Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


109 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ እውነተኝነት

109 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ እውነተኝነት

በምሳሌ 12:22 ላይ "በውሸት የሚናገር ከንፈር ለእግዚአብሔር አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን ደስታው ናቸው" ይላል። ይህ ሐቀኛ መሆን እግዚአብሔርን የምናስደስትበት መንገድ መሆኑን ያሳየናል።

ሐቀኝነት እውነትን ከመናገር ባለፈ በሁሉም ሁኔታዎች ፍትሃዊና ትክክለኛ በሆነ መንገድ መመላለስን ይጨምራል። በኤፌሶን 4:25 ላይ "ውሸትን አስወግዱ፤ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተናገሩ፤ እኛ የአንድ አካል ብልቶች ነንና" ተብለናል። ስለዚህ ሐቀኝነታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነትም እንደሚነካ ማስታወስ አስፈላጊ ነው።

በመዝሙር 15:2 ላይ "በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ማን ይኖራል? በንጹሕ መንገድ የሚሄድ፣ ጽድቅን የሚያደርግ፣ እውነትንም ከልቡ የሚናገር" የሚል ኃይለኛ ጥያቄ እናገኛለን። ይህ ሐቀኝነት ከውስጣችን የሚመነጭ ባሕርይ መሆን እንዳለበት፣ በአንደበታችን ብቻ የሚወጣ ሳይሆን፣ በሐሳባችንና በተግባራችንም ጭምር እውነተኛና ግልጽ መሆን እንዳለብን ያስታውሰናል።

በሮሜ 12:17 ላይ "ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ" ተብለናል። ይህም ሌሎች በእኛ ላይ በደል ቢያደርሱብን እንኳ ፍትሃዊና ሐቀኛ በሆነ መንገድ መመላለስ እንዳለብን ያስተምረናል።

በአጠቃላይ ሐቀኝነት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ወሳኝ እሴት ነው። ሐቀኝነትን ስንለማመድ ለእግዚአብሔር ታዛዥነታችንን እናሳያለን፣ ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነትም እናጠናክራለን።


ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:15

እንደማያፍርና የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያስረዳ የተመሰከረለት ሠራተኛ፣ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ልታቀርብ ትጋ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:1

እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:25

ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋራ እውነትን ተነጋገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ነንና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 16:10

“በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ በትልቁም ይታመናል፤ በትንሽ ነገር ያልታመነ በትልቁም አይታመንም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:18

ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:9

አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋራ አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:3

ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:3

ቅኖችን ትክክለኛነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶች ግን በገዛ አታላይነታቸው ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 1:6

ከርሱ ጋራ ኅብረት አለን እያልን በጨለማም ብንመላለስ፣ እንዋሻለን፤ እውነቱንም አናደርግም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:10

ስለዚህ፣ “ሕይወትን የሚወድድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 20:16

በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:7

ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ከሆነ ግብርን፣ ቀረጥ ከሆነም ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባውም ክብርን ስጡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:8

ከጽድቅ ጋራ ጥቂቱ ነገር፣ በግፍ ከሚገኝ ብዙ ትርፍ ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:8

ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 3:17

ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ ዕሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና ግብዝነት የሌለባት ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:27

ማድረግ እየቻልህ ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ አትቈጠብ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 8:21

ምክንያቱም ዐላማችን በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን፣ በሰውም ፊት መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:2

ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:37

ስለዚህ ስትነጋገሩ ቃላችሁ፣ ‘አዎን’ ከሆነ ‘አዎን’፤ ‘አይደለም’ ከሆነ ‘አይደለም’ ይሁን፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ከክፉው የሚመጣ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:22

እግዚአብሔር ሐሰተኛ ከንፈርን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ደስ ይለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 2:9

በዚያ ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣ መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 112:5

ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 19:7

አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ማጣመም፣ አድልዎ ማድረግና መማለጃ መቀበል ስለሌለ ተጠንቅቃችሁ ፍረዱ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:11

ሐቀኛ መስፈሪያና ሚዛን ከእግዚአብሔር ናቸው፤ በከረጢት ውስጥ ያሉት መመዘኛዎችም ሁሉ ሥራዎቹ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:12

ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:9

ሐቀኛ ሰው ያለ ሥጋት ይራመዳል፤ በጠማማ ጐዳና የሚሄድ ግን ይጋለጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:1

ንግግሩ ጠማማ ከሆነ ሞኝ ሰው ይልቅ፣ ያለ ነውር የሚሄድ ድኻ ሰው ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:11

“ ‘አትስረቁ። “ ‘አትዋሹ። “ ‘ከእናንተ አንዱ ሌላውን አያታልል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:19

እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 24:16

ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ንጹሕ ኅሊና እንዲኖረኝ ሁልጊዜ እጥራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:1

“የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:21

አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 15:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል? አካሄዱ የቀና፣ ጽድቅን የሚያደርግ፤ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:13

አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:16-19

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦ ትዕቢተኛ ዐይን፣ ሐሰተኛ ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆች፣ ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣ በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:5

ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:6

እነሆ፤ እውነትን ከሰው ልብ ትሻለህ፤ ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:15

ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:7

ጻድቅ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት ይመራል፤ ከርሱም በኋላ የሚከተሉት ልጆቹ ብፁዓን ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:1-4

“ሰዎች እንዲያዩላችሁ፣ መልካም ሥራችሁን በፊታቸው ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ከሰማዩ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም። መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን። የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን። እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን። ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉው አድነን እንጂ፤ መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም ለዘላለሙ ያንተ ነውና፤ አሜን። ’ እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን በደል ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይልላችሁም። “ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ እነርሱ መጾማቸው እንዲታወቅላቸው ሆነ ብለው በፊታቸው ላይ የሐዘን ምልክት ያሳያሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። አንተ ግን በምትጾምበት ጊዜ ፊትህን ታጠብ፤ ራስህንም ተቀባ፤ በዚህም መጾምህ በስውር ያለው አባትህ ብቻ የሚያውቀው፣ ከሰዎች ግን የተሰወረ ይሆናል፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል። “ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። “ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤ ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና። “ዐይን የሰውነት መብራት ነው፤ ስለዚህ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ መላው ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። ዐይንህ ታማሚ ከሆነ ግን መላው ሰውነትህ በጨለማ የተሞላ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ድቅድቅ ይሆን? “ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወድዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም። “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ኑሯችሁ ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? በማለት አትጨነቁ። ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን? እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? ለመሆኑ፣ ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ሰዓት መጨመር የሚችል ማን ነው? “ደግሞስ ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? እስኪ የሜዳ አበቦችን ተመልከቱ፤ አይለፉም፤ ወይም አይፈትሉም። ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነርሱ እንደ አንዷ አልለበሰም። እናንተ ግን ለድኾች ስትሰጡ፣ ቀኝ እጃችሁ የሚያደርገውን ግራ እጃችሁ አይወቅ፤ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ እሳት የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ? ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት አጥብቀው ይሻሉና፤ የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል። ስለዚህ ለነገ በማሰብ አትጨነቁ፤ የነገ ጭንቀት ለነገ ይደር፤ እያንዳንዱ ዕለት የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለውና። ምጽዋታችሁ በስውር ይሁን፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባታችሁም ዋጋችሁን ይከፍላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:6

በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣ መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:17

ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:29

የሽንገላን መንገድ ከእኔ አርቅ፤ ሕግህን በጸጋህ ስጠኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:13

በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:12

ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ፤ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:35-36

“ ‘በመስፈሪያ ወይም በሚዛን አታጭበርብሩ። የጽድቅ መለኪያ፣ የጽድቅ ሚዛን፣ የጽድቅ የኢፍ መስፈሪያ፣ የጽድቅ የሂን መስፈሪያም ይኑራችሁ። ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 4:6

በዚህም ነገር ማንም ተላልፎ ወንድሙን አያታልል፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ እንደ እነዚህ ያለውን ኀጢአት ሁሉ የሚፈጽሙትን ይበቀላል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:26

እውነተኛ መልስ መስጠት፣ ከንፈርን እንደ መሳም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:13

ነገሥታት በታማኝ ከንፈሮች ደስ ይላቸዋል፤ ጽድቅ የሚናገረውን ሰው ይወድዱታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 8:16-17

ልታደርጓቸው የሚገባችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም እውነትንና ትክክለኛ ፍርድን አስፍኑ፤ በባልንጀራችሁ ላይ ክፋትን በልባችሁ አታውጠንጥኑ፤ በሐሰት መማልን አትውደዱ፤ እነዚህን ሁሉ እጸየፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 26:1

እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 33:15

በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 12:24

ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አትርሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 1:47

ኢየሱስም፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ፣ “እነሆ፤ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ” አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:7

አንደበቴ እውነትን ይናገራል፤ ከንፈሮቼ ክፋትን ይጸየፋሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:32

የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤ የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 2:3-4

የምናቀርበው ልመና ከስሕተት ወይም ከክፉ ዐላማ ወይም እናንተን ለማታለል ከመፈለግ የመነጨ አይደለም። ነገር ግን ወንጌልን በዐደራ ለመቀበል እግዚአብሔር ብቁ አድርጎ እንደ ቈጠራቸው ሰዎች ሆነን እንናገራለን። ይህንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን እንጂ ሰዎችን ደስ ለማሠኘት ብለን አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:9

ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ክፉ የሆነውን ሁሉ ተጸየፉ፤ በጎ ከሆነው ነገር ጋራ ተቈራኙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 101:7

አታላይ የሆነ ማንም ሰው፣ በቤቴ ውስጥ አይኖርም፤ ሐሰትን የሚናገር፣ በፊቴ ቀና ብሎ አይቆምም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:7

በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:17

ሐቀኛ ምስክር በእውነት ይመሰክራል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸት ይናገራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 18:21

ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 8:15

በመልካም መሬት ላይ የወደቀውም ቃሉን ቅንና በጎ በሆነ ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፣ ታግሠውም በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:5

ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:32

እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:16

ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፏል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:4

ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 40:10

ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን፣ ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 12:15

ለሠራተኞቹ እንዲከፍሉ ገንዘቡ የተሰጣቸው ሰዎች ፍጹም ታማኞች በመሆናቸው ተቈጣጣሪ ማድረግ አላስፈለጋቸውም ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:22

ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 13:6

ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 6:3-4

አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ ለማንም ዕንቅፋት መሆን አንፈልግም። ይሁን እንጂ በምናደርገው ነገር ሁሉ ራሳችንን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች እናቀርባለን፦ በብዙ ትዕግሥት፣ በመከራ፣ በችግር፣ በጭንቀት፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:16

መልካም ነው ብለህ የምታስበው ነገር ክፉ ተብሎ እንዲነቀፍ አታድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 19:8

ዘኬዎስ ግን ቆመና ጌታን፣ “ጌታ ሆይ፤ እነሆ ካለኝ ሀብት ሁሉ ግማሹን ለድኾች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ቀምቼ ከሆነ፣ አራት ዕጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 15:5

ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣ በንጹሓን ላይ ጕቦ የማይቀበል። እነዚህን የሚያደርግ፣ ከቶ አይናወጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:18

ለእኛ ደግሞ ጸልዩልን። በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚናፍቅ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን ርግጠኞች ነን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:25

እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:17

በርሱ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና እያቀረባችሁ፣ በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:16

በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ አክፋፍተው የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:33

እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን መማር ነው፤ ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:163

ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ፤ ሕግህን ግን ወደድሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:2

መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:28

ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:23

ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ አባይ ሚዛን አይወደድም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:7

መልካም አነጋገር ለሞኝ አይሰምርለትም፤ ለገዥ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆን!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:6

በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 141:3

እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:5

ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:18

በክፋታቸው እውነትን ዐፍነው በሚይዙ፣ በዐመፃቸውና በክፋታቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:8-9

በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ። ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 18:21

አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:5-6

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:20

ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 22:16

ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋራ ወደ እርሱ ልከው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉን እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:20

የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 5:6

ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 6:31

ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:5

የጻድቃን ሐሳብ ቀና ነው፤ የክፉዎች ምክር ግን ሸር አለበት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:3-4

ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትሕትና ቍጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ። እርሱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለማሟላት ሲል ለሕይወቱ እንኳ ሳይሣሣ፣ ለክርስቶስ ሥራ ከሞት አፋፍ ደርሶ ነበርና። እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:5

ለፍጹማን ሰዎች ጽድቃቸው መንገዳቸውን ታቃናላቸዋለች፤ ክፉዎች ግን በገዛ ክፋታቸው ይወድቃሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:18-19

እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል። በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤ በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:24

ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤ ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 27:5

የተገለጠ ዘለፋ፣ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:6

በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 4:24

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 23:23

“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ ወዮላችሁ! ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት እየሰጣችሁ በሕጉ ውስጥ ዋነኛ የሆኑትን ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና ታማኝነትን ግን ንቃችኋልና፤ እነዚያን ሳትተዉ እነዚህን ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:27

ጻድቃን አታላዮችን ይጸየፋሉ፤ ክፉዎችም ቅኖችን ይጠላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 25:14

የማይለግሰውን ስጦታ እቸራለሁ ብሎ ጕራ የሚነዛ ሰው፣ ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

ክብርና ምስጋና የሚገባህ ውድ አምላኬ ፈጣሪዬ፤ ለዘላለም ከፍ ከፍ ትላለህ። አንተ የኔ እድል፣ የኔ ዝማሬ፣ የኔ ደስታ ነህ። የኔ ሰላም፣ የኔ መጠጊያ፣ የኔ አለኝታ ነህ። ያንተ እርዳታ ከሌለኝ ምንም ማድረግ አልችልም። በአንተ እኖራለሁ፣ በአንተ እተነፍሳለሁ። ለኔ ላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ። ስለ ይቅርታህ፣ ስለ ምህረትህ አመሰግናለሁ። በየማለዳው ስለምትጠራኝ፣ ስለ ታማኝነትህ አመሰግናለሁ። ከእኔ ጋር ስለሆንክ፣ እጄን ስለማትለቅ አመሰግናለሁ። ያለኝ ሁሉ ከአንተ እንደሆነ አውቃለሁ። ጌታ ሆይ፣ በቅድስና እንድኖር እርዳኝ። የልቤ ሃሳብ ሁልጊዜ ንጹህ ይሁን። ልቤ እንደ አንተ ልብ ይሁን። የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ሁልጊዜ በእኔ ይታይ። በአንተ እመራ፣ በእውነትህም ጸንቼ እኖር። እውነተኛ እንድሆን፣ ከአፌ የሚወጣው ቃል በፊትህ እንደ መልካም ሽታ ይሁን። በበደልና በክፋት መኖር አልፈልግም። አንተ የምትፈልገውን ሁሉ አደርጋለሁ። እንደ አምሳልህ እንድሆን በእግርህ ስር እሰግዳለሁ። በኢየሱስ ስም፣ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች