ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ መቃብያን ካልእ 18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የሙታንን መነሣት የማታምኑ ሰዎች፥ ምን ያህል ስሕተትን ትስታላችሁ? ወደማታውቁትም ቦታ በወሰዷችሁ ጊዜ፥ በነፍስና በሥጋ በአንድነት የሙታንን መነሣት ስለ አላመናችሁ ወደ ገሃነም በጣሏችሁ ጊዜ ያንጊዜ የማይረባ ጸጸትን ትጸጸታላችሁ። 2 ትቢያና ዐመድ የሆኑ ሙታን እንደማይነሡ እኛ እናውቃለን እያላችሁ የባልንጀሮቻችሁን ልቡና ታስታላችሁና በጎውንም ቢሆን፥ ክፉውንም ቢሆን እንደ ሠራችሁ ዋጋችሁን ትቀበላላችሁ። 3 ስለዚህም ባልንጀሮቻቸውን ያስታሉ፤ ለሞታቸው ዕረፍት የለውምና፥ ለመቅሠፍታቸውም ኀይል የለውምና፥ በድካማቸውም የጸኑ አልሆኑምና፥ በእግዚአብሔር አደባባይም ይቆሙ ዘንድ አላቸውና። 4 በመዓቱም በሚገሥጻቸው ጊዜ፥ ክፉም ስለ አደረጉ በሚቈጣቸው ጊዜ እጅግ ያፍራሉ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ሳያውቁ ይናገራሉና። ከየት እንደ መጡም አያውቁምና። 5 የሚሄዱበትንም ገሃነም አያውቁም፤ ቍጡዎች፥ በሥራቸውም ጠማሞችና ክፉዎች ስለ ሆኑ እንደ ልቡናቸው ጥመት ለባልንጀሮቻቸው ያስተምራሉና፤ ትንሣኤ ሙታንም የለም እያሉ ጠማማ ነገርን የሚያስተምሩ ናቸውና። 6 ያንጊዜም ሙታን እንደሚነሡ ያውቃሉ፤ ለሰው ልጆች ወገን ሁሉ የሚሆነውን የሙታን ትንሣኤ ስለ አላመኑ እንደሚፈረድባቸው ያውቃሉ። 7 ሁላችን የአዳም ልጆች ስለ ሆንን በአዳምም ምክንያት ሞተናልና፥ ሁላችንም በአባታችን በአዳም ስሕተት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሞት ፍርድ አግኝቶናልና። 8 ዳግመኛም በሠራነው ሥራችን ፍዳችንን እንቀበል ዘንድ ከዚያ ከአባታችን ከአዳም ጋራ እንነሣለን፤ በአባታችን በአዳም አለማወቅ ዓለም ለሞት ተገዝትዋልና። 9 ስለዚህም በአዳም መተላለፍ ፍዳን እንቀበላለን፤ ሥጋችንም በመቃብር ውስጥ ቀለጠች፤ አጥንቶቻችንም ደቀቁ። 10 ምድርም ቅልጥማችንን ጠጣች፤ ጠፋንም፤ ደም ግባታችንም በትቢያ ጠፋ፤ ሥጋችንም በመቃብር ተቀበረ፤ የአማረ ቃላችንም በመሬት ተቀበረ። 11 ከሚያበሩ ዐይኖቻችንም ትሉ ወጣ፤ መልካችንም በመቃብር ጠፋ፤ ትቢያም ሆንን። 12 መልከ መልካም የነበሩ፥ ቁመታቸውም ያማረ፥ የቃላቸውም ንግግር የተቀላጠፈ የጐልማሶች የመልካቸው ደም ግባት ወዴት አለ? የአርበኞችስ ገናናነታቸው ወዴት አለ? 13 የነገሥታቱ ኀይላቸው፥ የመኳንንቱስ ክብራቸው ወዴት አለ? በፈረስ መጠረር፥ በወርቅና በብርም ማጌጥ፥ በሚያንጸባርቅ የጦር መሣሪያም መጠረር ወዴት አለ? 14 የመባልዕት ጣዕምና ጣፋጩ የወይን መጠጥ የት አለ? |