Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 93 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔር ንጉሥ ነው

1 እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም።

2 እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘመናት ሁሉ በፊት አምላክ ነህ።

3 እግዚአብሔር ሆይ! ባሕሮች ይነሣሉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ የሞገዳቸውም ድምፅ ይሰማል።

4 ነገር ግን ድምፁ ከብዙ ውቅያኖሶች ድምፅ ይልቅ ታላቅ የሆነው ከባሕር ማዕበሎችም የበረታው እግዚአብሔር፥ ከሁሉ የበለጠ ኀያል ነው።

5 እግዚአብሔር ሆይ! ሕግህ ጽኑ ነው፤ መቅደስህም ለዘለዓለም ያማረና ቅዱስ ነው።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች