Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ድሃ በጥ​በቡ ይከ​ብ​ራል፤ በመ​ኳ​ን​ን​ትም መካ​ከል ይቀ​መ​ጣል።

2 ስለ መልከ መል​ካ​ም​ነቱ ለሰው አታ​ድላ፤ ስለ መልከ ጥፉ​ነ​ቱም ሰውን አት​ና​ቀው።

3 ንብ ከወ​ፎች ሁሉ ታን​ሳ​ለች፤ ማርዋ ግን ከሁሉ ይጣ​ፍ​ጣል።

4 በል​ብ​ስህ ጌጥ አት​ታ​በይ። በከ​በ​ር​ህ​በ​ትም ወራት ራስ​ህን አታ​ኵራ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ልዩ፥ ጥበ​ቡም ከሰው የተ​ሰ​ወረ ነውና።

5 በም​ድር የወ​ደቁ መኳ​ን​ንት ብዙ ናቸው፤ ዘውድ የተ​ቀ​ዳጀ ባሕ​ታ​ዊም አለ።

6 ፈጽ​መው የተ​ዋ​ረዱ መኳ​ን​ንት ብዙ ናቸው፤ በሌ​ሎ​ችም እጅ የወ​ደቁ መኳ​ን​ንት ብዙ ናቸው።

7 ሳት​መ​ረ​ምር አት​ን​ቀፍ፤ አስ​ቀ​ድ​መህ ተረዳ፥ በኋ​ላም ትቈ​ጣ​ለህ።

8 ሳት​ሰማ አት​መ​ልስ፤ በሌ​ላ​ውም ነገር ውስጥ አት​ግባ።

9 ግዳ​ጅ​ህም ባል​ሆነ ነገር አት​ጨ​ነቅ፤ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ጋርም በፍ​ርድ አት​ቀ​መጥ።

10 ልጄ ሆይ፥ ሥራ​ህን አታ​ብዛ፤ ብታ​በዛ ትከ​ብር ዘንድ አያ​ሠ​ለ​ጥ​ን​ህ​ምና፤ ብት​ሮጥ አታ​መ​ል​ጥም፥ ብት​ከ​ተ​ልም አታ​ገ​ኝም።

11 የሚ​ቸ​ኩ​ልና የሚ​ሠራ፥ የሚ​ደ​ክ​ምም አለ፤ ነገር ግን እጅግ ይቸ​ገ​ራል።

12 ደክሞ ሳለም የማ​ይ​ለ​ምን፥ ምንም ማድ​ረግ ሳይ​ችል የሚ​ገዛ አለ፤ ምንም ቢጸና ፈጽሞ የሚ​ቸ​ገር አለ።

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በመ​ል​ካም ዐይን ቢያ​የው ከች​ግሩ ያነ​ሣ​ዋል። ከፍ ከፍ ያደ​ር​ገ​ዋል፥ ያከ​ብ​ረ​ዋል፥ ብዙ ሰዎ​ችም ያደ​ን​ቁ​ታል።

14 መል​ካ​ምና ክፉ፥ ሕይ​ወ​ትና ሞት፤ ድህ​ነ​ትና ብል​ጽ​ግና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ናቸው።

15 ጥበብ፥ ማስ​ተ​ዋ​ልና ሕግን ማወቅ፥ ፍቅ​ርና መል​ካም ሥራን መሥ​ራት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይመ​ጣሉ።

16 ስሕ​ተ​ትና ጨለማ ከመ​ወ​ለ​ዳ​ቸው ጀምሮ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ኖረ​ዋል። ክፋ​ትም በእ​ርሱ ደስ ከሚ​ሰ​ኙት ጋር አብሮ ያድ​ጋል።

17 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው ጻድ​ቃ​ንን ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለች፤ ፈቃ​ዱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ ታሰ​ኛ​ለች።

18 እየ​ነ​ፈገ በን​ፍ​ገቱ ብዛት የሚ​ከ​ብር ሰው አለ። በእ​ር​ስ​ዋም ደስ​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ባ​ታል።

19 ያርፍ ዘንድ ተስፋ ባደ​ረገ ጊዜ፥ “እበ​ላ​ለሁ እጠ​ጣ​ለሁ፥ እን​ግ​ዲ​ህስ ደስ ይለ​ኛል፥ በቃ​ኝም” ባለ ጊዜ፥ የሚ​ሞ​ት​ባ​ትን ቀን አያ​ው​ቅም፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ሁሉ ለባ​ዕድ ትቶ እርሱ ይሞ​ታል።

20 በቃል ኪዳ​ንህ ቁም፤ በእ​ር​ሱም ተማር፤ በሥ​ራ​ህም ሸም​ግል።

21 የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሥራ​ቸው አያ​ስ​ጐ​ም​ጅህ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመን፥ ድካ​ም​ህ​ንም ተስፋ አድ​ርግ፥ ሁሉ በአ​ንድ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቀሊል ነውና፥ ድሃ​ው​ንም ድን​ገት ያከ​ብ​ረ​ዋ​ልና።

22 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት ለጻ​ድ​ቃን ዋጋ​ቸው ናት፥ የጻ​ድ​ቅም በረ​ከቱ ትበ​ዛ​ለች።

23 “የአ​ገ​ል​ግ​ሎቴ ትርፍ ምን​ድን ነው? ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ የማ​ገ​ኘው መል​ካም ነገር ምን​ድን ነው?” አት​በል።

24 “እን​ግ​ዲ​ህስ በቃኝ፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ አል​ቸ​ገ​ርም” አት​በል።

25 በመ​ል​ካም ቀን ጊዜ ክፉ ይረ​ሳል፤ በክፉ ቀንም ጊዜ መል​ካም ይረ​ሳል።

26 የሞት ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቀሊል ነው፤ ለሰው እንደ ሥራው ዋጋ​ውን ይከ​ፍ​ለ​ዋ​ልና።

27 በክፉ ቀን ጥጋብ ያቀ​ና​ጣል፤ የሰ​ውም ሥራው በፍ​ጻሜ ዘመኑ ይታ​ወ​ቃል።

28 ፍጻ​ሜ​ውን ሳታይ ሰውን ብፁዕ አት​በ​ለው፥ የሰው አኗ​ኗሩ በል​ጆቹ ይገ​ለ​ጣል።


ጓደ​ኛን ስለ መም​ረጥ

29 ተን​ኰ​ለኛ ብዙ ይተ​ነ​ኰ​ል​ብ​ሃ​ልና ያገ​ኘ​ኸ​ውን ሰው ሁሉ ወደ ቤትህ አታ​ግባ።

30 ቆቅ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል፥ የት​ዕ​ቢ​ተኛ ሰውም ልቡ እን​ደ​ዚሁ ነው፤ መከ​ራ​ው​ንም እንደ ጕበኛ ይመ​ለ​ከ​ታ​ታል።

31 ተን​ኰ​ለኛ ሰው በበጎ ፋንታ ክፉ ነገ​ርን ይከ​ፍ​ል​ሃል፤ ሳይ​ኖ​ር​ብህ ነው​ርን ያወ​ጣ​ብ​ሃል።

32 በእ​ሳት ትን​ታግ ብዛት ፍሙ ይበ​ዛል፤ ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም ሰው​ነ​ቱን ያድ​ድ​ና​ታል።

33 ክፉ ነገ​ርን ይሠ​ራ​ብ​ሃ​ልና፥ ሁል​ጊዜ ስድ​ብን እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ግ​ብህ ከክፉ ሰው ተጠ​በቅ።

34 ባዕድ ሰውን ከአ​ንተ ጋር ብታ​ሳ​ድር ያው​ክ​ሃል፤ ይወ​ነ​ጅ​ል​ሃል፥ ከገ​ን​ዘ​ብ​ህም ይለ​ይ​ሃል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች