Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


115 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፤ ዓለምና ምኞት

115 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፤ ዓለምና ምኞት

ዓለማችን ብዙ ውጣ ውረድና ፈተና የሞላባት ናት። ውስብስብና አታላይም ልትሆን ትችላለች። አንዳንዴ ውብና ማራኪ ብትመስልም፣ ይህችን ዓለም ለመውደድ መኖር የለብንም። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ነው ዋናው ዓላማችን። አንደኛ የዮሐንስ መልእክት 2:17 ላይ «ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል» ይላል።

መጽሐፍ ቅዱስ የዓለምን እሴቶችና አኗኗር እንዳንከተል፣ በእግዚአብሔር መርሆችና ትምህርቶች መሠረት እንድንኖር ያስተምረናል። የራሳችንን ፍላጎት ለማርካት ከመኖር ይልቅ፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳችንን አስገዝተን፣ እርሱ የሚፈልገውን እና የሚያስደስተውን አኗኗር መከተል ይገባናል።

አሁን የምታየው ሁሉ አንድ ቀን ይጠፋል፤ ትዝታው እንኳን አይቀርም። ስለዚህ ዓይንህን በእምነታችን ራስና ፈጻሚ በሆነው በኢየሱስ ላይ እንድታኖር እመክርሃለሁ። ወደ ቆሎሴ ሰዎች 3:2 «ከላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም» ይላል።

ዓለምንና ምኞቱን አለመውደድ ማለት ከኅብረተሰብ መገለል ማለት አይደለም። በዓለም ውስጥ ብንኖርም፣ በዓለም መመዘኛዎችና አኗኗር አላንቀረጽም። በጨለማ ውስጥ ጨውና ብርሃን መሆን አለብን። በፍቅር፣ በፍትሕና በምሕረት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሕግ ለዓለም ማሳየት አለብን።


1 ዮሐንስ 2:15

ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:4

አመንዝሮች ሆይ፤ ከዓለም ጋራ ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋራ ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:2

መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:15-17

ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤ ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም። ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 8:36

ሰው ዓለሙ ሁሉ የርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 10:3

የምንኖረው በዚህ ዓለም ቢሆንም፣ የምንዋጋው በዚህ ዓለም ስልት አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:16-17

እንግዲህ በመንፈስ ኑሩ እላለሁ፤ የሥጋንም ምኞት አትፈጽሙም። ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን፣ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን ይመኛልና፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚጋጩ፣ የምትፈልጉትን አታደርጉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 16:33

“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:10

ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:11-12

ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጧልና፤ ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:24

“ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወድዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:17

ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:11

ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:16

ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:4

ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሸንፈውም እምነታችን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:13

በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:27

ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:9

ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:14

ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 8:12

ኢየሱስ እንደ ገና ለሰዎቹ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:5

ደግሞም ይህን ዕወቁ፤ ማንም አመንዝራ ወይም ርኩስ ወይም ስግብግብ፣ ይኸውም ጣዖት አምላኪ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 16:26

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው በነፍሱ ምትክ ሊከፍለው የሚችለው ዋጋ ምንድን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላላወቀው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:5

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:27

በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳትና ከዓለም ርኩሰት ራስን መጠበቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:8

ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፣ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:2

ሐሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:4

ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ፣ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:5-6

እንደ ሥጋ የሚኖሩ ሐሳባቸውን በሥጋ ፍላጎት ላይ ያሳርፋሉ፤ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን ሐሳባቸውን በመንፈስ ፍላጎት ላይ ያደርጋሉ። የሥጋን ነገር ማሰብ ሞት ነው፤ የመንፈስን ነገር ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 3:16

በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:18

“ዓለም ቢጠላችሁ፣ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:19

ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ፣ ዓለም የራሱ እንደ ሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር፤ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኋችሁ የዓለም አይደላችሁም፤ ዓለም የሚጠላችሁም ስለዚሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:4

ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:19

እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋራ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:2-3

በዚህም፣ የዓለምን ክፉ መንገድ ተከትላችሁ፣ በአየር ላይ ላሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ ለሆነውና አሁንም ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤ በርሱ ሕንጻ ሁሉ አንድ ላይ ተገጣጥሞ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል። እናንተም ደግሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ ዐብራችሁ እየተገነባችሁ ነው። እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞት እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 3:17

እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በርሱ ለማዳን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:5-6

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞትና አምልኮተ ጣዖት የሆነው መጐምጀት ናቸው። በእነዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙት ላይ ይመጣል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:9

እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 6:17

“ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤ ተለዩም፤ ይላል ጌታ። ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:12-13

ስለዚህ ክፉ መሻቱን ትፈጽሙ ዘንድ በሟች ሥጋችሁ ላይ ኀጢአት እንዲነግሥበት አታድርጉ። ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:8

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 7:31

በዚህ ዓለም ነገር የሚጠቀሙም እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ፤ የዚህ ዓለም መልክ ዐላፊ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 4:3-5

የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤ ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤ ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:22

ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋራም ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከታተል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:2-4

ከዚህም የተነሣ ከእንግዲህ በሚቀረው ምድራዊ ሕይወት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ምኞት አይኖርም። አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል። ይህን በመሰለ ብኩን ሕይወት ከእነርሱ ጋራ ስለማትሮጡ እንግዳ ሆኖባቸው በመደነቅ ይሰድቧችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:14-15

ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:17

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:22-24

ቀድሞ ስለ ነበራችሁበት ሕይወትም፣ በሚያታልል ምኞቱ የጐደፈውን አሮጌ ሰውነታችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ ደግሞም በአእምሯችሁ መንፈስ እንድትታደሱ፣ እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:15

ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:28

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ሴትን በምኞት ዐይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከርሷ ጋራ አመንዝሯል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:23

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:22

ከማንኛውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:13

እንደ ሥጋ ብትኖሩ ትሞታላችሁና፤ ክፉ የሆነውን የሥጋ ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ ግን፣ በሕይወት ትኖራላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:5

ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 7:18

በእኔ፣ ማለትም ኀጢአተኛ በሆነው ተፈጥሮዬ ውስጥ ምንም በጎ ነገር እንደማይኖር ዐውቃለሁ፤ በጎ የሆነውን የማድረግ ምኞት አለኝ፤ ነገር ግን ልፈጽመው አልችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:3

ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሣ፤ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:7

እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:24-25

ስለዚህም እግዚአብሔር በኀጢአት በተሞላው የልባቸው ምኞት እርስ በርሳቸው የገዛ አካላቸውን እንዲያስነውሩ ቅድስና ለሌለው ሩካቤ ሥጋ አሳልፎ ሰጣቸው። የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው። አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:27

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር፣ ሰውነቴን እየጐሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 10:3-5

የምንኖረው በዚህ ዓለም ቢሆንም፣ የምንዋጋው በዚህ ዓለም ስልት አይደለም። ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው። በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:24

የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋራ ሰቅለውታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:1

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:20

ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:33

አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኛነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 17:14-16

ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ፣ እነርሱም ከዓለም ባለመሆናቸው ዓለም ጠልቷቸዋል። የምለምንህም ከክፉው እንድትጠብቃቸው እንጂ፣ ከዓለም እንድታወጣቸው አይደለም። እኔ ከዓለም እንዳልሆንሁ ሁሉ፣ እነርሱም ከዓለም አይደሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 3:3

አሁንም ሥጋውያን ናችሁ፤ በመካከላችሁ ቅናትና ክርክር አለ። ታዲያ፣ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? ተግባራችሁስ እንደ ማንኛውም ሰው ተግባር መሆኑ አይደለምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 6:11

የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:37

ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤ በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 6:18

ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:19-21

“ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። “ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤ ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 11:25

ለጥቂት ጊዜ በኀጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ፣ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋራ መከራን መቀበል መረጠ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 101:3

በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:31-32

መልኩ ቀይ ሆኖ፣ በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ ሰተት ብሎ በሚወርድበትም ጊዜ፣ ወደ ወይን ጠጅ ትክ ብለህ አትመልከት። በመጨረሻው እንደ እባብ ይነድፋል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:29

እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 4:12

ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 6:14

ከማያምኑ ሰዎች ጋራ አግባብ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋራ ምን ግንኙነት አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋራ ምን ኅብረት አለው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:8

አሁን ግን ቍጣን፣ ንዴትን፣ ክፋትን፣ ስድብንና አሳፋሪ ንግግርን የመሳሰሉትንም ሁሉ አስወግዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:22

በእሾኽ መካከል የተዘራው ዘር ቃሉን ሰምቶ ለዚህ ዓለም በመጨነቅና በብልጽግና ሐሳብ በመታለል ታንቆ ያላፈራን ሰው ይመስላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:9

ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:14-16

ታዛዦች ልጆች እንደ መሆናችሁ መጠን ቀድሞ ባለማወቅ ትኖሩበት የነበረውን ክፉ ምኞት አትከተሉ። ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤ ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፏል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:33

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:20

ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኩሰት ካመለጡ በኋላ እንደ ገና ተጠላልፈው ቢሸነፉ፣ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታቸው የከፋ ይሆንባቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:7-8

ለኀጢአት የተገዛ አእምሮ ከእግዚአብሔር ጋራ ጠበኛ ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛም፤ መገዛትም አይችልም። በሥጋ የሚመሩትም እግዚአብሔርን ማስደሰት አይችሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 5:11

ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋራ እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋራ ምግብ እንኳ አትብሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:11

ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋራ ምንም ዐይነት ግንኙነት አይኑራችሁ፤ ይልቁን ግለጡት፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ ይህን ዕወቅ። አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዐላማዬን፣ እምነቴን፣ ትዕግሥቴን፣ ፍቅሬንና ጽናቴን ሁሉ ታውቃለህ፤ ስደቴንና መከራዬን፣ በአንጾኪያና በኢቆንዮን፣ በልስጥራንም የደረሰብኝን ሁሉ፣ የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከእነዚህ ሁሉ አዳነኝ። በርግጥም በክርስቶስ ኢየሱስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መኖር የሚወድዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። ክፉዎችና አታላዮች ግን እየሳቱና እያሳቱ፣ በክፋትም ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ። አንተ ግን በተማርኸውና በተረዳኸው ጽና፤ ይህን ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። ሰዎች ራሳቸውን የሚወድዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወድዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኵሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድዱ ይሆናሉና። ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 1:10

ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ ዕሺ አትበላቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:16

ራሳችሁን እንደ ባሪያ አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ለምትታዘዙት ለርሱ፣ ይኸውም ወደ ሞት ለሚወስደው ለኀጢአት ወይም ወደ ጽድቅ ለሚያደርሰው ለመታዘዝ ባሮች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:8

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 1:10

አሁን እኔ ተቀባይነት ለማግኘት የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሠኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሠኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:3

በርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 8:14

በእሾኽ መካከል የወደቀውም ቃሉን የሚሰሙት ናቸው፤ እነዚህም ውለው ዐድረው በምድራዊ ሕይወት ጭንቀት፣ በባለጠግነትና ተድላ ደስታ ታንቀው በሚገባ አያፈሩም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:14

ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 3:11-12

እንግዲህ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ የሚጠፋ ከሆነ፣ እናንተ እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል? አዎን፣ በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት ልትኖሩ ይገባችኋል፤ ደግሞም የእግዚአብሔርን ቀን እየተጠባበቃችሁ መምጫውን ልታፋጥኑ ይገባል። በዚያ ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በታላቅ ትኵሳት ይቀልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:15

ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:1

እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:32

ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል የሚለውን ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:31

እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:17

በርሱ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና እያቀረባችሁ፣ በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:15

በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 141:4

ከዐመፀኞች ጋራ፣ በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣ ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤ ከድግሳቸውም አልቋደስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 16:19

የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:6

ማንም በርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:22

እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን ስላነጻችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ ቅን ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:10

አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:13-14

“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:6

ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ የሚመጣው በእንደዚህ ዐይነት ነገር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:6

እንግዲህ እንንቃ፤ ራሳችንንም እንግዛ እንጂ እንደሚያንቀላፉት እንደ ሌሎቹ አንሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:13

ስለዚህ እርስ በርሳችን፣ አንዱ በሌላው ላይ ከመፍረድ እንቈጠብ፤ በዚህ ፈንታ ግን በወንድምህ መንገድ ላይ የማሰናከያ ድንጋይ ወይም ወጥመድ እንዳታስቀምጥ ቍርጥ ሐሳብ አድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 13:5

በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:21

ስለዚህ ርኩሰትንና ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ክፋትን አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን፣ በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 16:13

ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ መልካም አምላኬ፥ አመሰግንሃለሁ። ሕይወቴ በሙሉ የተቀደሰ ስምህን ይባርክ። አንተ ከፍ ያልክና ታላቅ ነህ፤ ለዘላለም ክብር ላንተ ይሁን። አንተ ኃይሌ፥ መጠጊያዬ፥ ነፃ አውጪዬም ነህ። ነፍሴ በፍቅርህ ታምናለች። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ታማኝነትህንና ምሕረትህን አሳይተኸኛል። ድምፅህ ስሜን ሲጠራ እነቃለሁ፤ ስተኛም አንተ ትጠብቀኛለህ። ላደረግኸውና ላደረግኸው ሁሉ አመሰግንሃለሁ። በቃልህ ውስጥ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ስላገኘሁ አመሰግንሃለሁ። ዛሬ በፈቃድህ እንድኖር እርዳኝ። ከሁሉም በላይ እንድወድህ እርዳኝ። በሕይወቴ ውስጥ ቅድሚያ የምትሰጠው አንተ እንድትሆንና ምንም ነገር ከፊትህ እንዳያርቀኝ እፈልጋለሁ። በስሜቴና በስሜቴ እንዳልመራ እርዳኝ። እይታዬን በዚህ ዓለም ነገሮች ላይ ከማድረግ ጠብቀኝ። እይታዬ በአንተ ላይ እንዲያርፍ እፈልጋለሁ። ቃልህ እንደሚለው፥ ትኩረቴን በሰማያዊ ነገሮች ላይ እንጂ በምድራዊ ነገሮች ላይ አላደርግም። በኢየሱስ ስም፥ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች