Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ይፈ​ት​ኑት ዘንድ ነው እንጂ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰውን መከራ አያ​ገ​ኘ​ውም፤ ከመ​ከ​ራ​ዪ​ቱም ይድ​ናል።

2 ብልህ ሰው መጽ​ሐፍ መስ​ማ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ርና በመ​ጽ​ሐፉ የማ​ያ​ምን ሰው ግን በጥ​ቅል ነፋስ መካ​ከል እን​ደ​ም​ት​ን​ጓ​ለል መር​ከብ ይሆ​ናል።

3 ብልህ ሰው አምኖ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይገ​ዛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የታ​መነ ወዳጁ ይሆ​ናል፤ ደስም ያሰ​ኘ​ዋል።

4 የም​ት​ና​ገ​ረ​ውን ነገ​ር​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተህ አድ​ምጥ፤ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ምክር አጽ​ን​ተህ ተና​ገር።

5 የሰ​ነፍ ሰው ልቡና እንደ ሰረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵር ነው፤ የፈሪ ሰው ምክ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሽ​ከ​ረ​ከር እን​ዝ​ርት ነው።

6 ጮሌ ፈረስ እንደ በጎ ወዳጅ ነው። በሚ​ጋ​ል​በ​ውም ሁሉ በታች ያሽ​ካ​ካል።

7 የዓ​መቱ ቀን ሁሉ በፀ​ሐይ ብር​ሃን ጸንቶ ሲኖር፥ አን​ዲቱ ቀን ካን​ዲቱ ቀን በምን ትበ​ል​ጣ​ለች?

8 ቀኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይለ​ያል፤ የበ​ዓ​ላ​ቱም ጊዜ በቍ​ጥሩ ይታ​ወ​ቃል።

9 ከቀ​ኑም የቀ​ደ​ሰ​ውና ያከ​በ​ረው አለ። ከእ​ነ​ር​ሱም በየ​ጊ​ዜ​ያ​ቸ​ውና በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ክረ​ም​ት​ንና መጸ​ውን፥ በጋ​ንም ለየ።

10 እኛ ሁላ​ችን የአ​ዳም ልጆች ከመ​ሬት ተገ​ኘን፤ አዳ​ምም ከመ​ሬት ተፈ​ጠረ።

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጥ​በቡ ብዛት ለያ​ቸው፤ በየ​መ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።

12 ከእ​ነ​ር​ሱም የባ​ረ​ካ​ቸ​ውና ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ጋ​ቸው አሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የቀ​ደ​ሳ​ቸ​ውና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው አሉ። ከእ​ነ​ር​ሱም የረ​ገ​ማ​ቸ​ውና ያጐ​ሳ​ቈ​ላ​ቸው አሉ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም የወ​ነ​ጀ​ላ​ቸው አሉ።

13 እኛ ሁላ​ችን በእ​ርሱ ዘንድ በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ ጭቃ፥ ነን፤ ፍጥ​ረቱ ሁሉ በመ​ን​ገ​ዶቹ ይሄ​ዳል፤ ሰውም እን​ዲሁ በፈ​ጣ​ሪው እጅ ነው፤ ለሁ​ሉም እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋል።

14 የክ​ፋት ተቃ​ራ​ኒዋ በጎ​ነት ናት፤ የሞ​ትም ተቃ​ራ​ኒዋ ሕይ​ወት ናት፤ እን​ደ​ዚሁ የጻ​ድቅ ተቃ​ራ​ኒው ኃጥእ ነው።

15 ከዚህ ሁሉ ጋር የል​ዑ​ልን ፍጥ​ረ​ቶች ተመ​ል​ከት፤ አንዱ የሌ​ላው ተቃ​ራኒ ሆኖ ሁለት ሁለት ናቸው።

16 እኔ ግን ከሁሉ በኋላ ተነ​ሥቼ ይኽን ነገር አሰ​ብ​ሁት፥ ከጥ​ን​ቱም ጀምሬ መረ​መ​ር​ሁት።

17 አቤቱ በስ​ምህ የተ​ጠሩ ወገ​ኖ​ች​ህን ይቅር በል፤ የበ​ኵር ልጄ ያል​ሃ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቅር በል።

18 ቅድ​ስት ከተ​ማ​ህን፥ ማረ​ፊያ ቦታ​ህን ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ይቅር በል።

19 ጽዮ​ን​ንም የቃ​ል​ህን በረ​ከት ሙላት፤ ክብ​ር​ህ​ንም በወ​ገ​ኖ​ችህ ላይ ሙላ።

20 አስ​ቀ​ድሞ ለፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ሕግ​ህን ስጣ​ቸው፤ ለስ​ም​ህም ነቢ​ያ​ትን አስ​ነሣ።

21 ነቢ​ያ​ት​ህን ያም​ኗ​ቸው ዘንድ ተስፋ ላደ​ረ​ጉህ ዋጋ​ቸ​ውን ስጣ​ቸው። አቤቱ የባ​ሮ​ችህ የነ​ቢ​ያ​ትን ጸሎ​ታ​ቸ​ውን ስማ፤

22 የአ​ሮ​ን​ንም በረ​ከት በሕ​ዝ​ብህ ላይ አሳ​ድር፤ በም​ድር የሚ​ኖሩ ሰዎች ሁሉ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ብቻ እንደ ሆንህ ይወቁ።

23 እህል ሁሉ ይበ​ላል፤ ወደ ሆድም ይወ​ር​ዳል፤ ነገር ግን ከእ​ህል የሚ​ጣ​ፍጥ እህል አለ።

24 የእ​ህ​ልን ጣዕም ሁሉ ጕሮሮ ይለ​የ​ዋል፥ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ የጠ​ቢብ ሰው ልብ የሐ​ሰት ነገ​ርን ይለ​ያል።

25 ክፉ ልቡና ኀዘ​ንን ያመ​ጣል፤ ብዙ መከራ የተ​ቀ​በለ ሰውም ትዕ​ግ​ሥ​ትን ይለ​ም​ደ​ዋል።

26 ወንድ ሁሉ ሚስት ያገ​ባል፤ ነገር ግን ከሴት የም​ት​ሻል ሴት አለች።

27 የሴት ውበቷ ፊትን ያበ​ራ​ዋል፤ ከሰው ፈቃድ ሁሉ እርሷ ትበ​ል​ጣ​ለች።

28 የዋህ ብት​ሆን፥ ቃሏም ያማረ ቢሆን፤ ባሏ እንደ ሌሎች ሰዎች አይ​ደ​ለም።

29 ረዳቱ፥ መደ​ገ​ፊያ ምሰ​ሶ​ውም ናትና፥ ልባም ሴትን ያገባ ሰው ደስ​ታ​ውን አገኘ።

30 ቅጥር የሌ​ለው ቤት ገን​ዘቡ እን​ዲ​ሠ​ረቅ፥ እን​ደ​ዚ​ሁም ሚስት የሌ​ለ​ችው ሰው ተቸ​ግሮ ይኖ​ራል።

31 ከከ​ተማ ወደ ከተማ የሚ​ዞር ሌባን የሚ​ዋ​ሰው ማን ነው? ልጆች የሌ​ሉት፥ ንብ​ረ​ትም የሌ​ለ​ውና በመ​ሸ​በት የሚ​ያ​ድር ሰውም እን​ዲሁ ነው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች