Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 92 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በሰ​ን​በት ቀን የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ ክብ​ሩ​ንም ለበሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ለበሰ፥ ታጠ​ቀም፤ ዓለ​ም​ንም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ አጸ​ናት።

2 አቤቱ፥ ዙፋ​ንህ ከጥ​ንት ጀምሮ የተ​ዘ​ጋጀ ነው፥ አን​ተም መቼም መች እስከ ዘለ​ዓ​ለም ነህ።

3 አቤቱ፥ ወን​ዞች ከፍ ከፍ አደ​ረጉ፥ ወን​ዞች ቃሎ​ቻ​ቸ​ውን ከፍ ከፍ አደ​ረጉ።

4 ከብዙ ውኆች ድምፅ የተ​ነሣ የባ​ሕር እን​ቅ​ስ​ቃ​ሴዋ ድንቅ ነው። ድን​ቅስ በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

5 ምስ​ክ​ርህ እጅግ የታ​መነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤ​ትህ ምስ​ጋና ይገ​ባል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች