ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ መቃብያን ካልእ 17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የስንዴ ቅንጣት ካልፈረሰች አትበቅልም፤ ፍሬም አታፈራም። የስንዴ ቅንጣት ብትፈርስ ግን ወደ ምድር ሥር ትሰዳለች፤ ቅጠልም ታወጣለች፤ ዝርዝርም ይሆናል፤ ፍሬም ያፈራል። 2 አንዲቱ የስንዴ ቅንጣት ብዙ ቅንጣት እንደምትሆን እናንተ ታውቃላችሁ። 3 እንደዚሁ ይህች ቅንጣት ከነፋስና ከውኃ፥ ከመሬትም የተነሣ ትበቅላለች፥ ፀሐይ ግን በእሳት ፋንታ ነው። ስንዴ ያለ ፀሐይ ፍሬ ማፍራት አይችልምና። 4 ነፋስም ስለ ነፍስ ፋንታ ነው፥ ያለ ነፋስም ስንዴ ማፍራት አይችልም፤ ውኃውም ምድርን ያጠጣታል፤ ያረካታልም። 5 መሬትም ውኃን ከጠጣች በኋላ ሥርን ታስገኛለች፤ ጫፏም ወደ ላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ እግዚአብሔርም የባረካትን ያህል ታፈራለች። 6 የስንዴ ቅንጣት ግን እግዚአብሔር የፈጠራት ነባቢት ነፍስ ያደረችበት የአዳም አምሳል ነው፤ የወይን ግንድም እንደዚሁ ውኃ ይጠጣል፤ ሥርም ይሰድዳል፤ ቀጫጭኑ የሥሩ ገመድም ውኃን ይስባል። 7 ውኃዋንም ወደ ቅጠሎች ጫፍ ያወጣታል፤ ከእግዚአብሔር የተገኘ ጠል ረጃጅም የሐረጎችን ጫፎች ያጠጣቸዋልና። በፀሐይም ሙቀት ይዘረዝራል፤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ፍሬን ያፈራል። 8 ልብን ደስ የሚያሰኝ በጎ መዓዛንም ያደርጋል፤ በበሉትም ጊዜ እንደማያስርብ እህልና እንደማያስጠማ ውኃ ያጠግባል፤ በጠመቁትም ጊዜ የወይን ጠጅ ይሆናል። 9 በጠጡትም ጊዜ “ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል” ተብሎ በመዝሙር እንደ ተነገረ የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፤ ፈታ ፈታ ያለ ሰውም አፉን ከፍቶ በጠጣ ጊዜ ይሰክራል፤ በሳምባውም ይመላል፤ ደሙም ወደ ልቡ ይፈስሳል። 10 የወይን ስካር እጅግ ያስታልና አእምሮውን ያሳጣዋል፤ ጐጻጕጹንና ገደሉንም እንደ ሰፊ ሜዳ ያደርገዋል፤ በእጁና በእግሩ ያለውንም እንቅፋትና እሾህ አያውቅም። 11 እግዚአብሔርም ፈቃዱን በሚያደርጉና የሙታንን ትንሣኤ በሚያምኑ ስሙ ይመሰገን ዘንድ በወይን ግንድና በፍሬዋ እንዲሁ አደረገ። 12 የሙታንን መነሣት የሚያምኑትንም በሕይወት ማደሪያ ደስ ያሰኛቸዋል። |