Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


101 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡- ለእረኛ መታዘዝ

101 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡- ለእረኛ መታዘዝ

እግዚአብሔር የሰጠንን የበረከት ሕይወት እንድንኖር የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መንፈሳዊ ምግብ ጥሩ እረኛ ያካፍለናል። ኢየሱስ "ሌባ የሚመጣው ሊሰርቅና ሊያጠፋ እንጂ ሕይወት እንዲኖራቸው አይደለም፤ እኔ የመጣሁት ሕይወት እንዲኖራቸው እንዲሁም የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖራቸው ነው" ብሏል (ዮሐንስ 10:10)።

እረኞቻችንና ሽማግሌዎቻችን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንድንመራና እንድንጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ስለዚህ "እረኞቻችሁን አድምጡ፤ ተገዙላቸውም፤ እነርሱ ስለ ነፍሳችሁ እንደሚጠብቁ እንደሚቆጥሩ ያውቃሉና፤ ይህን በደስታ እንዲያደርጉ እንጂ እያዘኑ እንዳያደርጉ ተገዙላቸው፤ ይህ ለእናንተ አይጠቅምምና" ተብሎ በዕብራውያን 13:17 እንደተጻፈው ልንታዘዝላቸው ይገባል።

እግዚአብሔር በልጆቹ መታዘዝ ደስ ይለዋል። ለእረኞቻችን መታዘዝ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያሳይ ነው። መታዘዝ ማለት ያለምንም ጥያቄ፣ ያለምንም ነቀፋ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከልብ መከተል ማለት ነው። በዚህ መንገድ በኢየሱስ እንሸለማለን፤ ሕይወታችንም በተስፋዎቹ ውስጥ ጸንቶ ይኖራል።

እረኞቻችን በመንፈስ ቅዱስ እንዲመሩና እንዲጠናከሩ ሁልጊዜ መጸለይ አንርሳ። ሕይወታቸውን እናክብር፤ እንዲሁም ለማገልገል ዝግጁ እንሁን።


ዕብራውያን 13:17

ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:7

የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፤ የኑሯቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:15

እንደማያፍርና የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያስረዳ የተመሰከረለት ሠራተኛ፣ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ልታቀርብ ትጋ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:22

ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 27:23

በጎችህ በምን ሁኔታ እንዳሉ ደኅና አድርገህ ዕወቅ፤ መንጋህንም ተንከባከብ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 18:19-24

ምክር እሰጥሃለሁና አሁን እኔን ስሙኝ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሁን። አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝብን የምትወክል መሆን አለብህ፤ ክርክራቸውን ወደ እርሱ ታቀርባለህ። ሙሴ ሚስቱን ሲፓራን ከመለሳት በኋላ ዐማቱ ዮቶር እርሷንና ሁለት ወንድ ልጆቿን ተቀብሏቸው ነበር። ሥርዐቶቹንና ሕጎቹን አስተምራቸው፤ እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን መሥራት እንደሚገባቸው አሳያቸው። ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው። በማንኛውም ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ፤ ቀላሉን ነገር እነርሱ ይወስኑ፤ አስቸጋሪ የሆነውን ጕዳይ ሁሉ ግን ለአንተ እንዲያቀርቡ አድርግ፤ ሥራውን ስለሚያግዙህ ሸክምህ ይቃለላል። አንተ ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም ይህንኑ ቢያዝዝህ፣ ድካምህን መቋቋም ትችላለህ፤ እነዚህም ሰዎች ሁሉ ረክተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።” ሙሴ ዐማቱን ሰማ፤ ያለውንም ሁሉ ፈጸመ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 3:15

እንደ ልቤም የሆኑ፣ በዕውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:17

ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ የሚያስተዳድሩ፣ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚተጉ ሽማግሌዎች ዕጥፍ ክብር ይገባቸዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘኍል 27:18-20

ስለዚህም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት። በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በፊታቸውም ሹመው፤ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ቀረቡ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በመሪዎችና በመላው ማኅበርም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲታዘዝለትም ከሥልጣንህ ከፍለህ ስጠው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:12-13

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በእናንተ መካከል በትጋት የሚሠሩትን፣ በጌታም የበላዮቻችሁና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን፤ ስለ ሥራቸውም በፍቅር እጅግ አክብሯቸው። እርስ በርሳችሁም በሰላም ኑሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 17:12

አምላክህን እግዚአብሔርን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህን ወይም ዳኛ የሚንቅ ይገደል፤ ከእስራኤልም መካከል ክፉውን አስወግድ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢያሱ 1:16-17

እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን። ለሙሴ ሙሉ በሙሉ እንደ ታዘዝን ሁሉ፣ ለአንተም እንታዘዛለን፤ ብቻ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበረ፣ አሁንም ከአንተ ጋራ ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 15:22

ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣ እግዚአብሔር፣ በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 16:7

እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፣ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። እግዚአብሔር የሚያየው፣ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 24:6

ለሰዎቹም፣ “እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና እግዚአብሔር የቀባው ስለ ሆነም እጄን በርሱ ላይ ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:11-12

አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይኸውም የክርስቶስ አካል ይገነባ ዘንድ፣ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት ሲሆን፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዜና መዋዕል 29:20

ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱት” አላቸው። ስለዚህ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 20:20

በማግስቱም ጧት በማለዳ ተነሥተው ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ሄዱ። መንገድ እንደ ጀመሩም ኢዮሣፍጥ ቆሞ፣ “ይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፣ ስሙኝ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፤ ትጸኑማላችሁ። በነቢያቱም እመኑ፤ ይሳካላችሁማል” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 23:1-4

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ አንዳች አይጐድልብኝም። በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤ ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል። በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:72

እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 133:1

ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:14

በአመራር ጕድለት መንግሥት ይወድቃል፤ የመካሮች ብዛት ግን ድልን ርግጠኛ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 12:13

እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣ የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤ አምላክን ፍራ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 3:10-11

ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና። በደለኞች ወዮላቸው! ጥፋት ይመጣባቸዋል! የእጃቸውን ያገኛሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 23:4

የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም አይፈሩም፤ አይደነግጡም፤ ከእነርሱም አንድ እንኳ አይጐድልም” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 23:16

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነዚህ ነቢያት የሚተነብዩላችሁን አትስሙ፤ በባዶ ተስፋ ይሞሏችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ የወጣ ሳይሆን፣ ከገዛ ልባቸው የሆነውን ራእይ ይናገራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:23

በእነርሱ ላይ አንድ እረኛ፣ ባሪያዬን ዳዊትን አቆማለሁ፤ እርሱም ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:31

እናንተ በጎቼ የማሰማሪያዬ በጎች ያልኋችሁ፣ ሕዝብ ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 2:7

“ካህኑ የሁሉ ገዥ፣ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለ ሆነ ከንፈሮቹ ዕውቀትን ሊጠብቁ፣ ሰዎችም ከአንደበቱ ትምህርትን ሊፈልጉ ይገባል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 10:40-41

“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 20:25-28

ኢየሱስ ግን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የአሕዛብ ገዦች በሕዝባቸው ላይ ጌቶች እንደሚሆኑ፣ ባለሥልጣኖቻቸውም በእነርሱ ላይ እንደሚሠለጥኑባቸው ታውቃላችሁ፤ በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም። ከእናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን፤ ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤ የሰው ልጅ እንዲያገለግሉት ሳይሆን፣ ለማገልገልና ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት መጥቷልና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 23:3

ስለዚህ የሚነግሯችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እንደሚናገሩት አያደርጉምና ተግባራቸውን አትከተሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 24:45-47

“በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ባለቤቱ በቤተ ሰዎቹ ላይ የሾመው ታማኝና ብልኅ ባሪያ እንግዲህ ማነው? ጌታው ሲመለስ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ባሪያ እርሱ ምስጉን ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 10:16

“እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተን የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔንም የማይቀበል የላከኝን አይቀበልም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:11

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 10:14-15

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን ዐውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፤ ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው ነው። ሕይወቴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 13:20

እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የላክሁትን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለም የላከኝን ይቀበላል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 6:2-4

ስለዚህ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሌሎችን ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሰብስበው እንዲህ አሉ፤ “እኛ የማእዱን አገልግሎት ለማስተናገድ ስንል የእግዚአብሔርን ቃል አገልግሎት መተው አይገባንም። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ መካከል በመንፈስ ቅዱስና በጥበብ የተሞሉ ለመሆናቸው የተመሰከረላቸውን ሰባት ሰዎች ምረጡ፤ ይህን ኀላፊነት ለእነርሱ እንሰጣለን፤ እኛ ግን በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንተጋለን።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 14:23

ከዚያም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ፣ በጾምና በጸሎት ላመኑበት ጌታ ዐደራ ሰጧቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 20:28

ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:1-2

ማንኛውም ሰው በሥልጣን ላሉት ሹማምት መገዛት ይገባዋል፤ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው። ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቧልና። ሌሊቱ ሊያልፍ፣ ቀኑም ሊጀምር ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን፣ የብርሃንን ጦር ዕቃ እንልበስ። በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን። ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት። ስለዚህ፣ በባለሥልጣን ላይ የሚያምፅ በእግዚአብሔር ሥርዐት ላይ ማመፁ ነው፤ ይህን የሚያደርጉትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:7

ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ከሆነ ግብርን፣ ቀረጥ ከሆነም ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባውም ክብርን ስጡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 4:1

እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 4:2

ባለዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:14

እንደዚሁም ወንጌልን የሚሰብኩ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ከወንጌል እንዲቀበሉ ጌታ አዝዟል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 16:15-16

የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እለምናችኋለሁ፤ እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋራ በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 1:24

ጸንታችሁ የምትቆሙት በእምነት ስለ ሆነ፣ ደስ እንዲላችሁ ከእናንተ ጋራ እንሠራለን እንጂ በእምነታችሁ ላይ ለመሠልጠን አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 10:8

ጌታ በሰጠን ሥልጣን እጅግ ብመካም በዚህ አላፍርም፤ ሥልጣኑን የተቀበልነው እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:6

ማንም ቃሉን የሚማር፣ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ከመምህሩ ጋራ ይካፈል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:21

ለክርስቶስ ካላችሁ አክብሮታዊ ፍርሀት የተነሣ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ተገዙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:29

በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፤ እንደ እርሱ ያሉትንም ሰዎች አክብሯቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:9

ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማንኛውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋራ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:7

ይህንም ስለ እኛ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነው፣ ዐብሮንም በአገልግሎት የተጠመደው ተወዳጁ ኤጳፍራ አስተማራችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:22-24

ባሮች ሆይ፤ ለታይታ ሰውን እንደሚያስደስቱት ሳይሆን፣ በቅን ልብ ጌታን በመፍራት ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ። የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት፤ ከጌታ ዘንድ እንደ ብድራት የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:25

ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ተሰሎንቄ 3:4

እኛ ያዘዝናችሁን አሁን አደረጋችሁ፤ ወደ ፊትም እንደምታደርጉ በጌታ እንታመናለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 3:1-2

“ማንም ኤጲስቆጶስነትን ቢፈልግ፣ መልካም ሥራን ይመኛል” የሚለው ቃል የታመነ ነው። እነርሱም አስቀድመው ይፈተኑ፤ ከዚያም፣ አንዳች ነቀፋ ካልተገኘባቸው በዲቁና ያገልግሉ። እንዲሁ ሴቶችም የተከበሩ፣ ሐሜተኞች ያልሆኑ ነገር ግን ልከኞችና በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል። ዲያቆናት የአንዲት ሚስት ባል መሆን ይገባቸዋል፤ ደግሞም ልጆቻቸውንና ቤተ ሰቦቻቸውን በአግባቡ የሚያስተዳድሩ መሆን አለባቸው። በአግባቡ ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ክብርን፣ በክርስቶስ ኢየሱስም ባላቸው እምነት ብዙ ድፍረትን ያገኛሉ። ወደ አንተ ቶሎ ለመምጣት ተስፋ ባደርግም ይህን ትእዛዝ እጽፍልሃለሁ፤ ይህንም የምጽፍልህ ብዘገይ እንኳ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤት እንዴት መኖር እንዳለባቸው እንድታውቅ ነው፤ ቤቱም የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፣ ይኸውም የእውነት ዐምድና መሠረት ነው። የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱ በሥጋ ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ። እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ በሥርዐት የሚኖር፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማስተማር የሚችል፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 4:12

ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 4:16

ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:19

በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብ ክስ አትቀበል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 6:1-2

የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱም እንዳይሰደቡ፣ በባርነት ቀንበር ሥር ያሉ ሁሉ፣ ጌቶቻቸው ሙሉ ክብር እንደሚገባቸው አድርገው ይቍጠሩ። ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል። የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል። መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ። ለሁሉም ሕይወትን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁም በጳንጥዮስ ጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ዐደራ የምልህ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ይህን ትእዛዝ ያለ ዕድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ እንድትጠብቅ ነው፤ ያም መገለጥ፣ የተባረከውና ብቻውን ገዥ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ የሚያሳየው ነው፤ እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን። አሜን። በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። መልካም እንዲሠሩ፣ ቸሮችና ለማካፈል ፈቃደኞች የሆኑ እንዲሆኑ እዘዛቸው። በዚህ ዐይነት እውነተኛ የሆነውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ፣ ለሚመጣው ዘመን ጽኑ መሠረት የሚሆን ሀብት ለራሳቸው ያከማቻሉ። የሚያምኑ ጌቶች ያሏቸውም፣ ወንድሞች ስለ ሆኑ የሚገባቸውን ክብር አይንፈጓቸው፤ ይልቁንም በአገልግሎታቸው የሚጠቀሙ አማኞችና ወዳጆቻቸው ስለ ሆኑ የበለጠ ሊያገለግሏቸው ይገባል። እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ ምከርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 1:13-14

ከእኔ የሰማኸውን የጤናማ ትምህርት ምሳሌ አድርገህ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር ያዝ። የተሰጠህን መልካሙን ዐደራ በእኛ ውስጥ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:24-25

የጌታም ባሪያ ሊጣላ አይገባውም፤ ይልቁን ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማር ብቃት ያለው፣ ትዕግሥተኛም መሆን ይገባዋል፤ እውነትን ወደ ማወቅ ይደርሱ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ንስሓን እንደሚሰጣቸው ተስፋ በማድረግ የሚቃወሙትን በየዋህነት የሚያቃና መሆን ይኖርበታል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 4:2

ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ዝግጁ ሁን፤ በታላቅ ትዕግሥትና በማስተማር አቅና፤ ገሥጽ፤ አበረታታም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 1:5

አንተን በቀርጤስ የተውሁህ ገና ያልተስተካከለውን ነገር እንድታስተካክልና ባዘዝሁህ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 1:9

ሌሎችን ትክክል በሆነው ትምህርት እንዲያበረታታና ይህንኑ ትምህርት የሚቃወሙትን ይወቅሥ ዘንድ እንደ ተማረው በታመነ ቃል የሚጸና መሆን አለበት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:7-8

በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣ የማይነቀፍ ጤናማ አነጋገርንም አሳይ፤ ይኸውም ተቃዋሚ ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር በማጣት እንዲያፍር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:15

እንግዲህ ልታስተምር የሚገባህ እነዚህን ነው፤ በሙሉ ሥልጣን ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልሞና 1:21

ታዛዥ መሆንህን በመተማመን፣ ከምጠይቀውም በላይ እንደምታደርግ በማወቅ እጽፍልሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:24

ለመሪዎቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣሊያ የሆኑትም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 3:1

ወንድሞቼ ሆይ፤ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:13-14

ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለሥልጣን ሁሉ ተገዙ፤ የበላይ ባለሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣትና በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:1-3

እንግዲህ ከእነርሱ ጋራ እኔም ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምስክር የሆንሁ፣ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፣ በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል። ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ለርሱ ይሁን። አሜን። እንደ ታማኝ ወንድም በምቈጥረው በሲላስ አማካይነት ይህን ዐጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍሁላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልመሰክርላችሁ ብዬ ነው። በዚህ ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ። ከእናንተ ጋራ የተመረጠችው፣ በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ እንዲሁም ልጄ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን፤ እንዲሁም በዐደራ ለተሰጣችሁ መንጋ መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በላያቸው በመሠልጠን አይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:5

ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:20-21

ከሁሉ አስቀድሞ ይህን ልታውቁ ይገባችኋል፤ በመጽሐፍ ያለው የትንቢት ቃል ሁሉ ማንም ሰው በገዛ ራሱ መንገድ የሚተረጕመው አይደለም፤ ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:1

ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:6

እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም፤ በዚህም የእውነትን መንፈስና የሐሰትን መንፈስ እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ይሁዳ 1:8

በዚህ ሁኔታ እነዚህ ሕልም ዐላሚዎች የገዛ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ሥልጣንን አይቀበሉም፤ በሰማይ ክብር ያላቸውንም ፍጥረታት ይሳደባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 1:20

በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 2:1

“በኤፌሶን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘው፣ በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 2:7

መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን፣ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ አደርገዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዜና መዋዕል 16:22

እንዲህ ሲል፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 19:21

ስለዚህም ኤልሳዕ ትቶት ተመለሰ። ሁለቱን በሬዎቹን ወስዶ ዐረደ፤ የዕርሻ ዕቃውን አንድዶ ሥጋቸውን በመቀቀል ለሕዝቡ ሰጠ፤ እነርሱም በሉ። ከዚያም ኤልያስን ለመከተል ሄደ፤ ረዳቱም ሆነ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 2:15

ከኢያሪኮም መጥተው ይህን ያዩ የነበሩት የነቢያት ወገኖች፣ “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፏል” አሉ፤ ሊያገኙትም ሄደው በፊቱ ወደ መሬት ዝቅ ብለው እጅ ነሡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:70-72

ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች ጕረኖ ውስጥ ወሰደው፤ ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣ የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው። እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:33

ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:1

ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:20

ምክርን የሚሰማ ይለመልማል፤ በእግዚአብሔርም የሚታመን ብፁዕ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:20

ምክርን ስማ፤ ተግሣጽን ተቀበል፤ በመጨረሻም ጠቢብ ትሆናለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:11

መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፤ ጠቦቶቹን በክንዱ ይሰበስባል፤ በዕቅፉም ይይዛቸዋል፤ የሚያጠቡትንም በጥንቃቄ ይመራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:4

እነሆ፤ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፣ መሪ፣ የጦር አዝማችም አድርጌዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 6:8

ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 11:17

“መንጋውን ለሚተው፣ ለማይረባ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዐይኑን ትውጋው! ክንዱ ፈጽማ ትስለል! ቀኝ ዐይኑም ጨርሳ ትታወር!”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 12:28

እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ ነቢያትን፣ ሦስተኛ መምህራንን፣ ቀጥሎም ታምራት አድራጊዎችን፣ የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቧል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 20:35

በጕልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ምስጉን ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 6:10

እግዚአብሔር ዐመፀኛ አይደለም፤ እርሱ ሥራችሁን እንዲሁም በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:7-8

ማገልገል ቢሆን ያገልግል፤ ማስተማርም ከሆነ ያስተምር፤ መምከር ከሆነ ይምከር፤ ለሌላቸው መለገስ ከሆነም አብዝቶ ይለግስ፤ ማስተዳደር ከሆነም በትጋት ያስተዳድር፤ ምሕረት ማድረግ ከሆነም በደስታ ይማር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:3

በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:1-2

ስለዚህ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ይህ አገልግሎት ስላለን ተስፋ አንቈርጥም። የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ፣ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁልጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና። እንግዲህ ሞት በእኛ ይሠራል፤ ሕይወት ግን በእናንተ። “አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እኛም በዚያው የእምነት መንፈስ እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እኛንም ደግሞ ከኢየሱስ ጋራ አስነሥቶ ከእናንተ ጋራ በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን። ለብዙ ሰዎች እየደረሰ ያለው ጸጋ፣ ለእግዚአብሔር ክብር በምስጋና ላይ ምስጋናን እንዲጨምር ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሆኗል። ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየጠፋ ቢሄድም እንኳ፣ ውስጣዊው ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፤ ምክንያቱም ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል። ስለዚህ ዐይናችን የሚያተኵረው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን በማይታየው ላይ ነው፤ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው። ነገር ግን ስውርና አሳፋሪ ነገሮችን ትተናል፤ በማታለል አንመላለስም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ከሐሰት ጋራ አንቀላቅልም፤ ይልቁንም እውነትን በግልጽ እየተናገርን በሰው ሁሉ ኅሊና ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:14

“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ የዘላለም አምላክ፥ ልዑል ጌታ! አንተ ጻድቅና ቅዱስ ስለሆንክ፥ ከፍ ያለውን ምስጋናና አምልኮ ይገባሃልና አመሰግንሃለሁ። አባታችን ቅዱስ፥ ፈቃድህ እረኞቼን እንዳከብርና እንድጸልይላቸው ነው፥ እነርሱ መንፈሳዊ ሕይወቴን እንዲመሩ ያስቀመጥካቸው ሰዎች ናቸውና። በየዕለቱ በታዛዥነቴ እንድታከብርህ አስተምረኝ፥ እነርሱን በቃልህ እንዲያስተምሩኝና እንዲያዳብሩኝ እንዳስቀመጥካቸው እንድገነዘብ አድርገኝ። ምክራቸውንና ተግማራቸውን እንድቀበል የሚያስችለኝ ትሑት ልብ ስጠኝ። ቃልህ «እረኞቻችሁን ታዘዙ፥ ተገዙላቸውም፤ እነርሱ ስለ ነፍሳችሁ እንደሚጠይቁ ሆነው ይተጉላችኋልና፤ ስለዚህም በደስታ ያድርጉት እንጂ በኃዘን አይደለም፥ ይህ ምንም አይጠቅማችሁምና» ይላል። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ እውነተኛ ታዛዥነትን እንድለማመድ እርዳኝ፥ የመንግሥትህን ኃላፊነቶች እንዲያምኑኝ፤ እንደ ትጉ ሠራተኛ በትጋት እንድሠራ፥ ለሰዎች ሳይሆን ለአንተ እንደሆነ አድርጌ በልቤ እንዳደርገው፥ ያለ ማጉረምረምና ያለ አቤቱታ፥ ምክንያቱም ይህ ምንም አይጠቅምምና። እነርሱም እንደማንኛው ሰው እንደሆኑ፥ የሚያዝኑ፥ በችግርና በፈተና በሕመምም የሚያልፉ፥ በጸጥታ የሚያለቅሱ፥ በትከሻቸው ላይ ስለ ሕዝብህ ከባድ ሸክምና ኃላፊነት ያለባቸው እንደሆኑ፥ በዚህም ምክንያት በየዕለቱ ጸጋህን እንደሚያስፈልጋቸው እንድገነዘብና በጥበብ እንድይናቸው ጥበብን ስጠኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን!
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች