Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔር ከሰዎች የሚፈልገው ነገር

1 እግዚአብሔር ሆይ! ወደ መኖሪያህ መግባት የሚችል ማን ነው? በተቀደሰችው ተራራህስ ላይ ሊኖር የሚችል ማን ነው?

2 እርሱ ነቀፋ የሌለበት ሕይወትን የሚኖርና ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ፥ ከልቡም እውነትን የሚናገር፥

3 ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥ በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥

4 ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥ ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥ ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥

5 ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች