Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጠላት ከም​ት​ሆን ወዳጅ ሁን፤ የክፉ ስም ፍጻ​ሜው ስድ​ብና ውር​ደት ነውና፤ ምላሱ ሁለት የሆነ ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም እን​ዲህ ነው።

2 ከል​ቡ​ናህ ባነ​ቃ​ኸ​ውም ምክር ራስ​ህን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርግ፤ አን​በሳ ላምን እን​ደ​ሚ​ነ​ጣ​ጠቅ ሰው​ነ​ት​ህን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት።

3 ቅጠ​ል​ህን ይበ​ላ​ብ​ሃል፥ ፍሬ​ህ​ንም ታጣ​ለህ፤ እንደ ደረቅ እን​ጨ​ትም ይጥ​ል​ሃል።

4 ክፉ ሰው​ነት ገን​ዘብ ያደ​ረ​ጋ​ትን ሰው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ጠላ​ቱ​ንም በእ​ርሱ የጨ​ከነ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለች።


እው​ነ​ተ​ኛና እው​ነ​ተኛ ያል​ሆነ ጓደ​ኝ​ነት

5 ልዝብ አን​ደ​በት ወን​ድ​ማ​ማ​ች​ነ​ትን ያበ​ዛል፤ ልዝብ አፍም ወዳ​ጅን ያበ​ዛል።

6 ብዙ ሰዎች ወዳ​ጆች ይሁ​ኑህ፤ ነገር ግን ከብ​ዙ​ዎቹ አንዱ ምክ​ር​ህን የም​ት​ገ​ል​ጥ​ለት ይሁን።

7 ወዳጅ ብታ​በጅ በች​ግ​ርህ ወራት ወዳጅ አብጅ። ፈጥ​ነ​ህም እም​ነት አት​ጣ​ል​በት፤

8 ለጥ​ቂት ቀን የሚ​ሆን ወረ​ተኛ ወዳጅ አለና፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ከአ​ንተ ጋራ አይ​ታ​ገ​ሥም።

9 ጠላት የሚ​ሆ​ን​ህና፥ የሚ​ሰ​ድ​ብህ፥ ሰው​ረህ የሠ​ራ​ኸ​ውን ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም የሚ​ገ​ል​ጥ​ብህ ወዳጅ አለ።

10 ስለ ማዕ​ድ​ህም የሚ​ወ​ድህ ወዳጅ አለ፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋራ አይ​ኖ​ርም፥ በተ​ቸ​ገ​ር​ህም ጊዜ ይለ​ይ​ሃል።

11 ባለ​ጸጋ በሆ​ንህ ጊዜ እን​ዳ​ንተ ይሆ​ናል፤ ቤተ ሰብ​ህ​ንም ይገ​ዛል።

12 ብት​ቸ​ገር ግን እርሱ ባላ​ጋ​ራህ ይሆ​ናል፤ እን​ዳ​ታ​የ​ውም ይሰ​ወ​ር​ሃል።

13 ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ራቅ፥ ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንም ተጠ​ባ​በ​ቃ​ቸው።

14 የታ​መነ ወዳጅ እንደ ጸና አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ነው፤ እር​ሱን ያገኘ ሰው ድልብ አገኘ።

15 ለታ​መነ ወዳጅ ለውጥ የለ​ውም፤ ለደ​ግ​ነ​ቱም ሚዛን የለ​ውም።

16 የታ​መነ ወዳጅ የሕ​ይ​ወት መድ​ኀ​ኒት ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈሩ ያገ​ኙ​ታል።

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ወዳ​ጅ​ነ​ቱን ያጸ​ናል፤ ባል​ን​ጀ​ራው እንደ እርሱ ይሆ​ነ​ዋ​ልና።


የጥ​በብ በረ​ከት

18 ልጄ ሆይ፥ በሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጥበ​ብን ምረ​ጣት፤ እስ​ክ​ታ​ረ​ጅም ድረስ ታገ​ኛ​ታ​ለህ።

19 እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ስና እን​ደ​ሚ​ዘራ ሰው ወደ እር​ስዋ ሂድ፤ የተ​ባ​ረከ ፍሬ​ዋ​ንም ጠብቅ፤ ስለ እር​ስዋ በመ​ሥ​ራት ጥቂት ትደ​ክ​ማ​ለህ፤ ነገር ግን ፈጥ​ነህ ፍሬ​ዋን ትበ​ላ​ለህ።

20 በሰ​ነ​ፎች ዘንድ ፈጽማ ጐፃ​ጕፅ ናት፤ አእ​ምሮ በሌ​ለው ሰውም አታ​ድ​ርም።

21 የፈ​ተና ድን​ጋይ አን​ሥ​ተው በተ​ሸ​ከ​ሙት ጊዜ እን​ዲ​ከ​ብድ፥ እን​ደ​ዚሁ ትከ​ብ​ደ​ዋ​ለች፤ ፈጥ​ኖም ይጥ​ላ​ታል።

22 ጥበ​ብስ እንደ ስሟ ናት፤ ብዙ ሰዎ​ችም የሚ​ያ​ው​ቋት አይ​ደ​ሉም።

23 ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ በም​ክ​ሬም ጽና፤ ምክ​ሬ​ንም አታ​ቃ​ልል።

24 እግ​ሮ​ች​ህን ወደ ቀም​በ​ርዋ አግባ፤ ዛን​ጅ​ር​ዋ​ንም ባን​ገ​ትህ እሰር።

25 ጫን​ቃ​ህን ዝቅ አድ​ር​ገህ ተሸ​ከ​ማት፤ በእ​ግር ብረ​ት​ዋም አት​በ​ሳጭ።

26 በፍ​ጹም ነፍ​ስህ ወደ እርሷ ተሰ​ማራ፥ በፍ​ጹም ኀይ​ል​ህም መን​ገ​ድ​ዋን ጠብቅ።

27 ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ተል፥ ፈል​ጋት፤ ታገ​ኛ​ታ​ለ​ህም። ያዛት፥ አት​ተ​ዋ​ትም።

28 በፍ​ጻ​ሜ​ህም ዕረ​ፍ​ትን ታገ​ኛ​ለህ፤ ደስ​ታም ይሆ​ን​ሃል።

29 እግር ብረ​ት​ዋም እንደ ጽኑ ጋሻ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ዛን​ጅ​ር​ዋም የክ​ብር ልብስ ወደ መሆን ይመ​ለ​ስ​ል​ሃል።

30 የዘ​ለ​ዓ​ለም ወርቅ በእ​ርሷ ዘንድ አለና፤ ማሰ​ሪ​ያ​ዋም የሰ​ማ​ያዊ ሐር ጌጥ ይሆ​ን​ሃል።

31 እንደ ክብር ልብስ ትለ​ብ​ሳ​ታ​ለህ፥ የደ​ስታ ዘው​ድ​ንም ታቀ​ዳ​ጅ​ሃ​ለች።

32 ልጄ ሆይ፥ ብልህ ትሆን ዘንድ ብት​ወ​ድድ፥ ትማ​ርም ዘንድ በል​ቡ​ናህ ብት​ጨ​ክን፥

33 ትሰማ ዘንድ ብት​ወ​ድም ታገሥ፤ ጆሮ​ህ​ንም ብታ​ዘ​ነ​ብል ብልህ ትሆ​ና​ለህ።

34 በብዙ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዘንድ ቁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐዋቂ ሰው ብታይ ተከ​ተ​ለው።

35 የመ​ጽ​ሐ​ፉን ነገር ሁሉ ፈጥ​ነህ ስማ፤ የጥ​በ​ብም ምሳሌ አይ​ዘ​ን​ጋህ።

36 ብልህ ሰው ብታይ ፈጥ​ነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ እግ​ር​ህም በደ​ጃፉ መድ​ረክ ይመ​ላ​ለስ።

37 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ዐስብ፤ መጻ​ሕ​ፍ​ቱ​ንም ሁል​ጊዜ አን​ብብ፥ እር​ሱም ልቡ​ና​ህን ያጸ​ና​ዋል፤ ጥበ​ብ​ንም ትወ​ዳት ዘንድ ይሰ​ጥ​ሃል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች