Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በጎ ልቡ​ና​ንና የሚ​ጣ​ፍጥ እህ​ልን አይ​ን​ቁ​ትም፤ ለባ​ለ​ጸ​ግ​ነት መት​ጋት ፈጽሞ ሰው​ነ​ትን ያከ​ሳል፥ ገን​ዘ​ብ​ንም ማሰብ እን​ቅ​ል​ፍን ያሳ​ጣል።

2 የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ሩ​ትን ማሰብ በእ​ን​ጉ​ልቻ እን​ቅ​ል​ፍን ያስ​ረ​ሳል፤ ከባድ ሕማ​ምም ያተ​ጋል፥ እን​ቅ​ል​ፍ​ንም ያሳ​ጣል።

3 ባለ​ጸጋ ገን​ዘብ ያደ​ልብ ዘንድ ይዞ​ራል፤ ባረ​ፈም ጊዜ በጥ​ጋብ ደስ ይለ​ዋል።

4 ድሃ ገን​ዘብ በማ​ጣት ይደ​ክ​ማል፤ ባረ​ፈም ጊዜ ወደ ልመና ይመ​ለ​ሳል።

5 ገን​ዘ​ብን የሚ​ወድ ሰው አይ​ጸ​ድ​ቅም፤ ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ወ​ዳት ሰው ይከ​ተ​ላ​ታል።

6 ስለ ገን​ዘብ የወ​ደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ሞታ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ቸው አዩ​ኣት።

7 ገን​ዘብ ለሚ​ፈ​ል​ጓት የእ​ን​ቅ​ፋት ዕን​ጨት ናት፤ ሰነፍ ሰው ሁሉ በእ​ር​ስዋ ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል።

8 ከኀ​ጢ​አት ንጹሕ የሆነ፥ ልቡ​ና​ው​ንም ከገ​ን​ዘብ በኋላ ያላ​ስ​ከ​ተለ ባለ​ጸጋ ብፁዕ ነው።

9 ለወ​ገ​ኖቹ መል​ካም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን​ነው? እንጃ! እር​ሱን እና​ደ​ን​ቀ​ዋ​ለን።

10 በእ​ርሱ የተ​ፈ​ተነ፥ ያል​ሳ​ተም እር​ሱም መመ​ኪያ የሆ​ነው ማን ነው? ኀጢ​አት መሥ​ራት ሲቻ​ለው ኀጢ​አት የማ​ይ​ሠራ ማን ነው? እንጃ። ክፉ መሥ​ራት ሲቻ​ለ​ውስ ክፉ የማ​ያ​ደ​ርግ ሰው ማን ነው?

11 በረ​ከቱ ትጸ​ና​ለች፤ ምጽ​ዋ​ቱም በአ​ሕ​ዛብ ሀገር ትሰ​ማ​ለች።


የማ​ዕድ ሥር​ዐት

12 በታ​ላቅ ማዕ​ድም ብት​ቀ​መጥ ለመ​ብ​ላት ጉሮ​ሮ​ህን አት​ክ​ፈት፤ ምግ​ቡም ምን ያህል ነው ብለህ አታ​ጋን፤

13 የሰው ዐይን ክፉ እንደ ሆነ አስብ፤ ከሰው ዐይን የሚ​ከፋ ምን አለ? ስለ​ዚ​ህም ነገር ዐይን ታለ​ቅ​ሳ​ለች።

14 ላየ​ኸው ሁሉ አት​ሳሳ፤ እጅ​ህን አት​ን​ከር፤ ወጭ​ቱን ወደ አንተ አት​ጎ​ትት፥ ድስ​ቱ​ንም አት​ጥ​ረግ።

15 ባል​ን​ጀ​ራህ የጋ​በ​ዘ​ህን ዕወቅ፤ ያቀ​ረ​በ​ል​ህ​ንም ሁሉ ተረዳ።

16 ያቀ​ረ​ቡ​ል​ህን እንደ ብልህ ሰው ሁነህ ብላ፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እን​ዳ​ታ​ስ​ጸ​ይፍ ስታ​ላ​ምጥ ምላ​ስ​ህን አታ​ጩህ።

17 እንደ ብልህ ሰው ሁሉ አስ​ቀ​ድ​መህ ተው፤ አት​ሳሳ፤ እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ግብ ሰውም አት​ሁን።

18 በብ​ዙ​ዎች መካ​ከ​ልም ብት​ቀ​መጥ እጅ​ህን አስ​ቀ​ድ​መህ አት​ስ​ደድ።

19 በመ​ኝ​ታህ ሆድ​ህን እን​ዳ​ይ​ከ​ብ​ድህ፥ ጥቂት እን​ደ​ሚ​በ​ቃው እንደ ዐዋቂ ሰው መጥ​ነህ ብላ።

20 መጥኖ የሚ​መ​ገብ ሰው እን​ቅ​ልፉ ጤና ነው፤ ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም በጧት በነቃ ጊዜ ሆዱን አይ​ከ​ብ​ደ​ውም፤ ለማ​ይ​ጠ​ግብ ለስሱ ሰው በሽ​ታው ቍን​ጣን፥ ጓታና ብስና ነው።

21 ትበላ ዘንድ ግድ ቢሉህ ቀድ​መ​ሃ​ቸው ተነሥ፤ ከመ​ብ​ላ​ትም ዕረፍ።

22 ልጄ ሆይ አድ​ም​ጠኝ፤ ምክ​ሬ​ንም አት​ናቅ፤ ኋላ ነገ​ሬን ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ምንም እን​ዳ​ታጣ በም​ት​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ደካማ አት​ሁን።

23 ለጋ​ስን ሰው በሥ​ራው ማማር ይመ​ር​ቁ​ታል፤ የደ​ግ​ነቱ ምስ​ክ​ር​ነ​ትም የታ​መነ ነው፤ ንፉግ ሰው​ንም በክፉ ሥራው ይረ​ግ​ሙ​ታል። የክ​ፋቱ ምስ​ክ​ር​ነ​ትም የተ​ረዳ ነው።

24 መጠጥ ብዙ ሰዎ​ችን አስ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ልና፥ ወይን በጠ​ጣህ ጊዜ አት​ታ​በይ።

25 ጽኑ ብረ​ትን በወ​ናፍ ይፈ​ት​ኑ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም ሁሉ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ልቡና ወይን ይፈ​ት​ነ​ዋል።

26 የሰው ሕይ​ወቱ ወይን መጠ​ጣት ነው፤ መጥኖ ለሚ​ጠ​ጣ​ውም ሰው ደስታ ነው፤ እርሱ ለሰው ደስታ ሊሆን ተፈ​ጥ​ሯ​ልና ወይን ለማ​ይ​ጠጣ ሰው ሕይ​ወቱ ምን​ድን ነው?

27 ለልብ ደስታ ነው፤ ለሰ​ው​ነ​ትም ሐሤት ነው፤ ወይ​ንን መጥኖ በጊ​ዜው መጠ​ጣት መል​ካም ነው።

28 ወይን የል​ቡና ኀዘ​ንን ያስ​ረ​ሳል፤ ለሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና ለሚ​ያ​ዝን ሰውም ወይ​ንን አጠ​ጣው።

29 ሰነፍ ሰው ወይን በጠጣ ጊዜ ክር​ክ​ርን ያበ​ዛል፥ ይስ​ታል፥ ይበ​ድ​ላ​ልም፤ የመ​ጠጥ ብዛት ኀይ​ልን አያ​ስ​ገ​ኝም፤ ቍስ​ል​ንም አያ​ሳ​ጣም።

30 ወይን ጠጥቶ ሳለ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን አት​ቈ​ጣው፤ ልቡ ደስ ብሎት ሳለም አታ​ሳ​ዝ​ነው፤ የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ው​ንም አት​ን​ገ​ረው፤ እርሱ ሰክሮ ሳለ ጉዳ​ይ​ህን አት​ለ​ም​ነው፤ አት​ዘ​ብ​ዝ​በ​ውም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች