1 ተሰሎንቄ 5:18በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።
ቈላስይስ 3:15እንደ አንድ አካል ሆናችሁ የተጠራችሁበት የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
መዝሙር 100:4በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤
ኤፌሶን 5:20በዚህም እግዚአብሔር አብን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር ሁልጊዜ አመስግኑ።
መዝሙር 118:1እግዚአብሔር ቸር ነውና አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ፊልጵስዩስ 4:6በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ።
መዝሙር 34:1እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።
ሮሜ 1:21እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።
መዝሙር 30:12እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።
መዝሙር 69:30የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አወድሳለሁ፤ በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
ቈላስይስ 1:12በቅዱሳን ርስት በብርሃን ተካፋዮች ለመሆን ያበቃንን አብን እንድታመሰግኑ ነው።
መዝሙር 145:10እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።
መዝሙር 92:1እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤
ማቴዎስ 15:36ሰባቱን እንጀራና ዓሣውን ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ አከፋፈሉ።
መዝሙር 86:12ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤
መዝሙር 9:1እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።
መዝሙር 50:14“ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ።
መዝሙር 71:14እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።
1 ተሰሎንቄ 1:2በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን።
መዝሙር 147:7ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
መዝሙር 42:11ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና።
ዕብራውያን 13:15ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት፣ ይኸውም ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ።
መዝሙር 33:2እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።
መዝሙር 8:1እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሏል።
መዝሙር 149:1ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።
መዝሙር 145:7የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።
መዝሙር 32:11ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ።
መዝሙር 63:5ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።
መዝሙር 104:33በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ።
መዝሙር 103:20-21እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፣ ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፣ ሰራዊቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ።
መዝሙር 9:2በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።
መዝሙር 75:1አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ስምህ ቅርብ ነውና ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ሰዎችም ስለ ድንቅ ሥራህ ይናገራሉ።
መዝሙር 138:2ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ ስምህንና ቃልህን፣ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
መዝሙር 33:1ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል።
መዝሙር 147:1ሃሌ ሉያ። አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው! እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።
መዝሙር 116:17ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
መዝሙር 111:1ሃሌ ሉያ። በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
መዝሙር 73:28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ።
መዝሙር 7:17ስለ ጽድቁ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ስም በመዝሙር አወድሳለሁ።
ዕብራውያን 12:28ስለዚህ ከቶ የማይናወጥ መንግሥት ስለምንቀበል እግዚአብሔርን እናመስግን፤ ደግሞም ደስ በሚያሠኘው መንገድ በአክብሮትና በፍርሀት እናምልከው፤
መዝሙር 66:8ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
መዝሙር 103:22እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣ ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።
መዝሙር 105:1እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አሳውቁ።
መዝሙር 9:11በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤
መዝሙር 106:1ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
መዝሙር 27:6በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣ ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤ በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤ እዘምርለታለሁም።
መዝሙር 28:7እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።
ኢሳይያስ 12:4በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
መዝሙር 111:2የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።
ምሳሌ 3:5በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤
መዝሙር 45:17ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል።
መዝሙር 66:4ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤ በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ ለስምህም ይዘምራሉ።” ሴላ
1 ዜና መዋዕል 29:10ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል አመሰገነ፤ “የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ይሁን።
መዝሙር 138:1በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ “በአማልክት” ፊት በመዝሙር አወድስሃለሁ።
ኢሳይያስ 25:1እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፣ ድንቅ ነገር፣ በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።
መዝሙር 103:1ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ።
መዝሙር 145:1አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።
መዝሙር 92:2ምሕረትህን በማለዳ፣ ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤
መዝሙር 100:3እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የርሱ ነን፤ እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።
መዝሙር 30:4እናንተ የምትታመኑት፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።
መዝሙር 138:4እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፍህን ቃል በሰሙ ጊዜ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመስግኑህ።
መዝሙር 116:19ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ። ሃሌ ሉያ።
መዝሙር 22:27የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤ የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣ በፊቱ ይሰግዳሉ።
መዝሙር 48:1እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል።
መዝሙር 67:3እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
መዝሙር 98:4ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
ሮሜ 15:11እንደ ገናም፣ “አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወድሱት” ይላል።
መዝሙር 41:13የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን፤ አሜን፤ አሜን።
መዝሙር 100:5እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
መዝሙር 139:14ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።
መዝሙር 47:1ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
ሮሜ 6:13ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
መዝሙር 95:6ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤
መዝሙር 149:5ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤ በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።
መዝሙር 66:5ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ፤ በሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!
መዝሙር 91:15ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
መዝሙር 107:8እግዚአብሔርን ልክ ስለሌለው ፍቅሩ፣ ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤
ሮሜ 8:28እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።
መዝሙር 71:23ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።
መዝሙር 145:2በየቀኑ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።
መዝሙር 63:4እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
መዝሙር 116:2ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
ዕብራውያን 10:23የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ።