ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ስለ እስራኤል ድኅነት የቀረበ ጸሎት 1 የኀይል ሁሉ ፈጣሪ አቤቱ፥ ይቅር በለን፤ ተመለስልንም። 2 በአሕዛብ ሁሉ ላይ አንተን መፍራትን አሳድር። 3 ልዩ በሆኑ ወገኖችም ላይ እጅህን አንሣ፤ ኀይልህንም ይዩ። 4 እነርሱ እያዩ በእኛ ዘንድ እንደ ተመሰገንህ፥ እንደዚሁ እኛ እያየን በእነርሱ ዘንድ ተመስገን። 5 አቤቱ ያለአንተ ሌላ ፈጣሪ የለምና፥ እኛ እንዳወቅንህ እነርሱም ይወቁህ። 6 ተአምራትህን አሳይ፤ ጌትነትህንም ግለጥ። 7 በእጅህ ኀይል በቀኝህም ክብር፥ 8 ጥፋትን አምጣባቸው፤ መቅሠፍትንም ላክባቸው። 9 ዐመፀኛውንም አጥፋው፤ ጠላትንም ቀጥቅጠው። 10 ድንቅ ሥራህን ይነግሩ ዘንድ የባሮችህን መሐላ አስብ፤ የሚጠፉባትንም ቀን ፈጥነህ አድርጋት። 11 በቍጣና በእሳት ቅሠፋቸው፤ ከእነርሱም ያመለጡትን አጥፋቸው፤ በወገኖችህም ላይ ክፉ ያደረጉ ሰዎችን ሞት ያግኛቸው። 12 ያለ እኛ ሌላ ሰው የለም የሚሉ የጠላቶችን አለቆች ራስ ስበር። 13 የያዕቆብን ልጆች ሁሉ ሰብስባቸው። |