እግዚአብሔር ሠራዊቱን መላእክት ለእኔ እንዲዋደሉልኝና እንዲጠብቁኝ አዘጋጅቶልኛል፤ እኔ ግን እነርሱን መጠቀም አለብኝ። ስለዚህ ሩቅም ይሁን ቅርብ፣ ቤቴን ለቅቄ ስወጣ ሁልጊዜ መጸለይ አለብኝ። ለስራም ይሁን ለእረፍት፣ እቅዴን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥቼ መውጣቴንና መግባቴን እንዲጠብቅልኝ፣ የምሰራው ሁሉ እርሱን ደስ የሚያሰኘው ብቻ ሳይሆን ለእኔም አስደሳች እንዲሆን እንዲባርከው መጠየቅ አለብኝ። ልቤን በእግዚአብሔር ላይ አድርጌ የጠላትን ሽንገላ አቅልዬ ማየት የለብኝም። እንደሚያገሳ አንበሳ ማንን እንደሚውጥ እየፈለገ ስለሚዞር ንቁ ሆኜ ጸሎቴን መዘንጋት የለብኝም። እቅዴን ለእግዚአብሔር ፈቃድ አደራ ብሰጥ በምጀምረው ነገር ሁሉ እባረካለሁ። «እግዚአብሔር መውጣትህንና መግባትህን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ይጠብቃል» (መዝሙር 121:8)።
“ ‘ “እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፤ ይራራልህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ይመልስልህ፤ ሰላሙንም ይስጥህ።” ’
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”
ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል። በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።
እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ነፍስህንም ይንከባከባታል። እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።
አምላክህ እግዚአብሔር ትእዛዞቹን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ፣ ትሑት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጕዞህ ሁሉ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ ዐጥንትህን ያበረታል፤ በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ።
ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጣችሁ፣ የሰላም ሐሳብ እንጂ ለክፉ አይደለም።
ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል። ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።
በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።