መዝሙር 123 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የዳዊት የመዓርግ መዝሙር። 1 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦ 2 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ 3 የመዓት ቍጣቸውን በላያችን ባነሡ ጊዜ፥ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፥ 4 በውኃ ባሰጠሙን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፤ 5 ነፍሳችንም ከጐርፍ አመለጠች፤ ነፍሳችን ከክርክር ውኃ አመለጠች፤ 6 ወደ ከባቢ ወጥመዳቸው ያላገባን እግዚአብሔር ይመስገን። 7 ሰውነታችን ግን እንደ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረች፥ እኛ ግን ዳን። 8 ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር ስም ነው። |