Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


111 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፤ ስርቆት፣ ሌብነት

111 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፤ ስርቆት፣ ሌብነት

እግዚአብሔር በቃሉ እንደሚያስተምረን መስረቅ በመንፈሳዊም ሆነ በምድራዊ ሕግ የተከለከለ ኃጢአት ነው። መስረቅ በፍፁም አይጸድቅም ወይም አይሸልምም፤ ይልቁንም የሚሰርቁ ይቀጣሉ። ስለዚህ ልቤን ከክፉ ነገር ሁሉ አንጻ፤ ወደ ሞት የሚያደርሱ መጥፎ መንገዶችን አስወግድ።

መስረቅ ለሕይወትህ ምንም ጥቅም የለውም፤ ይልቁንስ እንደ አንገት ላይ ገመድ ማሰር ነው። የሰረቅከው ነገር መጠን ምንም ለውጥ አያመጣም፤ ያልሆነህን መውሰድ ብቻውን ያስወቅሳል። ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥምህ በእግዚአብሔር ፊት ምክንያት ማቅረብ አትችልም።

ስለዚህ «የሰረቀ የሰረቀውን ይተው፤ በገዛ እጁ በትጋት ይሥራ እንዲሁም ለችግረኞች ያካፍል» የሚለውን ምክር እንውሰድ። ከሌሎች ከመስረቅ ይልቅ እግዚአብሔር ለጋስ እንድትሆን እና ሁልጊዜ የምታካፍለው ነገር እንዲኖርህ ይፈልጋል። ለዚህም ነው መሥራት እና የሌሎችን በትጋት የሰሩትን ንብረት አለመናቅ አስፈላጊ የሆነው።

ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ባትያዝም ሁሉም ነገር ይገለጣል፤ ለብዙ ዓመታት እስር ቤት ልትወድቅ ትችላለህ። ለሕይወትህ ስለሚጠቅምህ ነገር አስብ፤ በጊዜያዊ ስሜት አትመራ፤ ሁኔታዎችም አይሸሉህ። የእግዚአብሔርን ፊት ፈልግ፤ እርሱ በምህረቱ እና በክብሩ መሠረት ይሰጣል። በጠላት ወጥመድ አትውደቅ፤ እርዳታ ፈልግ፤ መጥፎ ልማዶችህን ተው፤ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ እንዲመራህ ፍቀድ።

ትእዛዛቱን አትጣስ፤ በቃሉ ጸንተህ ቁም፤ እርሱ በየቀኑ እንዴት እንደሚደግፍህ ታያለህ።


መዝሙር 62:10

በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:2

ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:6

በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:21

ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ ጻድቅ ግን ይቸራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:11

“ ‘አትስረቁ። “ ‘አትዋሹ። “ ‘ከእናንተ አንዱ ሌላውን አያታልል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:22-23

ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤ እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤ የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 5:3-4

እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ በምድር ሁሉ ላይ የሚወጣ ርግማን ነው፤ በአንደኛው በኩል እንደ ተጻፈው የሚሰርቅ ሁሉ ይጠፋል፤ በሌላው በኩል ደግሞ እንደ ተጻፈው በሐሰት የሚምል ሁሉ ይጠፋልና። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ‘እኔ ርግማኑን አመጣዋለሁ፤ እርሱም ወደ ሌባው ቤትና በስሜ በሐሰት ወደሚምለው ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ይቀመጣል፤ ቤቱን፣ ዕንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል’ ይላል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 6:10

ወይም ሌቦች፣ ስግብግቦች፣ ሰካራሞች፣ ተሳዳቢዎችና ቀማኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:18

ሰውየውም፣ “የትኞቹን ትእዛዞች?” ሲል ጠየቀ። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አትግደል፣ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 15:19

ክፉ ሐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ማመንዘር፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ በሐሰት መመስከርና ስም ማጕደፍ ከልብ ይመነጫሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 19:8

ዘኬዎስ ግን ቆመና ጌታን፣ “ጌታ ሆይ፤ እነሆ ካለኝ ሀብት ሁሉ ግማሹን ለድኾች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ቀምቼ ከሆነ፣ አራት ዕጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:22

ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:70

ልባቸው የሠባና የደነደነ ነው፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:21

እንግዲህ አንተ ሌሎችን የምታስተምር፣ ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ፣ ትሰርቃለህን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:10

አይስረቁ፤ ይኸውም በሁሉም መንገድ የአዳኛችን የእግዚአብሔር ትምህርት ይወደድ ዘንድ ፍጹም ታማኝ መሆናቸውን እንዲያስመሰክሩ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 4:6

በዚህም ነገር ማንም ተላልፎ ወንድሙን አያታልል፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ እንደ እነዚህ ያለውን ኀጢአት ሁሉ የሚፈጽሙትን ይበቀላል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 23:30

“ስለዚህ ቃሌን እርስ በእርስ በመሰራረቅ ከእኔ እንደ ተቀበሉ አድርገው የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:1

እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 61:8

“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:1-4

“አንድ ሰው በሬ ወይም በግ ሰርቆ ቢያርድ ወይም ቢሸጥ በአንድ በሬ ምትክ ዐምስት በሬዎች፤ በአንድ በግ ምትክ አራት በጎች ይክፈል። “አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ ወይም ማንኛውንም እንስሳ በጎረቤቱ ዘንድ በዐደራ አስቀምጦ ሳለ እንስሳው ቢሞት ወይም ጕዳት ቢደርስበት ወይም ሰው ሳያይ ተነድቶ ቢወሰድ፣ በሁለቱ መካከል ያለው አለመግባባት መፍትሒ የሚያገኘው፣ ጎረቤቱ የሌላውን ሰው ንብረት እንዳልወሰደ በእግዚአብሔር ፊት በመማል ነው። ባለቤቱም ይህን መቀበል አለበት፤ የካሳም ክፍያ አይጠየቅም። እንስሳው ከጎረቤት ተሰርቆ ከሆነ ግን፣ ለባለቤቱ ካሳ መክፈል አለበት። በዱር አራዊት ተበልቶ ከሆነ፣ ከአውሬ የተረፈውን ማስረጃ አድርጎ በማቅረብ፣ ስለ ተበላው እንስሳ ካሳ እንዲከፍል አይጠየቅም። “አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ተውሶ ሳለ፣ ባለቤቱ በሌለበት ቢጐዳ ወይም ቢሞት ካሳ መክፈል አለበት። ባለቤቱ ከእንስሳው ጋራ ከሆነ ግን፣ ተበዳሪው መክፈል የለበትም፤ እንስሳው ከተከራየም ለኪራይ የተከፈለው ገንዘብ ኪሳራውን ይሸፍናል። “አንድ ሰው ያልታጨችን ልጃገረድ አታልሎ ክብረ ንጽሕናዋን ቢያጐድል፣ የማጫዋን ዋጋ ከፍሎ ሚስት ያድርጋት። እርሷን ለርሱ የልጅቷ አባት በሚስትነት ለመስጠት ከቶ የማይፈቅድ ቢሆን፣ ለድንግሎች መከፈል የሚገባውን ማጫ አሁንም ቢሆን መክፈል ይገባዋል። “መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ። “ከእንስሳ ጋራ ሩካቤ ሥጋ የሚፈጽም ሰው ይገደል። “አንድ ሌባ በር ሲሰብር ተይዞ ቢደበደብና ቢሞት፣ ተከላካዩ የደም ባለዕዳ አይሆንም፤ “ለእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አማልክት የሚሠዋ ይጥፋ። “መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተ በግብጽ መጻተኛ ነበራችሁና። “ባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጅ ላይ ግፍ አትዋሉ። ግፍ ብትውሉባቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ፣ ጩኸታቸውን በርግጥ እሰማለሁ። ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ። “ከሕዝቤ መካከል ችግረኛ ለሆነው ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ ዐራጣ አበዳሪ አትሁኑ፤ ወለድ አትጠይቁት። የጎረቤትህን ልብስ መያዣ አድርገህ ብትይዝ ሲመሽ መልስለት፤ ምክንያቱም ለሰውነቱ መሸፈኛ ያለው ልብስ ያ ብቻ ነው፤ ሌላ ምን ለብሶ ይተኛል? ወደ እኔ ሲጮኽ እኔ እሰማለሁ፤ እኔ ርኅሩኅ ነኝና። “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አታሰማ፤ ወይም የሕዝብህን መሪ አትርገም። “የእህልህን ወይም የወይን ጠጅህን በኵራት ለእኔ ከማቅረብ ወደ ኋላ አትበል። “የወንድ ልጆችህን በኵር ለእኔ ስጠኝ። ነገር ግን ፀሓይ ከወጣች በኋላ ከተፈጸመ፣ ሰውየው በነፍስ ግድያ ይጠየቃል። “ሌባ የሰረቀውን መክፈል አለበት፤ ምንም ከሌለው ግን የሰረቀውን ይከፍል ዘንድ ይሸጥ። ከቀንድ ከብትህና ከበጎችህም እንዲሁ አድርግ፤ ለሰባት ቀን ከእናቶቻቸው ጋራ ይቈዩ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ ሰጠኝ። “እናንተ ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ የዘነጠለውን የእንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ለውሾች ስጡት። የሰረቀው እንስሳ በሬ ወይም አህያ ወይም በግ ከነሕይወቱ በእጁ ከተያዘ ዕጥፍ መክፈል አለበት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 24:1

ምድርና በርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:27

ስስታም ሰው በቤተ ሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ ጕቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 146:7

ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:19-21

“ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። “ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤ ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:1

“የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:61

የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 24:7

አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባሪያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፣ ፈንጋዩ ይሙት። ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:9

“አታመንዝር”፣ “አትግደል”፣ “አትስረቅ”፣ “አትመኝ” የሚሉትና ሌሎችም ትእዛዞች ቢኖሩም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በዚህ በአንድ ሕግ ተጠቃልለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:24

ከአባት ከእናቱ ሰርቆ፣ “ይህ ጥፋት አይደለም” የሚል የአጥፊ ተባባሪ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 24:2

ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤ የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:12

ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 49:6-7

በሀብታቸው የሚመኩትን፣ በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ? የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣ ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:11

እኛ በእናንተ መካከል መንፈሳዊ ዘር ዘርተን ከሆነ ለሥጋ የሚሆን ነገር ብናጭድ ትልቅ ነገር መሆኑ ነውን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 10:2

ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 5:10

ገንዘብን የሚወድድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 50:18

ሌባውን ስታይ ዐብረኸው ነጐድህ፤ ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋራ አደረግህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 73:12

እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ ሁልጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:43-44

ይህን ልብ በሉ፤ ባለቤቱ ሌሊት ሌባ በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ በነቃ፣ ቤቱም እንዳይደፈር በተጠባበቀ ነበር። ስለዚህ የሰው ልጅም ባላሰባችሁት ሰዓት ይመጣል፤ እናንተም እንደዚሁ ዝግጁ ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:23

ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጕቦን ይወድዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:7

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:23

ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 26:10

በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ፤ ቀኝ እጃቸውም ጕቦን ያጋብሳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:29-30

በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣ ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ሆነ፣ ስም አጥፊዎች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞችና ትምክሕተኞች ናቸው፤ ክፋትን የሚሠሩበትን መንገድ ያውጠነጥናሉ፤ ለወላጆቻቸው አይታዘዙም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:12

ኃጥኣን የክፉዎችን ምርኮ ይመኛሉ፤ የጻድቅ ሥር ግን ይንሰራፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:28

እግዚአብሔር ፍትሕን ይወድዳልና፣ ታማኞቹንም አይጥልም። ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤ የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 56:11

እጅግ ሲበዛ ሆዳም ውሾች ናቸው፤ ጠገብሁን አያውቁም፤ የማያስተውሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ሄዱ፤ እያንዳንዳቸውም የግል ጥቅማቸውን ፈለጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:11

ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 2:1

ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 3:14

ወታደሮች ደግሞ፣ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “የማንንም ገንዘብ በግፍ አትንጠቁ፤ ሰውንም በሐሰት አትክሰሱ፤ ደመወዛችሁ ይብቃችሁ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:17

ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 10:3

ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:40-42

አንድ ሰው እጀ ጠባብህን ሊወስድ ቢከስስህ ካባህን ጨምረህ ስጠው። አንድ ሰው አንድ ኪሎ ሜትር ተኩል የሚያህል ርቀት እንድትሄድ ቢያስገድድህ ዕጥፉን መንገድ ዐብረኸው ሂድ። ለሚለምንህ ስጥ፤ ከአንተም ሊበደር የሚሻውን ፊት አትንሣው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:10

ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:119

የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:8

ከጽድቅ ጋራ ጥቂቱ ነገር፣ በግፍ ከሚገኝ ብዙ ትርፍ ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 49:16-17

ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣ የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤ በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤ ክብሩም ዐብሮት አይወርድም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:17

ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤ በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:70-72

ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች ጕረኖ ውስጥ ወሰደው፤ ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣ የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው። እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 7:10

መበለቲቱን ወይም ድኻ አደጉን፣ መጻተኛውን ወይም ድኻውን አታስጨንቁ፤ በልባችሁም አንዳችሁ በአንዳችሁ ላይ ክፉ አታስቡ።’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 5:19

አትስረቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:16-17

የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል። የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፣ ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:7

“አንድ ሰው ብሩ ወይም ንብረቱ ያለ ሥጋት ይጠበቅለት ዘንድ ለጎረቤቱ ሰጥቶ ሳለ ቢሰርቅበትና፣ ሌባው ቢያዝ ዕጥፍ ይክፈል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 4:8

ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ ብቸኛ ሰው አለ፤ ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤ እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው? ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:28

እንደ ወንበዴ ታደባለች፤ በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:27

ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም፤ አይቷቸው እንዳላየ የሚሆን ግን ብዙ ርግማን ይደርስበታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 82:3

ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:6

“በዳኝነት ጊዜ በድኻው ላይ ፍርድ አታጓድልበት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:19

ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:94

እኔ የአንተ ነኝ፤ እባክህ አድነኝ፤ ሕግህንም ፈልጌአለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:24

የሌባ ግብረ አበር የገዛ ራሱ ጠላት ነው፤ የመሐላውን ርግማን እየሰማ ጭጭ ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:10

ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣ በቈፈረው ጕድጓድ ይገባል፤ ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 109:11

ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤ የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:1-3

እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስሙ፤ ስለሚደርስባችሁ መከራ አልቅሱ፤ ዋይ ዋይም በሉ። ወንድሞች ሆይ፤ በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያት የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ አድርጋችሁ ተመልከቱ። በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው። ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ፤ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል። ከእናንተ መካከል በመከራ ውስጥ ያለ አለ? እርሱ ይጸልይ፤ የተደሰተ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር። ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትም ሠርቶ ከሆነ፣ ይቅር ይባላል። ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል። ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም። እንደ ገናም ጸለየ፤ ዝናብም ከሰማይ ዘነበ፤ ምድርም ፍሬዋን ሰጠች። ወንድሞቼ ሆይ፤ ከእናንተ አንዱ ከእውነት ቢስትና ሌላው ቢመልሰው፣ ሀብታችሁ ሻግቷል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። ይህን አስተውሉ፤ ኀጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ሰው ነፍሱን ከሞት ያድነዋል፤ ብዙ ኀጢአትንም ይሸፍናል። ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጓል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ ለመጨረሻው ዘመን ሀብትን አከማችታችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 33:15

በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:13-14

“ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።” “በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።” “አፋቸው ርግማንና ምሬት ሞልቶበታል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:155

ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 21:13

“ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን፣ ‘የወንበዴዎች ዋሻ’ አደረጋችሁት” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 12:5

እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣ ስለ ድኾችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:7

ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤ ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 10:30-37

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠው፤ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በወንበዴዎች እጅ ወደቀ፤ ልብሱንም ገፍፈው ደበደቡት፤ በሞት አፋፍ ላይ ጥለውት ሄዱ። አንድ ካህን በአጋጣሚ በዚያው መንገድ ቍልቍል ሲወርድ አየውና ገለል ብሎ ዐለፈ። ደግሞም አንድ ሌዋዊ እዚያ ቦታ ሲደርስ አየውና እርሱም ገለል ብሎ ዐለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን እግረ መንገዱን ሲሄድ ሰውየው ወዳለበት ቦታ ደረሰ፤ ባየውም ጊዜ ዐዘነለት፤ ቀርቦም ቍስሎቹ ላይ ዘይትና የወይን ጠጅ አፍስሶ አሰረለት፤ በራሱም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማረፊያ ቤት ወሰደው፤ በዚያም ተንከባከበው። በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለማረፊያ ቤቱ ባለቤት ሰጠና፣ ‘ይህን ሰው ዐደራ አስታምመው፤ ከዚህ በላይ የምታወጣውንም ወጭ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ’ አለው። “እንግዲህ፣ ከእነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ሰው ባልንጀራ የሆነው የትኛው ይመስልሃል?” ሕግ ዐዋቂውም፣ “የራራለት ነዋ” አለ። ኢየሱስም፣ “አንተም ሂድና እንዲሁ አድርግ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:21-22

ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ ጻድቅ ግን ይቸራል። እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤ እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:6

ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑም፤ በሚሠሩትም ሰውነታቸውን መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸው ክፉ ነው፤ እጃቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞላ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:3

ቅኖችን ትክክለኛነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶች ግን በገዛ አታላይነታቸው ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:30

“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:118

መሠሪነታቸው በከንቱ ነውና፣ ከሥርዐትህ ውጭ የሚሄዱትን ሁሉ ወዲያ አስወገድሃቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:22

ሰው የሚመኘው ጽኑ ፍቅር ነው፤ ውሸታም ከመሆንም ድኻ መሆን ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 79:12

ጌታ ሆይ፤ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ የተዘባበቱትን መዘባበት፣ ሰባት ዕጥፍ አድርገህ አስታቅፋቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 56:2

ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣ እነዚህን የሚፈጽም ሰው ብፁዕ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 52:1

ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ? አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣ እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:17

እንግዲህ መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ እንዳለበት እያወቀ የማያደርግ ሰው ኀጢአት ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:25

ሰነፍን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤ እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:24

“ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወድዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:10

ሁለት ዐይነት ሚዛን፣ ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:13

ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 53:4

ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣ እግዚአብሔርንም የማይጠሩት፣ እነዚህ ክፉ አድራጊዎች ምንም አያውቁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:21

ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:16

ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 84:11

እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 9:17

“የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የበሉት ምግብ ይጥማል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 3:8

“ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ትሰርቁኛላችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት እንሰርቅሃለን?’ ትላላችሁ። “ዐሥራትና መባ ትሰርቁኛላችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:1

“እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች ጕረኖ በበሩ ሳይሆን፣ በሌላ በኩል ዘልሎ የሚገባ ሌባና ነጣቂ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 7:9

“ ‘ትሰርቃላችሁ፤ ሰው ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ በሐሰት ትምላላችሁ፤ ለበኣል ታጥናላችሁ፤ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ትከተላላችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:30

ሌባ በተራበ ጊዜ ራቡን ለማስታገሥ ቢሰርቅ፣ ሰዎች አይንቁትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 20:15

አትስረቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:1

“አንድ ሰው በሬ ወይም በግ ሰርቆ ቢያርድ ወይም ቢሸጥ በአንድ በሬ ምትክ ዐምስት በሬዎች፤ በአንድ በግ ምትክ አራት በጎች ይክፈል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 2:26

“ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፣ የእስራኤልም ቤት ዐፍሯል፤ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸውና ሹሞቻቸው፣ ካህናታቸውና ነቢያታቸው እንዲሁ ያፍራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 10:19

‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ አታታልል፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለውን ትእዛዝ ታውቃለህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:28

ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዳጄ መንፈስ ቅዱስ፥ አንተ መሪዬ፥ አጽናኝዬ እና ለዋጭዬ ነህ። ከኃጢአት ከሚያስረኝ ነገር ሁሉ እንድትፈታኝ እና እንድትረዳኝ እለምንሃለሁ። ቃልህ "የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካም ሥራ ይሥራ" ይላል። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ለመስረቅ ስል ላስፈራራኋቸውና ላዋረድኋቸው ሰዎች ሁሉ ይቅር በለኝ፤ በችግርም ሆነ በስንፍና ለሰረቅሁት ነገር ሁሉ ይቅር በለኝ። ውስጣዊ ሰውነቴን አድስና አጽናው፤ በማታለል ምኞት የተበላሸውን የቀደመውን ሰው እንዳስወግድና በሕይወቴ ለኃጢአት ቦታ እንዳልሰጥ እርዳኝ። ለስርቆት ከሚገፋፋኝ ከማንኛውም ምኞትና ነገር እወጣለሁ። ጌታ ሆይ፥ በመጥፎ የሚነኩኝንና ክፉ የሚመኙኝን ሰዎች ሁሉ ከመንገዴ አርቃቸው። ቃልህ "እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው" ይላል። ጌታ ሆይ፥ ኃጢአትን ድል አድርጌ በሮቹን እንድዘጋ፥ ልቤም ስርቆትን፥ ዝሙትን፥ የብልግና ምስሎችን፥ ውሸትን፥ ምኞትን፥ ስስትን፥ ምንዝርን እና ርኩሰትን ሁሉ እንዲጠላና እንዲጥል እርዳኝ። በኢየሱስ ስም፤ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች