነገር አትኩራራ፤ አለበለዚያ ነፍስህ ትበላሻለች፤ የፈጠረህንና ሕይወትን የሰጠህን ትቃወማለህ።

የእግዚአብሔር መንገዶች ፍጹማን ናቸው፤ ወደ ዘላለም ሕይወትም ይመራሉ፤ የሰው መንገዶች ግን ጠማማዎች ናቸው፤ ወደ ሞትም ያደርሳሉ።


ኤርምያስ 28:16

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔርም ላይ ዐመፅ ተናግረሃልና፣ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:6

እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤ ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 15:22-23

ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣ እግዚአብሔር፣ በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል። ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 5:23

ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልኸኛ ልብ አለው፤ መንገድ ለቅቆ ሄዷል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 13:5

ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንድታምፁ ተናግሯልና፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጓልና፣ ያ ነቢይ ወይም ሕልም ዐላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘኍል 20:24

“አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፤ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችኋልና ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 12:14-15

እግዚአብሔርን የምትፈሩና የምታመልኩ፣ የምትታዘዙትና በትእዛዞቹ ላይ የማታምፁ ከሆነ፣ እንዲሁም እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከተከተላችሁ መልካም ይሆንላችኋል። እግዚአብሔርን የማትታዘዙና በትእዛዞቹም ላይ የምታምፁ ከሆነ ግን፣ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 30:1

“ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእኔ ያልሆነውን ሐሳብ ይከተላሉ፤ ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ በኀጢአት ላይ ኀጢአት ይጨምራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 32:9

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነዚህን ሕዝብ አይቻቸዋለሁ፤ ዐንገተ ደንዳናዎችም ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘኍል 14:9

ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 9:7

አምላክህን እግዚአብሔርን በምድረ በዳ እንዴት እንዳስቈጣኸው አስታውስ፤ ከቶም አትርሳ። ከግብጽ ከወጣህበት ዕለት አንሥቶ እዚህ ቦታ እስከ ደረስህበት ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅህ ነህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 5:10

አምላክ ሆይ፤ የእጃቸውን ስጣቸው! ተንኰላቸው መውደቂያቸው ይሁን፤ ከኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፣ በአንተ ላይ ዐምፀዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 63:10

እነርሱ ግን ዐመፁ፤ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ፤ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:24

“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 2:19

ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:8

ነገር ግን እንደ አባቶቻቸው፣ እልኸኞችና ዐመፀኞች፣ ልቡን ያላቀና፣ መንፈሱም በእግዚአብሔር የማይታመን ትውልድ አይሆኑም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 1:18

“እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔ ግን በትእዛዙ ላይ ዐመፅ አድርጌ ነበር፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ወይዛዝርቶቼና ጐበዛዝቴ፣ ተማርከው ሄደዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:42

“ዐምፀናል፤ ኀጢአትም ሠርተናል፤ አንተም ይቅር አላልኸንም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 4:17

ሰብል እንደሚጠብቁ ሰዎች ይከቧታል፤ በእኔ ላይ ዐምፃለችና፤’ ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:2

ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቷችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 13:16

የሰማርያ ሰዎች በደላቸውን ይሸከማሉ፤ በአምላካቸው ላይ ዐምፀዋልና። በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ሕፃኖቻቸውም በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤ የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 33:8

እኔን ከበደሉበት ኀጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔ ላይ ያመፁበትንም ኀጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 31:27

የቱን ያህል ዐመፀኞችና ዐንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ ዐውቃለሁና። እኔ በሕይወት ከእናንተ ጋራ እያለሁ በእግዚአብሔር ላይ ካመፃችሁ፣ ከሞትሁ በኋላማ የቱን ያህል ልታምፁ!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ተሰሎንቄ 2:3

ማንም ሰው በምንም መንገድ አያታልላችሁ፤ አስቀድሞ ዐመፅ ሳይነሣ፣ ለጥፋት የተመደበውም የዐመፅ ሰው ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 5:25

በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል። ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሏችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 107:11

በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማመፅ፣ የልዑልን ምክር አቃልለዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:2

ስለዚህ፣ በባለሥልጣን ላይ የሚያምፅ በእግዚአብሔር ሥርዐት ላይ ማመፁ ነው፤ ይህን የሚያደርጉትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 3:13

በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅሽ፣ ክብርሽንም ለእንግዶች አማልክት፣ በየለምለሙ ዛፍ ሥር አሳልፈሽ በመስጠት፣ ለእኔ ባለመታዘዝሽ፣ በደለኛ መሆንሽን ይህን አንድ ነገር ብቻ እመኚ’ ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 15:23

ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 20:8

“ ‘እነርሱ ግን በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ሊሰሙኝም አልፈለጉም፤ ዐይኖቻቸውን ያሳረፉባቸውን ርኩስ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖታት አልተዉም። እኔም በዚያው በግብጽ ምድር መዓቴን በላያቸው ላፈስስ፣ ቍጣዬንም ላወርድባቸው ወስኜ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:13

በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:11

ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤ በርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 20:13

“ ‘ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ ዐመፀብኝ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልጠበቁም፤ ሕጌንም ተላለፉ፤ ሰንበቴንም ፈጽሞ አረከሱ። እኔም መዓቴን ላፈስስባቸው፣ በምድረ በዳም ላጠፋቸው ወስኜ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 2:3

እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእኔ ላይ ወደ ዐመፀው፣ ወደ ዐመፀኞቹ የእስራኤል ልጆች እልክሃለሁ፤ እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐምፀውብኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:43

እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤ እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤ በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዳንኤል 9:9

ምንም እንኳ በርሱ ላይ ያመፅን ብንሆን፣ ጌታ አምላካችን ይቅር ባይና መሓሪ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:7

ለኀጢአት የተገዛ አእምሮ ከእግዚአብሔር ጋራ ጠበኛ ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛም፤ መገዛትም አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 65:2

ለዐመፀኛ ሕዝብ፣ መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣ የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ነህምያ 9:26

“ነገር ግን እንቢተኞች ሆኑ፤ ዐመፁብህም፤ ሕግህንም አሽቀንጥረው ጣሉ፤ ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩት ነቢያትህን ገደሉ፤ አስጸያፊ የስድብ ቃልም ተናገሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 1:26-27

እናንተ ግን ለመውጣት ፈቃደኞች አልነበራችሁም፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ። በየድንኳኖቻችሁ ሆናችሁ እንዲህ ስትሉ አጕረመረማችሁ፤ “እግዚአብሔር ጠልቶናል፤ ስለዚህም ከግብጽ ያወጣን አሞራውያን እንዲያጠፉን በእጃቸው አሳልፎ ሊሰጠን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:2

ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 44:16-17

“አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን መልእክት አንሰማም፤ እናደርጋለን ያልነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ አባቶቻችን፣ ነገሥታታችንና ባለሥልጣኖቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ለሰማይዋ ንግሥት እናጥናለን፤ የመጠጥ ቍርባን እናፈስስላታለን። በዚያ ጊዜ የተትረፈረፈ ምግብ ነበረን፤ በመልካም ሁኔታ እንገኝ ነበር እንጂ ምንም ክፉ ነገር አልገጠመንም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:4

እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ከጣላቸውና በጨለማ ጕድጓድ ለፍርድ ካስቀመጣቸው፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 36:16

እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሣለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 2:29

“ለምን በእኔ ታማርራላችሁ? ያመፃችሁብኝ እናንተ ሁላችሁ ናችሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 4:6

ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል። ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 8:5

ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መሳፍንት 2:19

መስፍኑ ከሞተ በኋላ ግን ሕዝቡ ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ እነርሱን በማገልገልና በማምለክ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ክፉ መንገድ ተመለሱ፤ ክፉ ሥራቸውንና የእልኸኝነት መንገዳቸውንም አይተውም ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 33:3

ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር ውጡ፤ ነገር ግን ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆናችሁ፣ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋራ አልሄድም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 81:11-12

“ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤ እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ። ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 7:24

እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብ ብለው ለማድመጥም አልፈለጉም፤ ይልቁን የክፉ ልባቸውን ሐሳብ በእልኸኝነት ተከተሉ፤ ወደ ፊት በመሄድ ፈንታም ወደ ኋላቸው ተመለሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 17:14-15

ይሁን እንጂ እነዚህም አልሰሙም፤ እግዚአብሔር አምላካቸውን እንዳልታመኑበት እንደ አባቶቻቸው ዐንገታቸውን አደነደኑ። ሥርዐቱንና ከአባቶቻቸው ጋራ የገባውን ኪዳን፣ ለእነርሱም የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ናቁ፤ ከንቱ ጣዖታትን ተከትለው ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ፤ እግዚአብሔር፣ “እነርሱ የሚያደርጉትን እንዳታደርጉ” ብሎ ቢያዝዛቸው እንኳ በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ፤ እግዚአብሔር እንዳያደርጉ የከለከላቸውንም ፈጸሙ እንጂ አልተዉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዳንኤል 9:5

እኛ ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናልም፤ ክፋትን አድርገናል፤ ዐምፀናልም፤ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 48:8

አልሰማህም ወይም አላወቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 7:13

ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 20:21

“ ‘ልጆቻቸው ግን በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልተከተሉም፤ ሕጌን ለመጠበቅ አልተጉም፤ ሰንበቴንም አረከሱ። እኔም በምድረ በዳ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ ቍጣዬንም አወርድባቸዋለሁ ብዬ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:9

ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 11:10

ቃሌን መስማት ወዳልፈለጉት ወደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፤ ሊያገለግሏቸውም ሌሎችን አማልክት ተከተሉ። የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋራ የገባሁትን ኪዳን አፈረሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 31:29

እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ፣ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ ዐውቃለሁና። በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፣ እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ለቍጣ ስለምታነሣሡት፣ በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:28

ዐመፀኞችና ኀጢአተኞች ግን በአንድነት ይደቅቃሉ፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 25:4-5

እግዚአብሔር አገልጋዮቹን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሞ ወደ እናንተ ላከ፤ ሆኖም አልሰማችሁም፤ ትኵረትም አልሰጣችሁትም። እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እንግዲህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ለዘላለም ትቀመጣላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:40

በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት! በበረሓስ ምን ያህል አሳዘኑት!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 50:5

ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤ እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 13:10

ቃሌን መስማት እንቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደ ሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 23:35

“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ረስተሽኛል፤ ወደ ኋላም ገሸሽ አድርገሽኛልና የብልግናሽንና የሴሰኝነትሽን ውጤት ትሸከሚአለሽ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 9:13-14

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው። በዚህ ፈንታ፣ በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ አባቶቻቸው ያስተማሯቸውን በኣሊምን ተከተሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:7

አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤ በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 30:9

እነዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመስማት የማይፈልጉ፣ ዐመፀኛ ሕዝቦችና አታላይ ልጆች ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 3:7

ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘የምንመለሰው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 15:6

እኔን ጥለሽኛል” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ ኋላም እያፈገፈግሽ ነው፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ አጠፋሻለሁም፤ ከእንግዲህም አልራራልሽም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 14:1

ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገሮችን ይሠራሉ። በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ነህምያ 9:17

ለመስማት አልፈለጉም፤ በመካከላቸውም ያደረግሃቸውን ታምራት ማስታወስ አልቻሉም። ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ በዐመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ። አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፣ ቸርና ርኅሩኅ፣ ለቍጣም የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ። ስለዚህ አልተውሃቸውም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 1:24-26

ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እንቢ ስላላችሁኝ፣ እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣ ምክሬን ሁሉ ስለ ናቃችሁ፣ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፣ እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 12:19

ስለዚህ እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንዳመፀ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 29:13

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 32:33

ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ ደጋግሜ ባስተምራቸውም አይሰሙም፤ ተግሣጽም አይቀበሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 7:11-12

“እነርሱ ግን ማስተዋል አልፈለጉም፤ በእልኸኝነት ጀርባቸውን አዞሩ፤ ጆሯቸውንም ደፈኑ። ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት በኩል በመንፈሱ የላከውን ቃል ወይም ሕግ አልሰሙም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እጅግ ተቈጣ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:24

ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፣ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃልለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 44:4-5

እኔም፣ ‘ይህን የምጠላውን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ’ በማለት አገልጋዮቼን ነቢያትን ደጋግሜ ላክሁባቸው። እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብም አላሉም፤ ከክፋታቸው አልተመለሱም፤ ለሌሎችም አማልክት ማጠን አልተውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 3:2-4

ሰዎች ራሳቸውን የሚወድዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወድዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኵሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድዱ ይሆናሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 16:12

እናንተም ደግሞ ከአባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አድርጋችኋል፤ እያንዳንዳችሁ እኔን በመታዘዝ ፈንታ የልባችሁን ክፋት ምን ያህል በእልኸኝነት እንደምትከተሉ ተመልከቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 3:7

ነገር ግን የእስራኤል ቤት ሁሉ ልበ ደንዳኖችና እልኸኞች ስለ ሆኑ ሊሰሙኝ አልፈለጉም፤ ስለዚህ የእስራኤል ቤት አንተንም አይሰሙህም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 18:12

እነርሱ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤ ባቀድነው እንገፋበታለን፤ እያንዳንዳችንም የክፉ ልባችንን እልኸኝነት እንከተላለን’ ይላሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:21-23

እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ቢሉም፣ ሞኞች ሆኑ፤ የዘላለም አምላክን ክብር ምዉት በሆነው ሰው፣ በወፎች፣ በእንስሳትና በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ መስለው ለወጡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:12

ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 3:15

ይኸውም፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:32

ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል የሚለውን ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:3-4

ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል። ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 23:17

እኔን ለሚንቁኝ፣ ‘እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል’ ይላሉ፤ የልባቸውን እልኸኝነት ለሚከተሉም ሁሉ፣ ‘ክፉ ነገር አይነካችሁም’ ይሏቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:26-27

የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 13:21-22

ከይሁዳ ለመጣውም የእግዚአብሔር ሰው፣ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፣ ‘የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለሃል፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህንም ትእዛዞች አልጠበቅህም፤ ተመልሰህ በመምጣት እንዳትበላና እንዳትጠጣ በነገረህ ቦታ እንጀራ በላህ፤ ውሃም ጠጣህ። ስለዚህ ሬሳህ በአባቶችህ መቃብር አይቀበርም’ ” ሲል ጮኾ ተናገረው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 32:15

ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 2:2-3

የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤ “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣ የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 50:17

ተግሣጼን ትጠላለህና፤ ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 24:5

ምድር በሕዝቧ ትረክሳለች፤ ሕግን ጥሰዋል፤ ሥርዐትን ተላልፈዋል፤ ዘላለማዊውንም ኪዳን አፍርሰዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 22:21

ተመችቶሽ በነበረ ጊዜ አስጠነቀቅሁሽ፤ አንቺ ግን፣ ‘አልሰማም’ አልሽ፤ ከትንሽነትሽ ጀምሮ መንገድሽ ይኸው ነበር፤ ቃሌንም አልሰማሽም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 33:11

እንዲህ በላቸው፤ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ በክፉዎች ሞት ደስ አልሰኝም። ተመለሱ! ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ?’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 24:20

የእግዚአብሔርም መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆሞ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? አይሳካላችሁም፤ እናንተ እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁት እርሱም ትቷችኋል’ ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:10

የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፤ በሕጉም መሠረት ለመሄድ እንቢ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 5:3

እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 16:8

ሙሴም ንግግሩን በመቀጠል፣ “በርሱ ላይ ማጕረምረማችሁን ሰምቷልና በምሽት የምትበሉትን ሥጋ፣ በማለዳም የምትፈልጉትን ያህል እንጀራ በሚሰጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቃላችሁ፤ እኛ ማን ነን? በእኛ ላይ አይደለም ያጕረመረማችሁት፤ በእግዚአብሔር ላይ ነው እንጂ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 7:13

እነዚህን ሁሉ ስታደርጉ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ደጋግሜ ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁኝም፤ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን አልመለሳችሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:16-19

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦ ትዕቢተኛ ዐይን፣ ሐሰተኛ ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆች፣ ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣ በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 24:13

“ ‘የረከስሽው በብልግናሽ ነው፤ ቍጣዬ በአንቺ ላይ እስኪፈጸም ድረስ ከእንግዲህ ንጹሕ አትሆኚም፤ ከርኩሰትሽ ላነጻሽ ፈልጌ፣ መንጻት አልወደድሽምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 2:13

“ሕዝቤ ሁለት ኀጢአት ፈጽመዋል፤ ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንሁትን፣ እኔን ትተዋል፤ ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓዶች፣ ለራሳቸው ቈፍረዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 12:14

እግዚአብሔርን ይሻ ዘንድ ልቡን ስላላዘጋጀ ክፉ ነገር አደረገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:5

ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ? ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ? ራሳችሁ በሙሉ ታምሟል፤ ልባችሁ ሁሉ ታውኳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 9:9

በጊብዓ እንደ ነበረው፣ በርኩሰት ውስጥ ተዘፍቀዋል፤ እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 57:17

ኀጢአት ስለ ሞላበት ስግብግብነቱ ተቈጣሁት፤ ቀጣሁት፤ ፊቴንም በቍጣ ከርሱ ሸሸግሁ፤ ያም ሆኖ በገዛ መንገዱ ገፋበት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
አሞጽ 4:6-8

“በየከተማው ጥርሳችሁን አጠራለሁ፤ በየመንደሩም የምትበሉትን አሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር። “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ ሌላው ዝናብ ዐጥቶ ደረቀ። ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 20:38

በእኔ ላይ ያመፁትንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ ከሚኖሩበት አገር አወጣቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 19:15

“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ዐንገታቸውን በማደንደን ቃሌን ስላልሰሙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች ሁሉ ላይ ላደርስ ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣለሁ።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 8:9

ጥበበኞች ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣ ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 25:7

“ነገር ግን አልሰማችሁኝም” ይላል እግዚአብሔር፤ “እጃችሁ በሠራው ነገር አስቈጣችሁኝ፤ በራሳችሁም ላይ ክፉ ነገር አመጣችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 28:15

ነገር ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝ በዛሬዋ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዐቱን ሁሉ በጥንቃቄ ባትከተላቸው፣ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱብሃል፤ ያጥለቀልቁሃልም፦

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 30:8

እንደ አባቶቻችሁም ዐንገተ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ እርሱ ለዘላለም ወደ ቀደሰውም መቅደስ ኑ። አስፈሪ ቍጣው ከእናንተ እንዲመለስም፣ እግዚአብሔር አምላካችሁን አገልግሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 10:6

ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣ በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰድደዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 3:4

እነርሱም ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም፤ ካደረጉት ክፋት የተነሣ፣ በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
አሞጽ 2:4

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘላለማዊ አምላክ፥ ልቤ ያመልክሃል። እጆችህ ፈጥረውኛል፥ ነፍሴንም ሕይወት ሰጥተሃታል። ታላቅ ኃይልህ በሰማይም በምድርም ሁሉን ይገዛል። ስለዚህ ክብር ሁሉ ለስምህ ይገባል፤ አንተ በእውነት የምትወደስ ነህ። አምላኬ ሆይ፥ ዛሬ በትሕትና ወደ አንተ እቀርባለሁ። የልቤን ጥልቀት መርምረህ ከክፋቴ ሁሉ እንድታነጻኝ እሻለሁ። አንተን የሚቃወም ስሜት ወይም ሐሳብ ካለኝ ይቅር በለኝ። ፈቃድህን የሚጻረር ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም። ስለዚህ እርምጃዬን አቅና፥ የምሄድበትንም መንገድ አስተምረኝ። በራሴ አስተሳሰብ ብልህ አትሁን፥ ልቤም አንተን አይክድህ። ወደ ክህደት የሚያስብ ሐሳብ ሁሉ ነጻ ነኝ። በኢየሱስ ስም ንጹሕ ልብ ስለፈጠርክልኝ አመሰግንሃለሁ። በኢየሱስ ስም፤ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች