Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


106 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ግድያ

106 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ግድያ

ሕይወትና ሞት በእግዚአብሔር እጅ ነው። እሱ ነው የሰውን ዕድሜ የሚወስነው፤ እስትንፋስንም የሚሰጠው። ነገር ግን ከዘላለም ጀምሮ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር ጠላት አለ፤ እሱም ሁልጊዜ የሚያምረውን ፍጥረቱን፥ ማለትም የሰውን ዘር ለማጥፋት ይፈልጋል። ብዙ ሰዎች ያለጊዜያቸው ሞተዋል፤ ይህ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ስላልነበረ አይደለም፥ ነገር ግን ከዘላለማዊ ዓላማው ስለራቁ ነው። የጠላት ሠራዊት በየዕለቱ የሰዎችን ልብ እያደነደነ በምቀኝነት፥ በቅናት፥ በስንፍና፥ በግዴለሽነት እየሞላ እስከ ቅዝቃዜ ድረስ እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል። ማንም ሰው ነፍስ ለመግደል ተወስኖ አይወለድም። ችግሩ የሚመጣው ሰው ከእግዚአብሔር ራሱን ሲያርቅ ነው። የኃጢአት ባህሪያችን ወደ ክፉ ነገር ያዘነብለናል፤ ያለ እግዚአብሔር በኖርን ቁጥር ህይወታችን በጣም ይበላሻል፤ ብዙ ልቦችም ፈጣሪያቸውን ይክዳሉ። ሰዎች እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ አብ በሰማይ ያዝናል፤ በቃሉ «አትግደል» ብሎናል (ዘጸአት 20:13)። መግደል መፍትሔ አይደለም። እጅህን ከማርከስህ በፊት፥ በጸጸትም ከመዋጥህ በፊት ኢየሱስ ሊረዳህ ይፈልጋል። ነፍስህን ከሲኦል አድን፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ጠብቅ፤ ምሕረትንም ታገኛለህ። ፈራጅ መሆን የአንተ ድርሻ አይደለም፤ በዚህ ዓለም ያለው ብቸኛ አስታራቂ ኢየሱስ ከናዝሬት ነው። እየተታለልክ እንደሆነ እወቅ። አንድን ሰው መግደል ከሞት አያድንህም፤ ይልቁንም የራስህን ሕይወት ወደ ጥፋት ይወስደዋል። የእግዚአብሔር ቃል በዘሌዋውያን 24:17 «ሰው ሰውን ቢገድል፥ እርሱ ደግሞ መገደል አለበት» ይላል። በሰላም ለመኖር ጣር፤ በቅንነት ተመላለስ፤ እግርህንም ወደ ክፋት አታዘንብል። ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ ለኃጢአቶችህ ሁሉ ይቅርታን ለመጠየቅ ወደ እርሱ ተመለስ፤ በሰማይ የዘላለም ሕይወትን ታገኛለህ፤ በሲኦልም ከዘላለም ሥቃይ ትድናለህ።


ሮሜ 1:29

በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:21-22

“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘አትግደል፤ የገደለ ይፈረድበታል’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:9

“አታመንዝር”፣ “አትግደል”፣ “አትስረቅ”፣ “አትመኝ” የሚሉትና ሌሎችም ትእዛዞች ቢኖሩም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በዚህ በአንድ ሕግ ተጠቃልለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 9:6

“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣ ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል፣ እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:15

ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:38

የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፣ ለከነዓን ጣዖታት የሠዉአቸውን፣ ንጹሕ ደም አፈሰሱ፤ ምድሪቱም በደም ተበከለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 21:12

“ሰውን ደብድቦ የገደለ ሞት ይገባዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 5:17

አትግደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:14-15

ችግረኞችንና ድኾችን ለመጣል፣ አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣ ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ ቀስታቸውንም ገተሩ። ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:18

ሰውየውም፣ “የትኞቹን ትእዛዞች?” ሲል ጠየቀ። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አትግደል፣ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:16-17

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦ ትዕቢተኛ ዐይን፣ ሐሰተኛ ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆች፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:17

የሰው ደም ያለበት ሰው፣ ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ ማንም ሰው አይርዳው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:16-17

መሥዋዕትን ብትወድድ ኖሮ ባቀረብሁልህ ነበር፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም። እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:3

እጆቻችሁ በደም፣ ጣቶቻችሁ በበደል ተነክረዋል፤ ከንፈሮቻችሁ ሐሰትን ተናገሩ፤ ምላሶቻችሁ ክፉ ነገርን አሰሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:2

ትመኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙም። ትገድላላችሁ፤ በብርቱም ትመኛላችሁ፤ ልታገኙም አትችሉም። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 21:14

አንድ ሰው በተንኰል ሆነ ብሎ ሌላውን ቢገድል፣ ከመሠዊያዬ ተወስዶ ይገደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:158

ቃልህን አይጠብቁምና፣ ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:10

ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤ ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 3:3

ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 19:11-13

ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣ አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፣ ቢገድለውና ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፣ የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። አትራራለት፤ ነገር ግን መልካም እንዲሆንልህ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 27:12

ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ፤ የሐሰት ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፣ ዐመፃ የሚረጩ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:38-39

“ ‘ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ‘ክፉ አድራጊውን ሰው አትቃወሙት’፤ ነገር ግን ቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ አዙርለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 1:11-12

“ከእኛ ጋራ ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤ እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው በሙሉ እንዋጣቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 8:11

በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 140:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከዐመፀኞችም ሰዎች ጠብቀኝ፤ የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ፤ ዳግመኛም እንዳይነሡ ወደ እሳት ይጣሉ፤ ማጥ ወዳለበት ጕድጓድ ይውደቁ። ምላሰኛ በምድሪቱ ጸንቶ አይኑር፤ ዐመፀኛውን ሰው ክፋት አሳድዶ ያጥፋው። እግዚአብሔር ለድኻ ፍትሕን እንደሚያስከብር፣ ለችግረኛውም ትክክለኛ ፍርድን እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ። ጻድቃን በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ፤ ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ። እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ፤ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:6

የክፉዎች ቃል ደም ለማፍሰስ ታደባለች፤ የቅኖች ንግግር ግን ይታደጋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:19

ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:15

እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:52

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “በል ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፤ ሰይፍን የሚመዝዙ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 56:6

ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 24:16

አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:24

ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:155

ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 16:5

ሦራም አብራምን፣ “ለደረሰብኝ በደል ተጠያቂው አንተ ነህ፤ አገልጋዬ ዕቅፍህ ውስጥ እንድትገባ እኔው ሰጠሁህ፤ አሁን ግን ይኸው ማርገዟን ስታውቅ ትንቀኝ ጀመር፤ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ይፍረድ” አለችው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 14:21

ተነሥተው ምድርን እንዳይወርሱ፣ ዓለምንም በከተሞቻቸው እንዳይሞሉ፣ ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት፣ ወንድ ልጆቹ የሚታረዱበትን ስፍራ አዘጋጁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:15

ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 10:15

የክፉውንና የበደለኛውን ክንድ ስበር፤ የእጁንም ስጠው፤ ምንም እስከማይገኝ ድረስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 27:24-25

“በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። “ንጹሕን ሰው ለመግደል ጕቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:12

ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:17

ግልፍተኛ ሰው የቂል ተግባር ይፈጽማል፤ መሠሪም ሰው አይወደድም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:119

የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 26:21

በምድር ላይ የሚኖረውን ሕዝብ ስለ ኀጢአቱ ለመቅጣት፣ እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያው ወጥቶ ይመጣል፤ ምድር በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤ የተገደሉትንም ከእንግዲህ አትሸሽግም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 139:19-22

አምላክ ሆይ፤ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት! ደም የተጠማችሁ ሰዎች ሆይ፤ ከእኔ ራቁ! አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ። ስለ አንተ በክፉ ሐሳብ ይናገራሉና፤ ጠላቶችህም ስምህን በከንቱ ያነሣሉ። እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚጠሉህን አልጠላምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልጸየፍምን? በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ፤ ባላጋራዎቼም ሆነዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 21:20-21

“አንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት ባሪያውን በዱላ ቢመታና ባሪያውም በዚህ የተነሣ ቢሞት መቀጣት አለበት፤ ነገር ግን ከአንድ ወይም ከሁለት ቀን በኋላ ባሪያው ቢነሣ መቀጣት የለበትም፤ ባሪያው ንብረቱ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 55:23

አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 9:18

ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤ ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:14-15

እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን በደል ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይልላችሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 3:15

እንዲህ ያለችዋ ጥበብ ከላይ አይደለችም፤ ነገር ግን ከምድር፣ ከሥጋና ከአጋንንት ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 21:1-9

አምላክህ እግዚአብሔር እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ተገድሎ ሜዳ ላይ ቢገኝና ገዳዩም ማን እንደ ሆነ ባይታወቅ፣ ከጠላቶችህ ጋራ ጦርነት ልትገጥም ወጥተህ አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶህ በማረክህ ጊዜ፣ ከምርኮኞቹ መካከል መልከ መልካም ሴት አይተህ ብትማርክህ፣ ሚስትህ ልታደርጋት ትችላለህ። ወደ ቤትህ ውሰዳት፤ ጠጕሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቍረጥ። ስትማረክ የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፤ እቤትህ ተቀምጣ ለአባትና ለእናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፣ ልትደርስባትና ባል ልትሆናት፣ እርሷም ሚስት ልትሆንህ ትችላለች። በርሷ ደስተኛ ባትሆን፣ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና ልትሸጣት ወይም እንደ ባሪያ ልትቈጥራት አይገባህም። አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፣ አንደኛዋን የሚወድዳት፣ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኵር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወድዳት ሚስቱ ቢሆን፣ ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፣ የብኵርናን መብት ከማይወድዳት ሚስቱ ከወለደው በኵር ልጅ ገፎ፣ ከሚወድዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤ ይልቁንም ከተጠላችው ሚስቱ ለተወለደው ልጅ ካለው ሀብት ሁሉ ሁለት እጅ ድርሻውን በመስጠት ብኵርናውን ያስታውቅ፤ ያ ልጅ የአባቱ ኀይል መጀመሪያ ነውና፣ የብኵርና መብት የራሱ ነው። አንድ ሰው፣ የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፣ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፣ አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፤ ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ ወጥተው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ አንሥቶ በአቅራቢያው እስካሉት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። “ይህ ልጃችን እልከኛና ዐመፀኛ ነው፤ አይታዘዘንም፤ አባካኝና ሰካራም ነው” ብለው ለከተማው አለቆች ይንገሯቸው። ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል። አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና በድኑ በዕንጨት ላይ ቢሰቀል፣ በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ፣ በዚያ ዕለት ቅበረው። ከዚያም ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፣ ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን ዐንገት ይስበሩ፤ እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጕዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህ እግዚአብሔር መርጧቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ። ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ባለችው ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፣ በሸለቆው ውስጥ፣ ዐንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ። እንዲህም ብለው ይናገሩ፤ “እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ተቤዠኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።” ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል። አንተም በእግዚአብሔር ፊት ቀና የሆነውን ስታደርግ፣ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:32-33

ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ ሊገድሉትም ይሻሉ። እግዚአብሔር ግን በእጃቸው አይጥለውም፤ ፍርድ ፊት ሲቀርብም አሳልፎ አይሰጠውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:13

ሰነፍ፣ “አንበሳ በውጭ አለ፤ በጐዳና ላይ እገደላለሁ” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:21

እንግዲህ አንተ ሌሎችን የምታስተምር፣ ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ፣ ትሰርቃለህን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:126

እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣ ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:7-8

እግሮቻቸው ወደ ኀጢአት ይሮጣሉ፤ ንጹሕ ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ የሚያስቡት ክፉ ሐሳብ ነው፤ በመንገዶቻቸው ጥፋት እና መፍረስ ይገኛሉ። የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በጐዳናቸውም ፍትሕ የለም፤ መንገዳቸውን ጠማማ አድርገውታል፤ በዚያም የሚሄድ ሰላም አያገኝም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:35

“ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:29

ክፉ ሰው ባልንጀራውን ያባብለዋል፤ መልካም ወዳልሆነውም መንገድ ይመራዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 79:10

ሕዝቦች፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ? የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም በቀል፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦች ይወቁት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:20

ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:36

ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰዎች ስለ ተናገሩት ከንቱ ቃል ሁሉ በፍርድ ቀን ይጠየቁበታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 140:3

ምላሳቸውን እንደ እባብ ያሾላሉ፤ ከከንፈራቸውም በታች የእፉኝት መርዝ አለ። ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:15-17

“እግሮቻቸው ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ በመንገዶቻቸው ጥፋትና ጕስቍልና ይገኛሉ፤ የሰላምንም መንገድ አያውቁም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 137:8-9

አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤ በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሽው ድርጊት፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ ብፁዕ ነው፤ ብፁዕ ነው፤ ሕፃናትሽንም ይዞ፣ በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 2:22

ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይወገዳሉ፤ ታማኝነት የጐደላቸውም ከርሷ ይነቀላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 3:15

ሕዝቤን በችግር ስታደቅቁት፣ የድኾችንም ፊት በሐዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 7:17

እጅግ ክፉ አትሁን፤ ሞኝም አትሁን፤ ለምንስ ያለ ቀንህ ትሞታለህ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 5:6

ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 27:11-12

እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ ስለ ጠላቶቼም፣ በቀና መንገድ ምራኝ። ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ፤ የሐሰት ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፣ ዐመፃ የሚረጩ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 33:15

በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:25-26

“የከሰሰህ ባላጋራህ እንዳያስፈርድብህ፣ ዳኛውም ለአገልጋዩ አሳልፎ እንዳይሰጥህ፣ ወደ ወህኒ እንዳትጣል፣ በመንገድ ላይ ሳለህ ከባላጋራህ ጋራ ፈጥነህ ተስማማ። እውነት እልሃለሁ፤ ካስፈረደብህ ግን የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ አትወጣም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 79:11

የእስረኞች ሰቈቃ በፊትህ ይድረስ፤ በክንድህም ብርታት፣ ሞት የተፈረደባቸውን አድን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:13

ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:28

በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ፤ በዚያ ጐዳና ላይ ሞት የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 109:16

ድኻውንና ችግረኛውን፣ ልቡም የቈሰለውን፣ እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:33

አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኛነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 36:1-4

ክፉውን ሰው፣ በደል በልቡ ታናግረዋለች፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ በዐይኖቹ ፊት የለም። ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው። የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤ የክፉውም ሰው እጅ አያሳድደኝ። ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት! በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና። ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል። በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ ክፋትንም አያርቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:10

“ከእነዚህ ከታናናሾች መካከል አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ እላችኋለሁና፤ በሰማይ ያሉት መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉ፤ [

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:6

ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑም፤ በሚሠሩትም ሰውነታቸውን መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸው ክፉ ነው፤ እጃቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞላ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 4:15

እግዚአብሔር ግን፣ “የለም! እንደርሱ አይሆንም፤ ማንም ቃየንን ቢገድል፣ ሰባት ዕጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው፤ ስለዚህ፣ ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው እግዚአብሔር በቃየን ላይ ምልክት አደረገለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 58:10

ጻድቃን በቀልን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤ እግራቸውንም በግፈኞች ደም ይታጠባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:36

ይህም፣ “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቈጥረናል” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:12

ክፋት ስለሚገንን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:15

በደለኛውን ማጽደቅ ሆነ፣ ጻድቁን በደለኛ ማድረግ፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 11:5

እግዚአብሔር ጻድቁንና ክፉውን ይመረምራል፤ ዐመፃን የሚወድዱትን ግን፣ ነፍሱ ትጠላቸዋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 140:4

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፤ እግሮቼንም ለመጥለፍ ከሚያደቡ ዐመፀኞች ሰውረኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:41

“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 42:22

ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣ በጕድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣ በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ ተበዝብዘዋል፣ የሚያድናቸውም የለም፤ ተማርከዋል፣ “መልሷቸው” የሚልም የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 69:27

በበደላቸው በደል ጨምርባቸው፤ ወደ ጽድቅህም አይግቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:12

ጻድቃን ድል ሲነሡ ታላቅ ደስታ ይሆናል፤ ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ይሸሸጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 101:5

ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣ አጠፋዋለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣ እርሱን አልታገሠውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:7

ከሐሰት ክስ ራቅ፤ በደል የሌለበትን ወይም ጻድቁን ሰው ለሞት አሳልፈህ አትስጥ፣ በደለኛውን ንጹሕ አላደርግምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:14

ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤ ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 3:8

ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:23

ሞኝ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤ አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:20

የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 24:17

“ ‘ሰውን ደብድቦ የገደለ ይገደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 21:8

ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 20:13

አትግደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:21

“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘አትግደል፤ የገደለ ይፈረድበታል’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:2

“አንድ ሌባ በር ሲሰብር ተይዞ ቢደበደብና ቢሞት፣ ተከላካዩ የደም ባለዕዳ አይሆንም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘኍል 31:7

እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋራ ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘኍል 31:17

አሁንም ወንዶቹን ልጆች ሁሉ፣ ወንድ ያወቁትንም ሴቶች በሙሉ ግደሏቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:12

የክፉው ወገን ሆኖ ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየን አትሁኑ፤ ለምን ገደለው? ምክንያቱም የርሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር አባቴ ሆይ፤ ታማኝና ቸር አምላክ፤ ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን! ዛሬ በኢየሱስ ስም ወደ አንተ እቀርባለሁ፤ ከክፉ አድራጊዎችና ከደም አፍሳሾች እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ። የክብር አምላክ ሆይ፤ ልቤን ከክፉ ሀሳብ ሁሉ አንጻ፤ እጄንም ከርኩሰት ሁሉ እንድታነጻልኝ እለምንሃለሁ። ንጹሕ ደም ከማፍሰስ ጠብቀኝ። የሰይጣን ፈተና እንዳያታልለኝ፤ በቁጣና በንዴት ጊዜ የሥጋዬን ምኞት እንዳላስፈጽም እርዳኝ። መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ሕይወቴ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን፤ በጊዜዬ፣ በአገልግሎቴ፣ በሰጠኸኝ ጸጋና ችሎታ ሁሉ እንድትመራኝ እለምንሃለሁ። የመንፈስ ቅዱስህን ቅባት በላዬ አፍስስ፤ ታሰሩትን ለመርዳት ኃይልህ በላዬ ያድር። ያለፍኩትን፣ የአሁኑንና የወደፊት ሕይወቴን ሁሉ በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ጌታ ሆይ፤ ለኃጢአት የከፈትኳቸውን በሮች ሁሉ በቀንበር አፍራሽ ቅባትህ ዝጋልኝ፤ ከክፉ ሁሉ አድነኝ። ቃልህ «አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የሚገድል ሁሉ ፍርድ ይገባዋል» ይላል። የተወደድክ አባት ሆይ፤ አንተ ቀናተኛ አምላክ እንደሆንክ ልቤ ይረዳ፤ በልጆችህ ላይ፣ በማንኛውም ሰው ላይ ክፉ እንዳላስብ። ጌታ ሆይ፤ ቂም በልቤ ሲያድር፣ የበቀል ስሜት ሲሰማኝ፣ ልቤ በየዋህነትና በትሕትና በፊትህ እንዲቆም እርዳኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን!
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች