Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 93 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በአ​ራ​ተኛ ሰን​በት የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቃይ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ልጥ ተበ​ቃይ ነው።

2 የም​ድር ፈራጅ፥ ከፍ ከፍ አለ፤ ለት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው።

3 አቤቱ፥ ኃጥ​ኣን እስከ መቼ? ኃጥ​ኣን እስከ መቼ ይታ​በ​ያሉ?

4 ይከ​ራ​ከ​ራሉ፥ ዐመ​ፃ​ንም ይና​ገ​ራሉ፤ ዐመ​ፃ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ይና​ገ​ራሉ።

5 አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን አዋ​ረዱ፥ ርስ​ት​ህ​ንም አሠ​ቃዩ።

6 ባል​ቴ​ቲ​ቱ​ንና ድሃ አደ​ጉን ገደሉ፥ ስደ​ተ​ኛ​ው​ንም ገደሉ።

7 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይም፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ አያ​ው​ቅም” አሉ።

8 ሰነ​ፎች ሕዝብ ሆይ፥ ልብ አድ​ርጉ፤ ሰነ​ፎ​ችም መቼ ይጠ​በ​ባሉ?

9 ጆሮን የተ​ከ​ለው አይ​ሰ​ማ​ምን? ዐይ​ንን የሠ​ራው አያ​ይ​ምን?

10 አሕ​ዛ​ብ​ንስ የሚ​ገ​ሥ​ጸው፥ ለሰ​ዎ​ችም ዕው​ቀ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው እርሱ አይ​ዘ​ል​ፍ​ምን?

11 የጠ​ቢ​ባን ዐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።

12 አቤቱ፥ አንተ የገ​ሠ​ጽ​ኸው ሕግ​ህ​ንም ያስ​ተ​ማ​ር​ኸው ሰው ብፁዕ ነው።

13 ከክ​ፉ​ዎች ዘመ​ናት ይወ​ገድ ዘንድ ለኃ​ጥ​ኣን ጕድ​ጓድ እስ​ኪ​ቆ​ፈር ድረስ።

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን አይ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ርስ​ቱ​ንም አይ​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና

15 ፍርድ ለእ​ው​ነ​ተኛ እስ​ኪ​መ​ለስ ድረስ፥ ልበ ቅኖ​ችም ሁሉ ይከ​ተ​ሉ​አ​ታል።

16 ስለ ክፉ​ዎች ማን ይከ​ራ​ከ​ር​ል​ኛል? ዐመ​ፃ​ንስ ስለ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ ማን ይቆ​ም​ል​ኛል?

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የረ​ዳኝ ባይ​ሆን ነፍሴ ለጥ​ቂት ጊዜ በሲ​ኦል ባደ​ረች ነበር።

18 እግ​ሮች ተሰ​ና​ከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ረዳኝ።

19 አቤቱ ለልቤ እንደ መከ​ራዋ ብዛት፥ ማጽ​ና​ና​ትህ ነፍ​ሴን ደስ አሰ​ኛት።

20 በሕግ ላይ ድካ​ምን የሚ​ፈ​ጥር፥ የዐ​መፃ ዙፋን አይ​ቃ​ወ​ም​ህም፥

21 የጻ​ድ​ቅን ነፍስ ያድ​ና​ታል፥ በን​ጹሕ ደምም ይፈ​ር​ዳል።

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጠ​ጊ​ያዬ ሆነኝ፥ አም​ላኬ የተ​ስ​ፋ​ዬም ረዳት ነው።

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ክፋ​ታ​ቸው ፍዳ​ቸ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋል፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች