Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 126 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ካል​ሠራ፥ ቤትን የሚ​ሠሩ በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማን ካል​ጠ​በቀ፥ የሚ​ጠ​ብቁ በከ​ንቱ ይተ​ጋሉ።

2 በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው። ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥ እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥ ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።

3 እነሆ፥ ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆ​ድም ፍሬ የእ​ርሱ ዋጋ ነው።

4 በኀ​ያል እጅ እን​ዳሉ ፍላ​ጾች፥ የተ​ጣሉ ሰዎች ልጆች እን​ዲሁ ናቸው።

5 ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ምኞ​ቱን የሚ​ፈ​ጽም ሰው ብፁዕ ነው፤ ጠላ​ቶ​ቹን በአ​ደ​ባ​ባይ በተ​ና​ገረ ጊዜ እርሱ አያ​ፍ​ርም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች