Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የጻ​ድ​ቃ​ንና የኃ​ጥ​ኣን ትር​ጓሜ

1 ምስ​ጉን ነው፥ በዝ​ን​ጉ​ዎች ምክር ያል​ሄደ፥ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መን​ገድ ያል​ቆመ፥ በዋ​ዘ​ኞ​ችም ወን​በር ያል​ተ​ቀ​መጠ ሰው።

2 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ብቻ ፈቃዱ የሆነ፥ ሕጉ​ንም በቀ​ንና በሌ​ሊት የሚ​ያ​ስብ፥

3 እር​ሱም በውኃ ፈሳ​ሾች ዳር እንደ ተተ​ከ​ለች፥ ፍሬ​ዋን በየ​ጊ​ዜዋ እን​ደ​ም​ት​ሰጥ፥ ቅጠ​ል​ዋም እን​ደ​ማ​ይ​ረ​ግፍ ዛፍ ይሆ​ናል፤ የሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል።

4 ኃጥ​ኣን እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም። ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ናቸው።

5 ስለ​ዚህ ዝን​ጉ​ዎች በፍ​ርድ፥ ኃጥ​ኣ​ንም በጻ​ድ​ቃን ምክር አይ​ቆ​ሙም።

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ንን መን​ገድ ያው​ቃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣን መን​ገድ ግን ትጠ​ፋ​ለች።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች