ልጄ ሆይ፣ ባህላችን ሴቶችን በትሕትናቸው፣ በመታዘዛቸውና በመሥዋዕትነታቸው ብቻ እንዲታወቁ ሊያደርግ ይችላል። ነፃነታቸውና ተሰጥኦአቸው ብዙም አይታይም። እንደ አባታቸው ንብረት አድርገው ያዩአቸዋል፣ በኋላም እንደ ባሎቻቸው። የቤት ውስጥ ሥራና የልጅ አስተዳደግ ብቻ እንደሚያንሷቸው አድርገው ያስባሉ። በእስራኤልም ሕዝብ ቆጠራ ላይ እንኳን አይቆጠሩም ነበር። ግን እግዚአብሔር ይህንን ቀይሮታል። እኛን ልዩ ዋጋ ሰጥቶናል፤ ለአገልግሎቱም ብቁና ዋጋ እንዳለን አድርጎናል።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለው ዓላማ በሰው ልጅ አስተሳሰብ ዝቅ ተደርጎ ቢታይም፣ በታሪክ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ብዙ አንስት ጀግኖች አሉ። እግዚአብሔር በእነርሱ በኩል ታላላቅ ተአምራትን አድርጓል። እስቴርን፣ ሩትን፣ ዲቦራን፣ ናኦሚን፣ ረዓብን፣ ማርያምን፣ ሣራን፣ ራሔልን፣ ርብቃንና ሌሎችንም ታሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ስለእነዚህ ሴቶች አጥኚ። ከምስክርነታቸው ብርታትን አግኝተሽ ሕይወትሽን ሙሉ በሙሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ እንድትሰጪ ተነሣሽ። እርሱ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚፈልገው መልስ አንቺ ሁኚ።
ፈርዖንም ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱ ኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።
የሥጋህ ቍራጭ የዐጥንትህ ፍላጭ ከሚሆኑት፣ ከምትወልዳቸው ልጆችህ አንዳንዶቹ በምርኮ ይወሰዳሉ፤ በባቢሎንም ቤተ መንግሥት ጃንደረቦች ይሆናሉ።”
ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት። ይህን ያለውም፣ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ይለኛልና።
ነገር ግን ንጉሡ፣ የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን፤ የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደችለትን ዐምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤
የሰውየው ስም ናባል፣ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።
ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።
የሔቤር ሚስት ኢያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፣ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፣ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋራ ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።
ላሜሕ ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የአንደኛዋ ስም ዓዳ፣ የሁለተኛዋም ሴላ ነበር። ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ፣ ቃየንም ዐራሽ ነበር። ዓዳ ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ከብት አርቢዎች አባት ነበረ። ወንድሙም ዩባል ይባላል፤ እርሱም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበረ። ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።
ዮአኪን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። እናቱ ኔስታ ትባላለች፤ እርሷም የኢየሩሳሌም ሰው የኤልናታን ልጅ ነበረች።
ከአሳፍ ወንዶች ልጆች፤ ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። የአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሡ አመራር ሥር ነበረ።
ኢያሪኮን እንዲሰልሉ ኢያሱ የላካቸውን ሰዎች ስለ ደበቀች፣ ጋለሞታዪቱን ረዓብን፣ ቤተ ሰቧንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ አዳናቸው፤ እርሷም እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤላውያን መካከል ትኖራለች።
ዳዊትም አቢግያን እንዲህ አላት፤ “ዛሬ እንድታገኚኝ ወደ እኔ የላከሽ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። ደም እንዳላፈስስና በገዛ እጄ እንዳልበቀል ዛሬ ስለ ጠበቅሽኝ ስለ በጎ ሐሳብሽ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ።
ከዚያም ናታን የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ አላት፤ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን? አሁንም የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት እንዴት ማዳን እንደምትችዪ ልምከርሽ፤
የሳኦል ቁባት የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችውን ዳዊት በሰማ ጊዜ፣ ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ወሰደ፤ የኢያቢስ ገዦች፣ ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ ከገደሉ በኋላ እነርሱን ከሰቀሉት ከቤትሳን አደባባይ በድብቅ ወስደዋቸው ነበር። ዳዊትም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከዚያ አመጣ፤ እንዲሁም የእነዚያን የተገደሉትን ሰዎች ዐፅም ሰበሰቡ። የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም በብንያም አገር ጼላ በተባለ ስፍራ በሳኦል አባት በቂስ መቃብር ቀበሩት፤ ንጉሡ ያዘዘውንም ሁሉ አደረጉ። ከዚያ በኋላም ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት እግዚአብሔር ሰማ።
ንጉሥ ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን ማለትም ሞዓባውያትን፣ አሞናውያትን፣ ኤዶማውያትን፣ ሲዶናውያትን፣ ኬጢያውያትን አፈቀረ።
ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ዳዊት ሰላምታውን እንዲያቀርቡለት ከምድረ በዳ ወደ ጌታችን መልእክተኞችን ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን የስድብ ናዳ አወረደባቸው።
እግዚአብሔርም፣ “ጊዜው ሲደርስ በርግጥ በዚህ ጊዜ በሚቀጥለው ዓመት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። ሣራም በዚህ ጊዜ ከበስተጀርባው ካለው ከድንኳኑ ደጃፍ ሆና ትሰማ ነበር።
አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ሄደ። በዚያም አንዲት ሀብታም ሴት ነበረች፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር ምግብ ለመብላት ወደ ቤቷ ይገባ ነበር።
ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም የቦጽቃት አገር ሰው የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች።
ንጉሥ ሰሎሞንም ለሳባ ንግሥት ከቤተ መንግሥቱ በልግስና ከሚሰጣት ሌላ፣ የፈለገችውንና የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ከዚያም ከአጃቢዎቿ ጋራ ወደ አገሯ ተመለሰች።
አብራምንም፣ “እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋራ ተኛ” አለችው። አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ።
እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው። ስለዚህ እርሱ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት።
ወንድሞቹና እኅቶቹ፣ ቀድሞም ያውቁት የነበሩ ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ በቤቱም ከርሱ ጋራ ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘናቸውን ገለጡለት፤ እግዚአብሔርም ካመጣበት መከራ ሁሉ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።
መኳንንቱ ሁሉ የኩሲን ልጅ የሰሌምያን ልጅ የናታንያን ልጅ ይሁዲን፣ “ለሕዝቡ ያነበብኸውን ብራና ይዘህ እንድትመጣ” ብለው ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ብራናውን ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤
እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
በማግስቱም አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሟት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር።
ኤልሳዕም፣ “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው። ሴትዮዋም ፀነሰች፤ ኤልሳዕ እንደ ነገራትም በተባለው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች።
መላው የሰራዊቱ ጦር አለቆችና ሰዎቻቸው የባቢሎን ንጉሥ፣ አገረ ገዥ አድርጎ ጎዶልያስን መሾሙን ሲሰሙ፣ እርሱ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፤ እነርሱም የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ የነጦፋዊው የተንሑሜት ልጅ ሠራያ የማዕካታዊው ልጅ ያእዛንያና ሰዎቻቸው ነበሩ።
እርሱም ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ፣ እነሆ፤ ከአብርሃም ወንድም ከናኮርና ከሚስቱ ከሚልካ የተወለደው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች።
እርሱም የአክዓብን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም የእስራኤል ነገሥታት የሄዱበትን መንገድ ተከተለ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።
ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦርና፣ ሳፋን፣ ዓሳያም የሐርሐስ የልጅ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የአልባሳት ጠባቂውን የሴሌምን ሚስት ነቢዪቱን ሕልዳናን ለመጠየቅ ሄዱ። እርሷም ምክር በጠየቋት ቦታ፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው የከተማው ክፍል ትኖር ነበር።
ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።
ኬልቅያስና ንጉሡ ከርሱ ጋራ የላካቸው ሰዎች የአልባሳት ጠባቂ የነበረው የሐስራ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የሴሌም ሚስት ወደሆነችው ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄደው ነገሯት። እርሷም በኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው የከተማው ክፍል ትኖር ነበር።
ንጉሥ ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን ማለትም ሞዓባውያትን፣ አሞናውያትን፣ ኤዶማውያትን፣ ሲዶናውያትን፣ ኬጢያውያትን አፈቀረ። ምንም እንኳ ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል ሰሎሞንን ቢከለክለውም፣ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልጠበቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “ይህን በማድረግህ ያዘዝሁህን ኪዳኔንና ሥርዐቴንም ባለመጠበቅህ፣ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጠዋለሁ፤ ይህን ግን ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ስል በዘመንህ አላደርገውም፤ መንግሥትህን የምቀድዳት ከልጅህ እጅ ነው። ይህም ሆኖ መንግሥቱን በሙሉ አልነጥቀውም፤ ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊትና ስለ መረጥኋት ስለ ኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።” እግዚአብሔር ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ኤዶማዊውን ሃዳድን በሰሎሞን ላይ አስነሣው። ከዚያ በፊት ዳዊት ከኤዶም ጋራ በተዋጋ ጊዜ፣ የሞቱትን ለመቅበር መጥቶ የነበረው የሰራዊቱ አዛዥ ኢዮአብ የኤዶምን ሰዎች ሁሉ ፈጅቶ ነበር። ኢዮአብና እስራኤላውያን ሁሉ፣ በኤዶም ያሉትን ወንዶች በሙሉ እስኪያጠፉ ድረስ፣ እዚያው ስድስት ወር ቈይተው ነበርና። ሃዳድ ግን ገና በልጅነቱ አባቱን ካገለገሉ ጥቂት ኤዶማውያን ጋራ ወደ ግብጽ ሸሸ፤ እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከፋራንም ሰዎች ይዘው ወደ ግብጽ በመምጣት፣ ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገቡ። ንጉሡም ለሃዳድ ቤትና መሬት ሰጠው፤ ቀለብም አዘዘለት። ፈርዖንም ሃዳድን እጅግ ወደደው፤ ስለዚህም ከሚስቱ ከንግሥት ጣፍኔስ እኅት ጋራ አጋባው። እነዚህም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን፣ “ልባችሁን ወደ አማልክታቸው በርግጥ ይመልሱታልና ከእነርሱ ጋራ መጋባት የለባችሁም” ካላቸው አሕዛብ ወገን ነበሩ፤ ሆኖም ሰሎሞን ከእነዚሁ ጋራ ፍቅሩ ጠና።
እግዚአብሔር ግን ለአኪያ፣ “እነሆ፤ የኢዮርብዓም ሚስት ስለ ታመመው ልጇ ልትጠይቅህ ሌላ ሴት መስላ ትመጣለችና እንዲህ ብለህ መልሳት” ብሎ ነገረው።
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጕዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ሄደች፤ ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ፤ እጅ ከነሣትም በኋላ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ንጉሡም ለእናቱ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።
ስለዚህ ተነሥቶ ወደ ሰራፕታ ሄደ። ወደ ከተማዪቱ በር እንደ ደረሰም፣ አንዲት መበለት ጭራሮ ስትለቃቅም አገኛት፤ ጠርቶም፣ “የምጠጣው ውሃ በዕቃ ታመጪልኛለሽን?” ሲል ለመናት። ልታመጣለት ስትሄድ አሁንም ጠራትና፣ “እባክሽን፣ ቍራሽ እንጀራም ይዘሽልኝ ነይ” አላት። እርሷም መልሳ፣ “አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ዕፍኝ ዱቄትና በማሰሮ ካለው ጥቂት ዘይት በቀር ምንም የለኝም። እነሆ፤ ለራሴና ለልጄ ምግብ አዘጋጅቼ በልተን እንድንሞት ጭራሮ ለቃቅሜ ወደ ቤት ልወስድ ነው” አለችው። ኤልያስም መልሶ እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ወደ ቤት ገብተሽ እንዳልሽው አድርጊ፤ በመጀመሪያ ግን ከዚያችው ካለችሽ ትንሽ ዕንጐቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ ከዚያም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር ለምድሪቱ ዝናብ እስከሚሰጥበት ዕለት ድረስ፤ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም።’ ” እርሷም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ በዚህ ሁኔታም ኤልያስ፣ መበለቲቱና ቤተ ሰቧ ብዙ ቀን ተመገቡ፤ በኤልያስ በተነገረው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም ነበርና።
በዚህ ጊዜ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ “እነግሣለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ስለዚህ ሠረገሎችንና ፈረሶችን እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሄዱ ዐምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።
የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፣ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው።
አቢግያም ጊዜ አላጠፋችም፤ ሁለት መቶ እንጀራ፣ ሁለት አቍማዳ የወይን ጠጅ፣ ዐምስት የተሰናዱ በጎች፣ ዐምስት መስፈሪያ የተጠበሰጠ እሸት፣ መቶ የወይን ዘለላና ዘቢብ፣ ሁለት መቶ ጥፍጥፍ የበለስ ፍሬ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች።
አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት ያደረገውን መልካም ነገር በእግዚአብሔር ፊት አላደረገም።
ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። እናቱ ናዓማ የተባለች አሞናዊት ነበረች። ልጁ አብያም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
ሰሎሞን የግብጽ ንጉሥ የፈርዖን ወዳጅ ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ። እርሱም ቤተ መንግሥቱን፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጥር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አስቀመጣት።
እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው።
በአሦር ንጉሥ በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ኢያዔል ድንኳን ሮጠ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “እርሷ በሌላ ሰው የምትወደድ አመንዝራ ብትሆንም፣ አሁንም ሂድና ሚስትህን ውደዳት፤ ወደ ሌሎች አማልክት ዘወር ቢሉና ለእነርሱም የተቀደሰውን የዘቢብ ጥፍጥፍ ቢወድዱም፣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንደ ወደዳቸው አንተም እርሷን ውደዳት።”
በዚህ ጊዜ ዔሊ እጅግ አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በመላው እስራኤል ያደርጉ የነበረውን፣ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋራ ዝሙት መፈጸማቸውን ሰማ።
ንጉሡም ጋታዊውን ኢታይን እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋራ የመጣኸው ለምንድን ነው? ተመለስና ከንጉሡ ከአቤሴሎም ጋራ ተቀመጥ፤ አንተ ለራስህ ከአገርህ ተወስደህ የመጣህ እንግዳ ነህ፤
ሚስቱ ኤልዛቤልም፣ “አንተ አሁን የእስራኤል ንጉሥ ትባላለህ? በል ተነሥና እህል ቅመስ፤ ደስም ይበልህ፤ የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እኔ እንድታገኝ አደርግሃለሁ” አለችው።
የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። ቅመማ ቅመም፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋራ ደረሰች፤ ወደ ሰሎሞንም ቀርባ በልቧ ያለውን ሁሉ አጫወተችው።
በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን፣ ከአብያ የክህነት ምድብ የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ነገድ ስትሆን፣ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ።
በዚህ ጊዜ አክዓብ በሰማርያ ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስለዚህ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ ለኢይዝራኤል ሹማምት፣ ለሽማግሌዎችና የአክዓብን ልጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ወደ ሰማርያ ላከ፤ መልእክቱም እንዲህ የሚል ነበር፤
በዚህ ጊዜ ሴቶች ከሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፣ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ እንዲሁም ሰሎሜ ነበሩ፤
ከዚያም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራት ተነሡ፤ የሚያግዟቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ዐብረዋቸው ነበሩ።
በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱ የዘካርያስ ልጅ ስትሆን፣ ስሟ አቢያ ይባል ነበር።
ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ዳዊት ሰላምታውን እንዲያቀርቡለት ከምድረ በዳ ወደ ጌታችን መልእክተኞችን ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን የስድብ ናዳ አወረደባቸው። እነዚህ ሰዎች ግን እጅግ መልካም ነበሩ፤ ጕዳትም አላደረሱብንም፤ በዱር ዐብረናቸው በነበርንበት ጊዜም ሁሉ፣ ምንም ነገር አልጠፋብንም። በጎቻችንን እየጠበቅን ዐብረናቸው ባሳለፍነው ጊዜ ሁሉ፣ ቀንም ሆነ ሌሊት በዙሪያችን ዐጥር ሆነውን ነበር።
እንደ ገና ፀንሳ አሁንም ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስሙንም ይሁዳ ብላ ጠራችው። ከዚያም በኋላ መውለድ አቆመች።
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቍ እጅግ ትበልጣለች። ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም። በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም። የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወድዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች። እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች። ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤ በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች። ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው። ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤ በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም። በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤ በጣቶቿም ዘንጉን ታሾራለች። “ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤ የስእለቴ ልጅ ሆይ፤ ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣ እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች። በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና። ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች። ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው። የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች። ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤ መጪውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች። በጥበብ ትናገራለች፤ በአንደበቷም ቀና ምክር አለ። የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤ የስንፍና እንጀራ አትበላም። ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤ ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤ አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።” ጕልበትህን በሴት አትጨርስ፤ ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል። ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት። የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።
ቂስ የተባለ አንድ ታዋቂ ብንያማዊ ሰው ነበረ፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፣ የጽሮር ልጅ፣ የብኮራት ልጅ፣ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር። ሳኦልም፣ “መልካም፤ ና እንሂድ” አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፣ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፣ “ባለራእዩ እዚህ ነውን?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፣ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ፣ ለመብላት ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን እርሱ መባረክ ስላለበት፣ እርሱ እስኪመጣ ድረስ ሕዝቡ መብላት አይጀምርም፤ ከዚያ በኋላ የተጋበዘው ሕዝብ ይበላል፤ አሁኑኑ ውጡ፤ ወዲያው ታገኙታላችሁ።” እነርሱም ወደ ከተማዪቱ ወጡ፤ ወደ ከተማዪቱም በመግባት ላይ ሳሉ፣ እነሆ፤ ሳሙኤል ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ለመውጣት እነርሱ ወዳሉበት አቅጣጫ መጣ። ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል ይህን እንዲህ ሲል ገልጾለት ነበር፤ “ነገ በዚህ ጊዜ ከብንያም ምድር አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንዲሆን ቅባው፤ እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋል። እነሆ፤ ሕዝቤን ከላይ ተመልክቻለሁ፤ ጩኸቱ ከእኔ ዘንድ ደርሷልና።” ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ እግዚአብሔር፣ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም ሕዝቤን ይገዛል” አለው። ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፣ “የባለራእዩ ቤት የት እንደ ሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው። ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋራ ስለምትበሉ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጧት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ። ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።