Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


106 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ክህደት እና መናፍቅነት

106 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ክህደት እና መናፍቅነት

ከሃይማኖት ወይም ከፖለቲካ አቋም መመለስ፣ እንደ መዝገበ ቃላቱ አባባል፣ ክህደት ይባላል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መዝገበ ቃላት ደግሞ ከቀድሞ አቋም መራቅ ማለት እንደሆነ ያስረዳል። በመጀመሪያው ወደ ጢሞቴዎስ 4:1 ላይ እንደተገለጸው፣ በመጨረሻው ዘመን አንዳንዶች ከእምነታቸው እንደሚወጡ ተነግሯል፤ ይህም የሚሆነው በአሳሳች መናፍስትና በአጋንንት ትምህርቶች ተጽዕኖ ስር በመውደቃቸው ነው። እንደ ወደ ገላትያ ሰዎች በተጻፈው መልእክት ላይ እንደምናየው የእግዚአብሔርን ቃል የሚቀበሉ ሁሉ ጸንተው አይቆዩም። ከተቀበልነው ትምህርት የተለየ ማንኛውንም ትምህርት አለመቀበል አስፈላጊ መሆኑ በግልጽ ተነግሯል።

እንዳንታለል እግዚአብሔርን ጥበብና ራዕይ መፈለግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ማንኛውንም ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘን ይኖርብናል። በሁለተኛ ጴጥሮስ 1:19 ላይ እንደተገለጸው የትንቢት ቃልን በጨለማ ውስጥ እንደሚያበራ መብራት አድርገን ልንይዘው ይገባል።

የቤርያ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ለእኛ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። ከጳውሎስ እንኳን የተቀበሉትን ትምህርት በጥንቃቄ መርምረዋል። የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ከፍተኛ ባለሥልጣን አድርገው በመያዝ ትምህርቱን መርምረዋል። ይህ አመለካከት ከክህደት ይጠብቀናል።

በማቴዎስ 24:13 ላይ እንደተገለጸው እስከ መጨረሻው መጽናት አስፈላጊ ነው። ማን እንደጀመረ ሳይሆን ማን እስከ መጨረሻው እንደደረሰ ነው ዋናው። በክርስቶስ ያለንን አቋም አጥብቀን መያዝ ይኖርብናል።


ማቴዎስ 24:10-11

በዚያ ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ ይጠላላሉም። ብዙዎች ሐሰተኛ ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችን ያስታሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 1:6-7

በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ወንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:20-22

ትክክል ነው፤ እነርሱ የተሰበሩት ካለማመን የተነሣ ነው፤ አንተም በእምነት ቆመሃል፤ ፍራ እንጂ ትዕቢተኛ አትሁን። እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራላቸው፣ ለአንተም አይራራልህምና። እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭካኔ ተመልከት፤ ጭካኔውም በወደቁት ላይ ነው፤ ቸርነቱ ግን በቸርነቱ ውስጥ እስካለህ ድረስ ለአንተ ነው፤ አለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:1

ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 6:4-6

አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን፣ ሰማያዊውን ስጦታ የቀመሱትን፣ ከመንፈስ ቅዱስ ተካፋዮች የሆኑትን፣ መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኀይል የቀመሱትን፣ በኋላ ግን የካዱትን እንደ ገና ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም፤ ምክንያቱም እነርሱ ለገዛ ጥፋታቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደ ገና ይሰቅሉታል፤ ያዋርዱታልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ይሁዳ 1:4

ከረዥም ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና፤ እነርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው፣ የአምላካችንን ጸጋ በርኩሰት የሚለውጡና እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:19

ከእኛ መካከል ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ተለዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:14-15

በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:37

ልባቸው በርሱ የጸና አልነበረም፤ ለኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:24

“ጻድቅ ሰው ግን ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት ቢሠራ፣ ኀጢአተኛው የሚያደርገውንም አስጸያፊ ነገር ቢፈጽም፤ ይህ ሰው በውኑ በሕይወት ይኖራልን? ከሠራው ጽድቅ አንዱም አይታሰብለትም፤ ታማኝነቱን በማጕደሉና ከፈጸመው ኀጢአት የተነሣ ይሞታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:7-8

ሩጫችሁ መልካም ነበር፤ ታዲያ ያሰናከላችሁ፣ ለእውነትስ እንዳትታዘዙ የከለከላችሁ ማን ነው? እንዲህ ያለው ማባበል ከሚጠራችሁ የመጣ አይደለም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:21

ነገር ግን ሥር ባለመስደዱ ብዙ አይቈይም፤ በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት ሲመጣ ወዲያውኑ ይሰናከላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 95:8-9

በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ። ሥራዬን ቢያዩም፣ አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:21-23

ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በዐሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ። አሁን ግን ነቀፋና እንከን አልባ ቅዱስ አድርጎ በርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፣ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፤ ይህም የሚሆነው በእምነታችሁ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በመቆም ከሰማችሁት የወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው። እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ የተሰበከውም ወንጌል ይኸው ነው፤ እኔም ጳውሎስ ለዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆንሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:12

ስለዚህ ተደላድዬ ቆሜአለሁ የሚል ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 33:18-19

ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ክፉ ቢሠራ፣ ይሞትበታል። ክፉም ሰው ከክፉ ሥራው ተመልሶ ቀናውንና ትክክለኛውን ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:14

ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 4:3-4

ምክንያቱም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ትምህርት የማይቀበሉበት ጊዜ ይመጣል፤ ከዚህ ይልቅ ለገዛ ምኞቶቻቸው የሚስማማውን፣ የሚያሳክክ ጆሯቸው ሊሰማ የሚፈልገውን እንዲነግሯቸው በዙሪያቸው ብዙ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ። እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ዘወር ይላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:21-22

እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ቢሉም፣ ሞኞች ሆኑ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 29:13

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:14-15

ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:176

እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና፣ ባሪያህን ፈልገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:38

ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ ነፍሴ በርሱ ደስ አትሰኝም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:8

ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፣ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:21-23

“በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም። በዚያ ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’ ይሉኛል። በዚያ ጊዜ፣ ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዐመፀኞች፤ ከእኔ ራቁ’ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:36-39

ጣዖቶቻቸውንም አመለኩ፤ ይህም ወጥመድ ሆነባቸው። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ። የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፣ ለከነዓን ጣዖታት የሠዉአቸውን፣ ንጹሕ ደም አፈሰሱ፤ ምድሪቱም በደም ተበከለች። በተግባራቸው ረከሱ፤ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:4-5

እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፣ በደል የሞላበት ወገን፣ የክፉ አድራጊ ዘር፣ ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ትተዋል፤ የእስራኤልን ቅዱስ አቃልለዋል፤ ጀርባቸውንም በርሱ ላይ አዙረዋል። ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ? ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ? ራሳችሁ በሙሉ ታምሟል፤ ልባችሁ ሁሉ ታውኳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:8

ነገር ግን በራስ ወዳዶች፣ እውነትን ትተው ክፋትን በሚከተሉ ፍርድና ቍጣ ይደርስባቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:9

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን በመለማመድ አይቀጥልም፤ የርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 81:11-12

“ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤ እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ። ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 15:2

እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋራ ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋራ ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:10

ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:18-19

ምክንያቱም ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደ ነገርኋችሁ፣ አሁንም እንደ ገና፣ ያውም በእንባ እነግራችኋለሁ፤ ብዙዎች የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው በምድራዊ ነገር ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:24

ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻል የተመረጡትን ለማሳት ሲሉ ታላላቅ ምልክቶችንና ታምራትን ያደርጋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:1

ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:7

ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:38-39

ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣ ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:7

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:15

ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት፣ ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:10-11

አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:8

በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ወግና በዚህ ዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:27

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር፣ ሰውነቴን እየጐሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 1:19-20

እምነትና በጎ ኅሊናም ይኑርህ፤ አንዳንዶች ኅሊናቸውን ጥለው ባሕር ላይ አደጋ ደርሶበት እንደሚጠፋ መርከብ እምነታቸውን አጥፍተዋል። በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት፣ ሰላምም ይሁን። ከእነርሱም መካከል እንዳይሳደቡ ትምህርት ያገኙ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ይገኛሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 95:10

ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤ እኔም፣ “በልቡ የሳተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:6

በጎቼ በየተራራው ሁሉና በየኰረብታው ላይ ተንከራተቱ። በምድር ሁሉ ተበተኑ፤ የፈለጋቸውም፤ የፈቀዳቸውም የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:15

እንግዲህ ምን ይሁን? ከሕግ በታች ሳይሆን፣ ከጸጋ በታች በመሆናችን ኀጢአት እንሥራን? ከቶ አይሆንም!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 62:10

በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:11

እንግዲህ ማንም የእነዚያን አለመታዘዝ ምሳሌ ተከትሎ እንዳይወድቅ፣ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 10:32-33

“በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ ነገር ግን በሰው ፊት የሚክደኝን፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:12

ብንጸና፣ ከርሱ ጋራ ደግሞ እንነግሣለን። ብንክደው፣ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:14

እግዚአብሔርን ዘወትር የሚፈራ ሰው ብፁዕ ነው፤ ልቡን የሚያደነድን ግን መከራ ላይ ይወድቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:17

ለሰው ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በዚህ ምድር በእንግድነት ስትኖሩ በፍርሀት ኑሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:4

አመንዝሮች ሆይ፤ ከዓለም ጋራ ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋራ ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:2

የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:2

መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 125:5

ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ያስወግዳቸዋል። በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:1

እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! ለመሆኑ ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በፊት ለፊታችሁ በግልጽ ተሥሎ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:20

ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:13-16

“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም። “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ ሰዎችም መብራት አብርተው ከእንቅብ በታች አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ። እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:10

ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ምክንያቱም እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:25

የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው። አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 3:20-21

“ጻድቁ ሰው ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት ቢሠራ፣ እኔም መሰናክል በፊቱ ባስቀምጥ እርሱ ይሞታል፤ አንተ አላስጠነቀቅኸውምና በኀጢአቱ ይሞታል፤ ያደረገውም ጽድቅ አይታሰብለትም፤ አንተንም ስለ ደሙ በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ። ነገር ግን ጻድቁን ሰው ኀጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀውና እርሱም ኀጢአትን ባይሠራ፣ ተጠንቅቋልና በርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም ነፍስህን ታድናለህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 1:1-2

ብፁዕ ነው፣ በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፤ ነገር ግን ደስ የሚሠኘው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:24

“ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወድዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:15-17

ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤ ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም። ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:15

ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:27-28

ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፣ ለዘላለምም ትኖራለህ። እግዚአብሔር ፍትሕን ይወድዳልና፣ ታማኞቹንም አይጥልም። ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤ የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:20

እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 6:11-12

የተሰጠው ተስፋ እስኪፈጸም ድረስ እያንዳንዳችሁ እንዲህ ያለውን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። በእምነትና በትዕግሥት የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:1-2

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋራ ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን ፈልጉ፤ የፈጣሪውን መልክ እንዲመስል በዕውቀት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችኋል፤ በዚያ ግሪክ ወይም ይሁዲ፣ የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣ አረማዊ ወይም እስኩቴስ፣ ባሪያ ወይም ጌታ ብሎ ልዩነት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው። እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤ እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ። በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት። እንደ አንድ አካል ሆናችሁ የተጠራችሁበት የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። በርሱ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና እያቀረባችሁ፣ በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። ሚስቶች ሆይ፤ በጌታ ዘንድ ተገቢ በመሆኑ ለባሎቻችሁ ተገዙ። ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ መራራም አትሁኑባቸው። ሐሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 4:16

ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:1

ከብዙ ተግሣጽ በኋላ ዐንገቱን የሚያደነድን ሰው፣ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:4

በሕግ ለመጽደቅ የምትጥሩ፣ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፤ ከጸጋ ርቃችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:12

ሁሉም ተሳስተዋል፤ በአንድነት የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:118

መሠሪነታቸው በከንቱ ነውና፣ ከሥርዐትህ ውጭ የሚሄዱትን ሁሉ ወዲያ አስወገድሃቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:22

ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 13:5

በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 16:24-26

ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነገር ግን ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ያድናታል። ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው በነፍሱ ምትክ ሊከፍለው የሚችለው ዋጋ ምንድን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:21-22

እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራላቸው፣ ለአንተም አይራራልህምና። እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭካኔ ተመልከት፤ ጭካኔውም በወደቁት ላይ ነው፤ ቸርነቱ ግን በቸርነቱ ውስጥ እስካለህ ድረስ ለአንተ ነው፤ አለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:11

ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 73:27

እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ የሚያመነዝሩትን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:2

ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቷችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:1

ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:13

እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:7

ሩጫችሁ መልካም ነበር፤ ታዲያ ያሰናከላችሁ፣ ለእውነትስ እንዳትታዘዙ የከለከላችሁ ማን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:3

እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ በሰጣችሁ እምነት መጠን ራሳችሁን በአግባቡ መዝኑ እንጂ፣ ከሆናችሁት በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ እያንዳንዳችሁን እመክራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:6

ዳሩ ግን ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ ምክንያቱም የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚናወጥ የባሕር ማዕበል ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 18:1

ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 4:6-7

እግዚአብሔርም ቃየንን እንዲህ አለው፤ “ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቈረ? መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 101:3

በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:4

ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:30

“ከእኔ ጋራ ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋራ የማይሰበስብ ይበትናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:25

አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:10

በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ በልቡ ምስክር አለው፤ ማንም እግዚአብሔርን የማያምን ሁሉ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 4:1

በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጽ ይናገራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:21

የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት ይሻላቸው ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 1:8

ነገር ግን እኛም ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:10

በዚያ ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ ይጠላላሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 3:17

እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፤ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ፣ ጸንታችሁ ከቆማችሁበት መሠረት በዐመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:26-27

የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ተሰሎንቄ 2:3

ማንም ሰው በምንም መንገድ አያታልላችሁ፤ አስቀድሞ ዐመፅ ሳይነሣ፣ ለጥፋት የተመደበውም የዐመፅ ሰው ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 8:13

በድንጋያማ ቦታ ላይ የወደቀውም ቃሉን ሲሰሙ በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነዚህ ለጊዜው ያምናሉ እንጂ ሥር ስለሌላቸው በፈተና ጊዜ ፈጥነው የሚክዱ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 4:3

ምክንያቱም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ትምህርት የማይቀበሉበት ጊዜ ይመጣል፤ ከዚህ ይልቅ ለገዛ ምኞቶቻቸው የሚስማማውን፣ የሚያሳክክ ጆሯቸው ሊሰማ የሚፈልገውን እንዲነግሯቸው በዙሪያቸው ብዙ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 3:12

ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ ይህን ዕወቅ። አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዐላማዬን፣ እምነቴን፣ ትዕግሥቴን፣ ፍቅሬንና ጽናቴን ሁሉ ታውቃለህ፤ ስደቴንና መከራዬን፣ በአንጾኪያና በኢቆንዮን፣ በልስጥራንም የደረሰብኝን ሁሉ፣ የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከእነዚህ ሁሉ አዳነኝ። በርግጥም በክርስቶስ ኢየሱስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መኖር የሚወድዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። ክፉዎችና አታላዮች ግን እየሳቱና እያሳቱ፣ በክፋትም ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ። አንተ ግን በተማርኸውና በተረዳኸው ጽና፤ ይህን ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። ሰዎች ራሳቸውን የሚወድዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወድዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኵሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድዱ ይሆናሉና። ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘላለማዊ አምላክ፥ ልዑል ጌታ! አንተ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ለከፍተኛ ምስጋናና አምልኮ የሚገባህ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። ሰማያዊ አባታችን ሆይ፥ በኢየሱስ ስም ልቤንና አእምሮዬን እንድትጠብቅልኝ፥ ከዚህ ዓለም ፈተናዎችና ከክህደት እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ። መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል በፍርሃትና በክብር እንድጠብቅ፥ አንዲት ነጥብ ወይም አንዲት ፊደል እንዳልጨምርበት እርዳኝ። ጌታ ሆይ፥ የከሃዲዎች እርሾ ጸሎቴንና ያስተማርከኝን ትምህርት እንዳያበላሽ አትፍቀድ። ሁልጊዜ እንድተጉ እንድጸልይም፥ በሃይማኖቶች፥ በኑፋቄዎች፥ በማታለሎች ውስጥ እንዳልወድቅ፥ ከክፉው ፈተናዎች እንድትጠብቀኝ እርዳኝ። በቃልህ "በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቁ ጊዜያት እንዲመጡ ይህን እናውቅ። እነዚህ ሰዎች የአምልኮ መልክ ይኖራቸዋል፥ ኃይሉን ግን ይክዳሉ። ከእነዚህ ራቅ።" ብለሃል። በማታለል፥ በማደናገርና በማጭበርበር ቃላት ከመንገድህ ሊያስቱኝ የሚፈልግን ሁሉ ከመንገዴ አርቅልኝ። ቃልህን በድፍረት፥ በትሕትናና በቅንነት፥ ኢየሱስ ክርስቶስን እያነሳሁ፥ እንዲሰበክ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች