Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 141 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በዋሻ በነ​በረ ጊዜ የዳ​ዊት ትም​ህ​ርት።

1 በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ንሁ።

2 ልመ​ና​ዬን በፊቱ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም በፊቱ እና​ገ​ራ​ለሁ።

3 ሰው​ነቴ በላዬ ላይ ባለ​ቀች ጊዜ አቤቱ፥ መን​ገ​ዴን አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ በም​ሄ​ድ​ባት በዚ​ያች መን​ገድ ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ።

4 ወደ ቀኝም ተመ​ልሼ አየሁ፥ የሚ​ያ​ው​ቀ​ኝም አጣሁ፤ መሸ​ሸ​ጊ​ያም የለ​ኝም፥ ስለ ሰው​ነ​ቴም የሚ​መ​ራ​መር የለም።

5 አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ “አንተ ተስ​ፋዬ ነህ፥ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር አንተ ዕድል ፋን​ታዬ ነህ” አልሁ።

6 እጅግ ተዋ​ር​ጃ​ለ​ሁና ወደ ልመ​ናዬ ተመ​ል​ከት፤ በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና ከከ​በ​ቡኝ አድ​ነኝ።

7 አቤቱ፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግን ዘንድ ሰው​ነ​ቴን ከእ​ሥ​ራት አው​ጣት፤ ዋጋ​ዬን እስ​ክ​ት​ሰ​ጠኝ ድረስ ጻድ​ቃን እኔን ይጠ​ብ​ቃሉ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች