መዝሙር 147 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር። ሃሌ ሉያ። 1 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥ 2 ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና። 3 ለወሰኖችሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ። 4 ቃሉን ወደ ምድር ይልካል፥ ነገሩም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል። 5 በረዶውን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤ 6 በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ ቅዝቃዜውንስ ማን ይቋቋማል? 7 ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል። 8 ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዐቱንና ፍርዱንም ለእስራኤል ይናገራል። 9 ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። |