መዝሙር 99 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምእግዚአብሔር ታላቅ ንጉሥ ነው 1 እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋኑ ተቀመጠ፤ ምድርም ትናወጥ። 2 እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ። 3 የአንተን ታላቅና አስፈሪ ስም ያመስግኑ! እርሱ ቅዱስ ነው። 4 ፍትሕን የምትወድ ኀያል ንጉሥ ሆይ! ቅንነትን መሥርተሃል፤ በእስራኤል ዘንድ ፍትሕንና ጽድቅን ተግባራዊ አድርገሃል። 5 አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑት! በእግሩ ማረፊያ ሥር ስገዱ! እርሱ ቅዱስ ነው። 6 ሙሴና አሮን የእርሱ ካህናት ነበሩ፤ ሳሙኤልም ወደ እርሱ ከጸለዩት አንዱ ነው፤ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ሰማቸው። 7 በደመና ዐምድ ሆኖ ተናገራቸው፤ የሰጣቸውንም ደንብና ድንጋጌ ፈጸሙ። 8 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ጸሎታቸውን ሰማሃቸው፤ ይቅር ባይ አምላክም ሆንክላቸው፤ ነገር ግን ስለ በደላቸው እነርሱን ከመቅጣት ቸል አላልክም። 9 አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና፥ እርሱን አክብሩት፤ በተቀደሰው ተራራም ላይ ስገዱለት፥ |