ልጆቼ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተሰወረ ኃጢያት የለም። ከሰዎች ልንሰውረው እንችላለን፤ ግን እግዚአብሔር በልባችን ያለውን ሁሉ ያውቃል።
በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው፣ የተሰወረ ኃጢያት ሕይወታችንን ሊያጠፋ ይችላል። አካን የተባረከውን ዕቃ ሰውሮ ቢወስድም፣ ኃጢያቱ ተጋለጠና እሱና ቤተሰቡ ከባድ ዋጋ ከፈሉ።
ምሳሌ 28:13 "ኃጢአቱን የሚሸሽግ አያልቅም፤ የሚሰወረውን ኃጢአት ይቅር አይባልም፤ የሚสารፍና የሚተው ግን ይምረዋል" ይላል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሉቃስ 8:17 "የተሰወረ ሁሉ ይገለጣል፤ የተሸፈነውም ሁሉ ይታወቃል" ብሏል። ኃጢያታችን የተሰወረ ቢመስለንም፣ አንድ ቀን ይገለጣል። ለሥራችን ሁሉ መልስ መስጠት አለብን።
ዛሬ ልባችንን መመርመርና የተሰወሩ ኃጢያቶቻችንን ማስታወስ አለብን። ሰዎች ባያዩትም፣ እግዚአብሔር ግን ያየዋል። እግዚአብሔር እንደ አካን በውስጣችን ያለውን ሐሳብና ድርጊት ሁሉ ያውቃል።
እንግዲህ፣ በእግዚአብሔር ፊት እንቆምና ኃጢያታችንን እንጹ። በትሕትናና በጸጸት ልብ ይቅርታን እንጠይቅ። ዳዊት በመዝሙር 32:5 "ኃጢአቴን በፊትህ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም አልሸፈንኩም፤ 'በደሌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ' አልኩ፤ አንተም የኃጢአቴን በደል ይቅር አልከኝ" ብሏል።
ኃጢያታችንን ለእግዚአብሔር ስንናዘዝና ስንተወው፣ እርሱ ብቻ የሚሰጠውን ይቅርታና ነጻነት እናገኛለን። እሱ ይርዳን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤ በዘላለምም መንገድ ምራኝ።
ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ ወደ ጥልቅ ጕድጓድ ለሚወርዱ ሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣ “ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው!
ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ ዝም ባልሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤ በቀንና በሌሊት፣ እጅህ ከብዳብኛለችና፤ ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደ ላሰው ነገር፣ ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤ በደሌንም አልሸሸግሁም፤ ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤ አንተም የኀጢአቴን በደል፣ ይቅር አልህ። ሴላ
መልካም ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ካከማቸው ክፉ ነገር ክፉውን ያወጣል፤ ሰው በልቡ ሞልቶ የተረፈውን በአፉ ይናገራልና።
ከርሱ ጋራ ኅብረት አለን እያልን በጨለማም ብንመላለስ፣ እንዋሻለን፤ እውነቱንም አናደርግም። ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንመላለስ፣ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፤ የልጁም የኢየሱስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል።
እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን በደል ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይልላችሁም።
የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰዎች ስለ ተናገሩት ከንቱ ቃል ሁሉ በፍርድ ቀን ይጠየቁበታል። ምክንያቱም ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህ፤ ከቃልህም የተነሣ ይፈረድብሃልና።”
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
የአንዳንድ ሰዎች ኀጢአት ግልጽ ነው፤ ከእነርሱም ቀድሞ ፍርድ ቦታ ይደርሳል፤ ሌሎችን ግን ኀጢአታቸው ይከተላቸዋል። መልካም ሥራም እንደዚሁ ግልጽ ነው፤ ግልጽ ያልሆነ ቢኖርም እንኳ ተሰውሮ አይቀርም።
እነሆ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፤ ጆሮውም መስማት አልተሳናትም። በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤ አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ ጀንበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤ በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን። ሁላችን እንደ ድቦች እናላዝናለን፤ እንደ ርግቦችም በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትሕን ፈለግን፤ ግን አላገኘንም፤ ትድግናን ፈለግን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል። በደላችን በፊትህ በዝቷል፤ ኀጢአታችን መስክሮብናል፤ በደላችን ከእኛ አልተለየም፤ ዐመፀኝነታችንንም እናውቃለን። በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል። ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም በሩቁ ቆሟል፤ እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሏል፤ ቅንነትም መግባት አልቻለም። እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ። ማንም እንደሌለ አየ፤ ወደ እርሱ የሚማልድ ባለመኖሩ ተገረመ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ ድነት አመጣለት፤ የራሱም ጽድቅ ደግፎ ያዘው። ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤ የድነትን ቍር በራሱ ላይ ደፋ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤ መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ። እንደ ሥራቸው መጠን፣ ቍጣን ለባላጋራዎቹ፣ ፍዳን ለጠላቶቹ፣ እንደዚሁ ይከፍላቸዋል፤ ለደሴቶችም የእጃቸውን ይሰጣቸዋል። በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤ በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣ እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና። ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቷችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም።
“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ ወይም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ ይኖራልን? እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጥ? ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና። “በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። “በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ። በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾኽ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ፣ መጥፎም ዛፍ ጥሩ ፍሬ ማፍራት አይችልም። ጥሩ ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። በምትፈርዱበትም ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።
ብፁዕ ነው፤ መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ ኀጢአቱም የተሸፈነለት፤ የክፉዎች ዋይታ ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን፣ ምሕረት ይከብበዋል። ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣ በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት፤
እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።
ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። “ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው። “የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንደዚሁ ይሆናል። በዚያ ቀን በቤቱ ጣራ ላይ ያለ፣ ማንም ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ለመውሰድ አይውረድ፤ እንዲሁም በዕርሻ ቦታ ያለ ሰው ወደ ኋላው አይመለስ። የሎጥን ሚስት አስታውሱ። ነፍሱን ለማሰንበት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ነፍሱን የሚያጠፋት ግን ያቈያታል። እላችኋለሁ፤ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ይተኛሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። ሁለት ሴቶች ዐብረው ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች [ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ቦታ ዐብረው ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።”] እነርሱም መልሰው፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወሰዱት ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም፣ “በድን ባለበት አሞሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው። በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ፣ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር በለው።”
“ወንድምህ ቢበድልህ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁ ጥፋቱን ንገረው። ቢሰማህ፣ ወንድምህን እንደ ገና የራስህ ታደርገዋለህ። ባይሰማህ ግን፣ ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ስለሚጸና፣ አንድ ወይም ሁለት ሰው ይዘህ አነጋግረው። እነርሱን ባይሰማ ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማ፣ እንደ አሕዛብና እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ ቍጠረው።
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ጻድቅ ማንም የለም፤ አንድ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻ አንድም የለም። ሁሉም ተሳስተዋል፤ በአንድነት የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ።”
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንመላለስ፣ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፤ የልጁም የኢየሱስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል።
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም። “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ ሰዎችም መብራት አብርተው ከእንቅብ በታች አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ። እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።
እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ። ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ። ነፍሴ በተማረረች ጊዜ፣ ልቤም በተቀሠፈ ጊዜ፣ ደነዝና አላዋቂ ሆንሁ፤ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ። ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል። በምክርህ መራኸኝ፤ ኋላም ወደ ክብር ታስገባኛለህ። በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምሻው የለኝም። ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣ የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው። እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ የሚያመነዝሩትን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ። ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ። ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።
አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።
በዚያ ጊዜ፣ በብዙ ሺሕ የሚቈጠር ሕዝብ እርስ በርስ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ ይህም ግብዝነት ነው። በሰው ልጅ ላይ የማቃለል ቃል የሚሰነዝር ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ግን አይሰረይለትም። “ሰዎች ይዘው ወደ ምኵራብ፣ ወደ ገዥዎችና ወደ ባለሥልጣናት በሚያቀርቧችሁ ጊዜ ሁሉ፣ እንዴት ወይም ምን እንደምትመልሱ አትጨነቁ፤ በዚያ ሰዓት መንፈስ ቅዱስ መናገር የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና።” ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፤ ወንድሜ ውርስ እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለው። ኢየሱስም፣ “አንተ ሰው፤ በእናንተ ላይ ፈራጅ ወይም ዳኛ ያደረገኝ ማነው?” አለው። ደግሞም፣ “የሰው ሕይወቱ በሀብቱ ብዛት የተመሠረተ ስላልሆነ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ራሳችሁንም ጠብቁ” አላቸው። ቀጥሎም እንዲህ ሲል ምሳሌ ነገራቸው፤ “ዕርሻው እጅግ ፍሬያማ የሆነችለት አንድ ሀብታም ነበረ፤ ይህም ሰው፣ ‘ምርቴን የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ ዐሰበ። “እንዲህም አለ፤ ‘እንደዚህ አደርጋለሁ፤ ያሉኝን ጐተራዎች አፈርስና ሌሎች ሰፋ ያሉ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም ምርቴንና ንብረቴንም ሁሉ አከማቻለሁ፤ ነፍሴንም፣ “ነፍሴ ሆይ፤ ለብዙ ዘመን የሚበቃሽ ሀብት አከማችቼልሻለሁ፤ እንግዲህ ዕረፊ፤ ብዪ፤ ጠጪ፤ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ የማይገለጥ የተሸፈነ፣ የማይታወቅ የተሰወረ ምንም የለም። “እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው። “ስለዚህ ለራሱ ሀብት የሚያከማች፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።” ከዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን? ለመሆኑ፣ ከእናንተ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ሰዓት መጨመር የሚችል ማን ነው? እንግዲህ ቀላሉን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ፣ ስለ ሌላው ነገር ለምን ትጨነቃላችሁ? “እስኪ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይለፉም፤ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነርሱ እንደ አንዷ አልለበሰም። እናንተ እምነት የጐደላችሁ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ እሳት የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ? ስለዚህ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ አትሹ፤ አትጨነቁም፤ ስለዚህ በጨለማ ያወራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ ያንሾካሾካችሁት በሰገነት በይፋ ይነገራል።
ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል። “በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና። ቀኝ እጅህ ቢያሰናክልህ ቈርጠህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።
ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና። ነገር ግን በጎ ለሚሠራ ለማንኛውም፣ አስቀድሞ ለአይሁድ ከዚያም ለአሕዛብ ክብር፣ ሞገስና ሰላም ይሆንለታል፤ እግዚአብሔር ለማንም አያደላምና። ሕግ ሳይኖራቸው ኀጢአት የሠሩ ሁሉ ያለ ሕግ ይጠፋሉ፤ ሕግ እያላቸው ኀጢአት የሠሩ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሚባሉት ለሕጉ የሚታዘዙ እንጂ፣ ሕጉን የሚሰሙ አይደሉም። ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ሕግ የሚያዝዘውን ነገር በተፈጥሮ ሲያደርጉ፣ ሕግ ባይኖራቸውም እነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው። ኅሊናቸው ስለሚመሰክር፣ ሐሳባቸው ስለሚከስሳቸው፣ ደግሞም ስለሚከላከልላቸው የሕግ ትእዛዝ በልባቸው የተጻፈ መሆኑን ያሳያሉ። ይህም በወንጌል እንደማስተምረው እግዚአብሔር በሰው ልብ የተሰወረውን በክርስቶስ በኩል በሚፈርድበት ዕለት ግልጽ ይሆናል። አንተ ይሁዲ ነኝ ካልህ፣ በሕግ የምትተማመንና ከእግዚአብሔር ጋራ ባለህ ግንኙነት የምትኵራራ፣ በሕግ በመመራትህም ፈቃዱን ዐውቀህ ፍጹም የሆነውን ለይተህ ከያዝህ፣ ለዕውሮች መሪ፣ በጨለማ ላሉትም ብርሃን መሆንህን ርግጠኛ ከሆንህ፣ እንደዚህ በሚያደርጉትም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ መሆኑን እናውቃለን። በሕጉም ካገኘኸው ዕውቀትና እውነት የተነሣ አላዋቂ ለሆኑት መካሪ፣ ለሕፃናት አስተማሪ ከሆንህ፣ እንግዲህ አንተ ሌሎችን የምታስተምር፣ ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ፣ ትሰርቃለህን? አንተ ሰዎች ማመንዘር የለባቸውም የምትል፣ ታመነዝራለህን? አንተ ጣዖትን የምትጸየፍ፣ ቤተ መቅደስን ትመዘብራለህን? አንተ በሕግ የምትመካ፣ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታዋርዳለህን? ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ዘንድ ይሰደባል” ተብሎ እንደ ተጻፈው መሆኑ ነው። ሕግን የምትፈጽም ከሆነ ግዝረት ዋጋ አለው፤ ሕግን የምትተላለፍ ከሆነ ግን እንዳልተገረዝህ ሆነሃል። ያልተገረዙት ሕጉ የሚያዝዘውን የሚፈጽሙ ከሆነ፣ እንደ ተገረዙ አይቈጠሩምን? አንተ የተጻፈ ሕግ፣ ግዝረትም ቢኖርህ፣ ሕግ ተላላፊ በመሆንህ፣ በሥጋ ያልተገረዘው ለሕግ በመታዘዙ ይፈርድብሃል። አንድ ሰው ለይምሰል በውጫዊው ብቻ ይሁዲ ልሁን ቢል ይሁዲ አይሆንም፤ እውነተኛ ግዝረትም ውጫዊና ሥጋዊ ሥርዐት አይደለም። ዳሩ ግን አንድ ሰው ይሁዲ የሚሆነው በውስጣዊ ማንነቱ ይሁዲ ሆኖ ሲገኝ ነው። ግዝረትም ግዝረት የሚሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ በመንፈስ የልብ ግዝረት ሲኖር ነው። እንዲህ ያለው ሰው ምስጋናው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። እንግዲህ አንተ ሰው በሌሎች ላይ እየፈረድህ ያንኑ የምታደርግ ከሆነ፣ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃል?
ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣ ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።
“በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም። በዚያ ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’ ይሉኛል። በዚያ ጊዜ፣ ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዐመፀኞች፤ ከእኔ ራቁ’ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ደርሷልና፤ እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?
አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
ስለዚህም እግዚአብሔር በኀጢአት በተሞላው የልባቸው ምኞት እርስ በርሳቸው የገዛ አካላቸውን እንዲያስነውሩ ቅድስና ለሌለው ሩካቤ ሥጋ አሳልፎ ሰጣቸው። የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው። አሜን።
ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።
ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ደነገጡ፤ አምላክ የሌላቸውም ፍርሀት ይዟቸው፣ “ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳት ጋራ ማን መኖር ይችላል፣ ከዘላለም እሳትስ ጋራ ማን መኖር ይችላል?” አሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል። ከእግዚአብሔር ዐይን የተሰወረ ምንም ፍጥረት የለም፤ ስለ ራሳችን መልስ መስጠት በሚገባን በርሱ ፊት ሁሉም ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው።
“ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።
ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነቱም በእኛ ውስጥ የለም። ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።
ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሣ፤ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና። እኛ የክርስቶስ አካል ብልቶች ነንና። “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እናገራለሁ። ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባሏን ታክብር። የሚያሳፍርና ተራ የሆነ ንግግር፣ ዋዛ ፈዛዛም ለእናንተ ስለማይገባ በመካከላችሁ አይኑር፤ ይልቁንስ የምታመሰግኑ ሁኑ።
የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም፣ ‘አለሁልህ’ ይልሃል። “የጭቈና ቀንበር፣ የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ፣
አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ። የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤ በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።
እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣ መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ። ክንድህን አንሣልኝ፤ ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁ። ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴን አድምጥ፤ ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤ በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ። ላለመመለስ ከመሰናበቴ በፊት፣ ዳግመኛ ደስ ይለኝ ዘንድ ዐይንህን ከላዬ አንሣ።” እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤ ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ።
“በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለምን ታያለህ? ወይም በዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን፣ ‘ዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ ማለት እንዴት ትችላለህ? አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።
አንዳንዶቹ ከዐመፃቸው የተነሣ ቂሎች ሆኑ፤ ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ገቡ። ሰውነታቸው የምግብ ዐይነት ሁሉ ተጸየፈች፤ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው። እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤ ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።