መዝሙር 93 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 93 1 እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም። 2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ። 3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ። 4 ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣ ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣ ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው። 5 ምስክርነትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ ቤትህ በቅድስና ይዋባል። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.